ቻይናዊው ሳይንቲስት መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን ማስተካከሉ ወቀሳ አስነሳ

ቻይናዊው ሳይንቲስት ሂ ጂያንኩ Chinese scientist He Jiankui speaks at the Second International Summit on Human Genome Editing in Hong Kong Image copyright AFP

ቻይናዊው ሳይንቲስት የመንታዎቹ "ዘረ መል" ማስተካከል ትክክል ነው ሲል ተከራከረ።

ሳይንቲስቱ ሆንግ ኮንግ በተካሄደ የዘረ መል (ስነ ባህርይ) ስብሰባ ላይ ባደረገው ንግግር የመንታዎቹን ፅንስ ኤች አይ ቪ ኤድስ እንዳይዛቸው አድርጎ ውስጣዊ አወቃቀራቸውን ማስተካከሉ የሚኮራበት እንደሆነ ተናግሯል።

በዚህ ሳምንት ይፋ ያደረገው ስራው ገና አልተረጋገጠም።

"ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም

ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች

በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ

የተለያዩ ሳይንቲስቶች የሳይንቲስቱን ስራ ያወገዙ ሲሆን፤ ቻይናን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት ዘረ መልን መቀየር የተከለከለ ነው።

ሳይንቲስቱ የሚሰራበት ሸንዘን የሚገኘው ሳውዘርን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ቴክኖሎጂ ስለ ምርምሩ ምንም እንደማያውቅ ጠቅሶ በአስቸኳይ ምርመራ እንደሚጀምርም አሳውቋል።

ሳይንቲስቱ ከየካቲት ወር ጀምሮም ሳይከፈለው እረፍት እንደወጣም ዩኒቨርስቲው ጨምሮ አስታውቋል።

ሳይንቲስቱም የምርምር ስራውን በተመለከተ ዩኒቨርስቲው ምንም እንደማያውቅና የሙከራ ስራውንም በራሱ ገንዘብ እንደሸፈነ ገልጿል።

ሉሉና ናና የሚባሉት መንትዮች በጤናማ ሁኔታ እንደተወለዱና ለቀጣዩ 18 ዓመታትም ክትትል እንደሚያደርግላቸው ገልጿል።

ለዚህ የሙከራ ስራ ስምንት ኤችአይቪ ቫይረስ ያለባቸው አባቶችና ኤች አይቪ ቫይረስ ነፃ የሆኑ እናቶች ባለትዳሮች በፈቃደኝነት የተሳተፉ ሲሆን ሁለት ባለትዳሮች ሙከራውን አቋርጠው ጥለው እንደወጡም ገልጿል።

ሳይንቲስቱ የምርምር ስራውን ለግምገማ ወደ አንድ ሳይንሳዊ የምርምር ስራዎች የሚወጡበት ቦታ ልኬዋለሁ ቢልም ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥቧል።

በአሁኑ ወቅትም እንዲሁ ሌላ ፅንስ ላይ ሙከራ እያደረገ መሆኑን ጠቅሶ "ምርምሩ ሳይጠበቅ ይፋ በመውጣቱ ይቅርታ ጠይቋል"

ሳይንቲስቶች ግን ፅንሱ ላይ የተቀየረው የዘረ መል ባህርይ ወደፊት ለሚቀጥለው ትውልድ የሚተላለፍ መሆኑን በመስጋት በተፈጥሮ ጣልቃ መግባት መሆኑን አስምረውበታል።

ተያያዥ ርዕሶች