ጆርጂያ ሰሎሜ ዙራቢሽቪሊን የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት በማድረግ መረጠች

ሰሎሜ ዙራቢሽቪሊ Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ሰሎሜ ዙራቢሽቪሊ እኤአ በ1921 ከጆርጂያ ወደ ፈረንሳይ ከተሰደዱ ቤተሰቦች የተገኘች ልጅ ናት

ሰሎሜ ዙራቢሽቪሊ የጆርጂያን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ሆኑ።

ግለሰቧ ያሸነፉት በምርጫው ከተሰጠው ድምፅ 59 በመቶውን በማግኘት ነው።

አዲሷ ፕሬዝዳንት ስልጣን ላይ ባለው ፓርቲ ይደገፉ የነበረ ሲሆን ተፎካካሪያቸው ደግሞ የተቃዋሚው ህብረትን ወክለው ነበር የተወዳደሩት።

ጆርጂያ የፕሬዚዳንቱን ስልጣን የሚገድብ አዲስ ህገመንግስት በቅርቡ ተግባራዊ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።

አዲሷ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ሀገራቸው ከሩሲያና ከምዕራቡ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ማሻሻል ይፈልጋሉ።

የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ ብሔር- አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፡ በሚያውቋቸው ሰዎች አንደበት

ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች

እኚህ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ሩሲያና ጆርጂያ ግጭት ውስጥ በነበሩበት እኤአ በ2008 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን በወቅቱ የምዕራባውያን ደጋፊ መስለው ይታዩ ነበር።

በጆርጂያ ይህ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመጨረሻው ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ባለፈው ዓመት ተቃዋሚዎች ካነሱት ተቃውሞ በኋላ ሀገሪቱ ወደ ፓርላሜንታዊ አስተዳደር እንደምትሸጋገር ተነግሯል።

ጆርጂያ የአውሮጳ እና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ሀገራት ህብረት አባል ለመሆን መጠየቋን ተከትሎ የምዕራቡ አለም ሀገራት ይህንን ምርጫ በቅርበት ተከታትለዋል።

ተቃዋሚዎች በደጋፊዎቻቸው ላይ ወከባና ጥቃት መድረሱንና በድምፅ አሰጣጡ ላይ አንዳንድ ግድፈቶች መታየታቸውን ቅሬታ ቢያሰሙም ገዢው ፓርቲ ግን ክሱን አጣጥሎታል።

አለምአቀፍ ታዛቢዎችም ባለፈው ወር የተሰጠውን የመጀመሪያ ዙር ድምፅ አሰጣጥ "ለሁሉም እኩል እድል ያልሰጠ" ብለውት ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች