በቢጫ እንቅስቃሴ (Yellow Movement) የተዘጋጀው 'እኔንም ስሙኝ' ዘመቻ

በአዲስ አበባ ሙዚየም የቀረበው 'ስትደፈር ምን ለብሳ ነበር? አውደ ርዕይ
አጭር የምስል መግለጫ በአዲስ አበባ ሙዚየም የቀረበው 'ስትደፈር ምን ለብሳ ነበር? አውደ ርዕይ

ጥቃት ሲደርስ ተጠቂዎችን የመውቀስ ልማድ አለ፤ አለባበሳቸው፣ ማህበራዊ ተግባቦታቸው፣ ከጥቃቱ በፊት የነበራቸው ባህሪ፣ ውሏቸው፣ የነበሩበት ቦታ፣ ከአጥቂው ጋር የነበራቸው ግንኙነት እናም ሌሎች በተደጋጋሚ ይነሳሉ።

ይህ ደግሞ 'እንደዚህ ባታደርግ፣ እንደዚህ ባትሆን ጥቃቱ አይፈፀምባትም ነበር' ወደ ሚል መላ ምት ያመራል፤ ጥቃቱን ካደረሰው ይልቅ ተጎጂዋ ላይ ጣት ይቀሰራል።

የተነጠቀ ልጅነት

"ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ

አሲድን እንደ መሳሪያ

የስነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት ሰብለ ኃይሉ በአንድ ወቅት የ14 ዓመት ህፃን የ5 ዓመት ልጅ ከደፈረ በኋላ የምክር አገልግሎት ለመስጠት ያነጋግሩታል፤ በድርጊቱ ስሜት ውስጥ ገብተው እንደነበር የሚያስታውሱት ባለሙያዋ ኮስተር ብለው

"አሁን ምን የሚሰማት ይመስልሃል?" ሲሉ ይጠይቁታል።

"አሳምኛታላሁ፤ ፈቅዳ ነው" ሲል በራስ በመተማመን ስሜት ይመልሳል ታዳጊው። ይህም ቀድሞ የነበራቸውን ስሜት አሳድጎት ቁጣ አስከተሉ።

ወደ ኋላ መለስ ብለው ሲያስቡት ታዳጊው ስለ ፈፀመው ድርጊትና ስለሚያደርሰው ጉዳት ቅንጣት ያህል አያውቅም ነበር ይላሉ።

አጋጣሚው 'ምን ለብሳ ነበር?' የሚለው ጥያቄ ትርጉም እንደማይሰጣቸው የገለፁበት አንዱ ምሳሌያቸው ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት በቅርቡ ያወጣው ጥናት ጠቅሰው ኢትዮጵያ በቅርብ ሰው በሚፈፀም ጥቃት ከዓለም አገራት ግምባር ቀደም ናት የሚሉት ባለሙያዋ "አባት ልጁን ፤ ወንድም እህቱን፤ ህፃናትና ከሃምሳ ዓመት በላይ አዛውንቶች ላይ ጥቃት የሚፈፀምባቸው በአለባበሳቸው ምክንያት ነው ወይ?" ሲሉ ይጠይቃሉ።

አጭር የምስል መግለጫ አንዲት ሴት ስትደፈር ለብሳው የነበረው ቀሚስ

ሃሳባቸውን የሚገልፁበት ሌላ ታሪክም ይመዛሉ ባለሙያዋ፤ የ3 ዓመት ህፃንን የመደፈር መራር ታሪክ አውስተው አንዲት ህፃን ስትደፈር 'ዳይፐር' አድርጋም ሊሆን ይችላል ይላሉ። በመሆኑም ሰበቡ ምክንያታዊ እንዳልሆነ ያስረዳሉ።

ምግብ ማብሰልና ማጽዳት የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለመቀነስ

ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠርና ውይይት ለማካሄድ '16 ቱ ብርቱካናማ ቀናት' ዘመቻ 'እኔንም ስሙኝ' (Hear Me too) በሚል በቢጫ እንቅስቃሴ (Yellow Movement) አዘጋጅነት ኅዳር 16፣2011 ዓ.ም ተጀምሯል።

ማህበራዊ ሚዲያውን የተቆናጠጠው እንቅስቃሴው ስሙኝ አትውቀሱኝ ( ተጠቂዎችን መውቀስ በተመለከተ) ፣ ለምን አልተናገርኩም(የሚደርስባቸውን ሪፖርት ስለማድረግ)፣ ህጉን ጠይቁ ( ሴቶች ለመሪዎቻቸው ጥያቄ የሚያቀርቡበትና የህግ ክፍተቶችን የሚያነሱበት)እንዲሁም ማንን ነው እየሰማን ያልሆነው?( ራሳችንን የምንጠይቅበት) በሚሉ ንዑሳን አርዕስቶች በተለያዩ የመድረክ ዝግጅቶችና አውደ ርዕዮች ዘመቻው እየተካሄደ ይገኛል።

የእንቅስቃሴው አንዱ አካል የሆነውና 'ምን ለብሳ ነበር? በሚል በአዲስ አበባ ሙዚየም አዳራሽ የቀረበው አውደ ርዕይ ግን የብዙዎችን ስሜት የነካ ነው። ስትደፈር ምን ለብሳ ነበር?

Image copyright Yellow Movement FB
አጭር የምስል መግለጫ አንዲት ሴት ስትደፈር ለብሳው የነበረው ቀሚስ

በአዳማ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት በሴቶች ህፃናት ክፍል የሚሰሩት ኢንስፔክተር ስንታየሁ በተላ ካላቸው የስራ ልምድ አንፃር ህብረተሰቡ አለባበስን ለጥቃት መነሻ አድርጎ ያስብ እንጂ እውነቱ ግን ሌላ ነው ይላሉ።

ራሷ እንኳን መልበስ የማትችል፤ ቤተሰብ የሚያለብሳት ሕፃን በምትደፈርበት አገር 'ይህን ለብሳ ነበር' ማለት የማይሆን ሰበብ እንደሆነ ያስረዳሉ።

በእርግጥ እርሳቸው እንደታዘቡት በሚያገለግሉበት ክፍል ጥቃቱን ፈፅሟል የተባለውን ተጠርጣሪ ለመመርመር ከጥቃት አድራሹ ይልቅ ተጠቂዋ ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ያነሳሉ።

"ምን ለብሰሽ ነበር?፣ ሁኔታው ምን ይመስል ነበር? የት ነበር? እየተባለች የምትናዘዘው እርሷ እንጂ እሱ አይደለም፤ ይህ ግን ስህተት ባይሆንም እነርሱ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጉ ጥፋተኝነት እንዲሰማቸው ያደርጋል" ሲሉ ያስረዳሉ።

ይህም በቁስላቸው ላይ እንጨት እንደ መስደድ ነው በማለት ማንኛውም ሰው ጥቃት አድራሹም ሆነ ጥቃት የሚደርስበት የራሱ ወገን እንደሆነ ተገንዝቦ ራሱን ከዚህ እኩይ ተግባር ሊቆጥብ ይገባል ሲሉ ያስረዳሉ ኢንስፔክተሯ።

"እኔና ልጄ ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ ሊኖረን አይችልም" የሚሉት ኢንስፔክተሯ ዘመንና ቴክኖሎጂ በተቀየረ ቁጥር አለባበስን ጨምሮ ብዙ ነገሮች ይለወጣሉ፤ በመሆኑም ማህበረሰቡም ይህንን ለውጥ ሊቀበል ይገባል፤ ህብረተሰቡ ከጊዜው ጋር መሄድ አለበት በማለት ይመክራሉ።

ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች

በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ

ሴቶችን ለደረሰባቸው ጥቃት ተወቃሽ ማድረጉ በህግ አካላትና በፍትህ ስርዓቱም የሚታይ ጉዳይ ነው የሚሉት ደግሞ የህግ ባለሙያው አቶ አለማየሁ ባጫ ናቸው። "የህግ አካላትም ከማህበረሰቡ እንደመውጣታቸው ጭምር እነርሱም የተዛባው አመለካከት ተጎጂ ናቸው" ይላሉ።

'ምን ለብሳ ነበር'?

"ይሄን ለብሰሽ ነበር፤ ይሄን ሆነሽ ነበር፣ሲያናግርሽ በፀባይ ብታናግሪው... እያሉ የሚያልፉ አሉ፤ ይህም የፍትህ ስርዓቱን ማዛባቱ አይቀርም" ብለዋል።

ተጠቂዎችን የመውቀስ ልምድ (Victim Blaming) በጣም አደገኛ እና ጥቃት እንዳይቀር ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንደኛው ነው የሚሉት በሴታዊት የፕሮጀክት ኃላፊ እንዲሁም የዘመቻው መሪ ወ/ሪት አክሊል ሰሎሞን ናቸው።

ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነት እንቅስቃሴዎች ሰዎች የማያስተውሉትን ነገር እንዲያስተውሉት ያደርጋል ይላሉ።

"ተጠቂዎችን ስለ መውቀስ ሲወራ ብዙ ሰው ሳያውቅ ስለሚያደርገው ብዙ ጊዜ አለማስተዋል ይታያል፤ በመሆኑም ብዙ ጊዜ በድረ ገፆች የሚደረጉ ዘመቻዎች እንዲህ ዓይነት ቀላል የሚመስሉ አመለካከቶችን ለመለወጥ ፋይዳው ከፍተኛ ነው" ሲሉ ያብራራሉ።

ጥናት ባያካሂዱም በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ለውጦችን እየተመለከቱ እንደሆነ ይናገራሉ።

'16 ቱ ብርቱካናማ ቀናት' ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች አስመልክቶ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ ቀን ተንተርሶ ኅዳር 16 የተጀመረ ሲሆን መዳረሻውን የዓለም የሰብዓዊ መብት ቀንን ታሳቢ በማድረግ ታኅሳስ 1፣2011 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ወ/ሪት አክሊል ሰሎሞን ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ