በስህተት 12 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ አለብሽ የተባለችው ሃገርና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

Image copyright Matt Cardy

ማዕከላዊ አፍሪካ

የራሺያው ቪቲቢ ባንክ ባለፈው ወር ባወጣው የብድር ዝርዝር ላይ የማዕከላዊ አፍሪካ መንግስት 12 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ አለበት ያለው በስህተት መሆኑን ገለጸ።

ባንኩ እንዳስታወቀው መረጃው የተለቀቀው በስህተት ሲሆን፤ ሃገሪቱ ምንም ዕዳ የለባትም ብሏል።

ማደጋስካር

የማደጋስካር የቀድሞ ሁለት ፕሬዝዳንቶች አንድሬይ ራሆሊና እና ማርክ ራቫሎማናና ፕሬዝንት ለመሆን በቀጣይ ወር ሊወዳደሩ ነው።

በመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሁለቱም ተፎካካሪዎች 50 በመቶ ድምጽ ማግኘት አልቻሉም ነበር።

ኦዴፓ እና ኦዴግ ተዋሃዱ

የ'ሰከረ' አዋላጅ ሐኪም እናትና ልጅን ገደለ

የሴኔጋል

የሴኔጋል መንግስት በፈረንሳይ ሙዚየም ውስጥ የሚገኘው ታዋቂ ስዕል እንዲመለስላት ጠየቀ።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ማንኛውም ያለሃገሪቱ ፈቃድ የተወሰዱ ሃብቶች መመለስ አለባቸው ማለታቸው ይታወሳል።

ሌሴቶ

አፍሪካዊቷ ሃገር ሌሴቶ እጸ ፋርስን ለመድሃኒትነት ለመላው ዓለም መሸጥ ልትጀምር ነው።

ሌሴቶ ባለፈው ዓመት እጹን በህጋዊ መንገድ ለማብቀል ፈቃድ የሰጠች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሃገርም ሆና ነበር።

ህንድ

ህንድ ውስጥ የሚገኝ ዶክተር ሰክረህ የቀዶ ህክምና ፈጽመሃል ተብሎ በቁጥጥር ስር ዋለ።

በቀዶ ጥገና ልጅ ለመገላገል የመጣችው እናትና ልጇም በዚሁ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።

ኢንዶኔዢያ

ባለፈው ወር ኢንዶኔዢያ ውስጥ የተከሰከሰውና ለ189 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው አውሮፕላን ለመብረር ብቁ አልነበረም ተባለ።

የሃገሪቱ የትራንስፖርት ደህንነት መስሪያ ቤት እንደገለጸው አውሮፕላኑ ተገቢውን ጥገና ሳያገኝ ነው ለበረራ ጥቅም ላይ የዋለው።

አውስትራሊያ

በሺዎች የሚቆጠሩ አውስትራሊያውያን በአካባቢኣቸው በተከሰተ ከፍተኛ የእሳት ሰደድ ምክንያት መኖሪያቸውን ለቅቀው እንዲሄዱ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።

ኩዊንስላንድ በተባለው ከተማ በኩል ከ150 የተለያዩ አቅጣጫዎች ሰደድ እሳት ተነስቷል ተብሏል።

418 ኢትዮጵያዊያንን ከየመን ወደ አገር ቤት ማጓጓዝ ተጀመረ

". . . ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል" ጠ/ሚ ዐብይ

ቻይና

አንድ ቻይናዊ የህክምና ጥናት ባለሙያ በምርምር ኤችአይቪ ኤድስ የማያጠቃቸው ህጻናት እንዲወለዱ ማድረጉን ገለጸ።

እሱ የሚሰራበት የሸንዘን ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ጉዳዩን እምረምረዋለው ብሏል።

ኒውዝላንድ

ኒውዝላንድ ሁዋዌ የተረባለው የቻይና ቴሌኮም ድርጀት በሃገሪቱ የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት እንዳይሰጥ ከለከለች።

ምክንያቱ ደግሞ ከሃገሪቱ የመረጃ ደህንነት ጋር በተያያዘ ድርጅቱ አመኔታን ማግኘት ስላልቻለ ነው ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች