ትዊተር በሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስም የተከፈተውን ሀሰተኛ ገጽ ዘጋ

ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን/ የትዊተር መለያ Image copyright Getty Images/PA
አጭር የምስል መግለጫ በፕሬዚዳንቱ ስም የተከፈተው ሀሰተኛ አካውንት ማን እንደሚያስተዳድረው በግልፅ የታወቀ ነገር የለም

ትዊተር በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስም ተከፍቶ በእንግሊዝኛ ቋንቋ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረን ሀሰተኛ ገጽ ዘጋ።

ከማህበራዊ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው ትዊተር፤ @putinRF_eng የተባለውን ሀሰተኛ ገጽ ለመዝጋት የተገደደው ከሩሲያ ባለስልጣናት በደረሰው ይፋዊ ሪፖርት እንደሆነ አስታውቋል።

ትዊተር 70 ሚሊዮን ሃሰተኛ ገጾችን ዘጋ

የትራምፕ ትዊተር ገጽ በኩባንያው ሠራተኛ ተዘጋ

የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻዎች

ይሄው በአውሮፓውያኑ 2012 የተከፈተው ሀሰተኛ ገጽ ብዙ ጊዜ ፕሬዚደንቱ በአደባባይ የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች ይቀርቡበት ነበር።

ገጹ ባለፉት ስድስት ዓመታት ጊዜ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል።

በርካታ የገጹ ተከታዮችም ገጹ እውነተኛና በሌሎች አንጋፋ ሚዲያዎችም ማጣቀሻ የሚሆን አድርገው ያስቡታል።

ከሩሲያ ባለስልጣናት ቅሬታ እንደቀረበለት የሚገልፀው ትዊትር "ገጹ አንድን ግለሰብ መስሎ መቅረብን የሚመለከተውን የትዊተር ህግ የሚጥስ ነው፤ በሚያምታታና በሚያታልል መልኩ፣ ሌላን ሰው በመምሰል የትዊተር ገጾችን መጠቀም በዘላቂነት ለመዘጋት ይዳረጋል" ሲል አሳስቧል።

ምንም እንኳን ከፕሬዚዳንቱ ሀሰተኛ ገጽ ጀርባ ማን እንዳለ በግልፅ የታወቀ ነገር ባይኖርም የትዊተር ተጠቃሚዎች በሀሰተኛ ገጾች ሲጭበረበሩ ግን ይህ የመጀመሪያው አይደለም ብለዋል።

በዚህ ዓመት ብቻ በአሜሪካው ባለሃብት ዋረን ቡፌት ስም በተከፈተ ሀሰተኛ ገጽ ለወጣቶች አነቃቂ መልዕክት ተለጥፎ 2 ሚሊዮን ውዴታ(like) ማግኘቱን ለንግግራቸው ዋቢ አድርገዋል።

ነገር ግን ገጹ ሰማያዊ መለያ የሌለውና ስሙ ላይ የፊደላት ስህተት መገኘቱ እንዳባነናቸው ገልጸው ሀሰተኛ መሆኑን ጊዜ ሳይወስድባቸው ይፋ እንዳደረጉ አስታውሰዋል።

ተያያዥ ርዕሶች