ኒጀር ማሪስቶፕስን ለመዝጋት ወሰነች

አለም አቀፍ ማሪስቶፕስ Image copyright Marie stopes

የኒጀር ባለስልጣናት ህገወጥ የፅንስ ማቋረጥ እያካሄደ በመሆኑ ማሪስቶፕስን ለመዝጋት ውሳኔ ማስተላለፋቸውን ሪፖርቶች አመለከቱ።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የእንግሊዙን አለም አቀፍ ድርጅት ማሪስቶፕስን ለመዝጋት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ምርመራ ከተደረገ በኋላ እንደሆነ የኒጀር ጤና ጥበቃ ሚኒስትርን በመጥቀስ ዘግቧል።

ኒጀር እንደ አውሮፓውያኑ በ2006 ባወጣችው ህግ መሰረት በአገሪቱ ፅንስ ማቋረጥ የሚቻለው የእናትየው ህይወት አደጋ ላይ ከወደቀ ብቻ ነው።

ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች

418 ኢትዮጵያዊያንን ከየመን ወደ አገር ቤት ማጓጓዝ ተጀመረ

ተቋሙን ለመዝጋት የኒጀር መንግስት የደረሰበትን ውሳኔ በተመለከተ እስከ አሁን ከማሪስቶፕስ በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም።

በኒጀር አንዲት እናት በአማካይ ሰባት ልጆች የሚኖሯት ሲሆን ይህ ደግሞ በአለም ላይ የውልደት ምጣኔያቸው ከፍተኛ ከሁኑ አገራት ኒጀርን ቀዳሚ አድርጓታል።

ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ ፅንስ ማቋረጥን በሚመለከት ጥብቅ ህግ ያላት ኬንያ በአለምአቀፉ ማሪስቶፕስ የሚሰጥ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎትን መዝጋቷ ይታወሳል።