የዕፀ ፋርስ የገበያ እሽቅድምድም በሌሴቶ

ማምፖ ቱሎ

ሌሶቶ በአለም ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ገበያ እያገኘ ያለውን ለመድኃኒትነት የሚያገለግለውን ዕፀ-ፋርስ ኢንዱስትሪ ለመቀላቀል እየጣረች ቢሆንም የቢቢሲው ቩማኒ ምክሂዜ በበኩሉ ግለሰቦች ህጋዊ ባልሆነ ንግድ ዕፀ ፋርስን ለመዝናኛነት እንደሚጠቀሙበት ዘግቧል።

ከነዚህም አምራቾች አንዷ ማምፖ ቱሎ ስትሆን ፤ የቢቢሲው ጋዜጠኛ በቦታው ላይ ሲደርስ የደረቀውን የዕፀ ፋርስ ቅጠሎች በእጇ እያፈሰች ቤቷ ወለል ላይ በተዘረጋው ትልቅ የላይነን ቦርሳ ውስጥ በማስገባት ላይ ነበረች።

ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ

"ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም

ማፖቴንግ በሚባል መንደር ውስጥ ነዋሪነቷን ያደረገችው ማምፖ ለዘመናት ዕፀ ፋርስን ስታበቅል ነበር።

ከመዲናዋ ማሴሩ በሰባ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው መሬቷ ሸለቋማ ሲሆን፤ ሀገሪቷ በምትታወቅበት ተራራም የተከበበ ነው።

ይህ መንፈስን በሚሰርቀው አካባቢ ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ዕፀ ፋርስ የሚበቅል ሲሆን ለአስርት አመታትም ለመዝናኛነት ይጠቀሙበታል።

ቦታው በከፍተኛ ስፍራ መገኘቱ፣ ከመሬቱ ለምለምነት፣ በማዳበሪያ አለመበከሉ፤ የአካባቢውን አብቃዮች በዓለም ላይ የሚፈለግ ጥሩ ምርት እንዲያፍሱ አድርጓቸዋል።

በተቃራኒው በመዲናዋ አካባቢ የተለያዩ ሰራተኞች ላብራቶሪ በሚመስል የአረንጓዴ ቤቶች ለመድኃኒትነት የሚያገለግለውን ዕፀ ፋርስን ለማብቀልና ከፍተኛ ገንዘብም ለማግኘት ኃገሪቷ እሽቅድምድም እያደረገች ነው።

በባለፈው አመት ሌሴቶ ዕፀ ፋርስን ለመድኃኒትነት ለመጠቀም ህጋዊ በማድረግ የመጀመሪያዋ ቀዳሚ አፍሪካዊ አገር ብትሆንም ኢንዱስትሪ ገና በጅማሮ ላይ ነው።

በትንሽ መሬት ዕፀ ፋርስን የሚያመርቱት ገበሬዎች ከመድኃኒት ዕፀ ፋርስ ጋር ሲወዳደር የቴክኖሎጂ አቅርቦትም ሆነ ንግዱ የሚያስፈልገው መነሻ ገንዘብ የላቸውም። የመድኃኒቱ ዕፀ ፋርስ በትልቅ ደረጃ የታሰበ ከመሆኑ አንፃር ጋር ሲወዳደር ያለውን ከፍተኛ የስራ እድል ለመፍጠርም ትግል ላይ ነው።

ነገር ግን የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ማምፖ ቱሎ ባላት ምርት ትተማመናለች።

"የእለት ጉርሳችን የምናገኘው ዕፀ ፋርስን በመሸጥ ነው። ስራ ያለው ለተማሩ ሰዎች ነው እሱም እምብዛም ነው። ትምህርትም ስላልተማርን ኑሯችንን የምንደግፈው ዕፀ ፋርስን በመሸጥ ነው" በማለት ለቢቢሲ ተናግራለች።

ምንም እንኳን ሌሴቶ ዕፀ ፋርስን ለመድኃኒትነት ለመጠቀም ህጋዊ ብታደርግም እንደነ ማምፖ ቱሎ ያሉት ግን አሁንም ምርታቸው ህገ ወጥ ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ