አሜሪካዊው ወንጀለኛ '90 ሰዎች መግደሉን አመነ'

አሜሪካዊው ሳሙኤል ሊትል '90 ሰዎችን መግደሉን አመነ' Image copyright Los Angeles Times via Getty Images

ሶስት ሴቶችን መግደሉ ተረጋግጦበት በእስር ላይ የሚገኘው ወንጀለኛ፤ ባለፉት 40 ዓመታት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ 90 ሰዎችን መግደሉን አመነ።

'ኤፍቢአይ' የ78 ዓመቱ የዕድሜ ባለጸጋ ሳሙኤል ሊትል ምናልባትም በአሜሪካ የወንጀል ታሪክ ውስጥ በርካታ ሰዎችን የገደለ ወንጀለኛ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

የፌደራል እና የተለያዩ የአሜሪካ ግዛት መንግሥታት እ.ኤ.አ. ከ1970 እስከ 2005 ድረስ ከተገደሉት ሴቶች ጋር ሳሙኤል ሊትል የነበረውን ግነኙነት እየመረመሩ ነው።

መርማሪዎች ሳሙኤል ሊትል እስካሁን ከ34 ግድያዎች ጋር ግኑኘነት እንዳለው ደርሰንበታል ብለዋል።

"ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ

ኢትዮጵያ በዲፕሎማቶቿ ላይ ሽግሽግና ለውጥ ልታደርግ ነው

ሳሙኤል ሊትል 2014 ላይ ሶስት ሴቶችን መግደሉ በመረጋገጡ የዕድሜ ልክ እስራት ተላልፎበት ነበር።

ከወንጀለኛው የተወሰደ የዘረ መል ናሙና እንደሚያሳየው እ.ኤ.አ. በ1987 እና በ1989 ሎስ አንጀለስ ውስጥ ከተገደሉት ሶስት ሴቶች ጋር ተገናኘቶ ነበር።

በወቅቱ ሶስቱም ሴቶች ተደብድበው እና ታንቀው ከተገደሉ በኋላ አስክሬናቸው በተለያዩ ስፍራዎች ተጥሎ መገኘቱ ተዘግቧል።

ወንጀለኛው 2012 ላይ ነበር በቁጥጥር ሥር የዋለው።

በወቅቱ ሳሙኤል ሊትል ወንጀሉን አለመፈጸሙን ቢክድም በሶስት የተለያዩ ክሶች የዕድሜ ልክ እስራት ተበይኖበታል።

ከዚህ ፍርድ በፊትም የአስገድዶ መድፈር እና የዘረፋ ወንጀል ክስ ሪከርዶች ነበሩበት።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ፐርል ኔልሰን (በስተ ግራ) በሳሙኤል ሊትል የተገደለችውን የእናቷን ፎቶግራፍ ይዛ።

መርማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ገዳዩ የዕጽ ሱሰኛ እና ሴተኛ አዳሪ የሆኑ ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ጥቃቱን ይሰነዝራል።

መርማሪዎቹ ጨምረው እንደሚሉት አስክሬናቸውንም ማንነታቸው እንዳይለይ አድርጎ ይጥላል።

''የሊትል የግድያ ስልት ሟቾች በሰው ስለመገደላቸው ምንም አይነት ፍንጭ ትቶ አያልፍም። በአንድ ወቅት የቦክስ ስፖርት ተወዳዳሪ የነበረው ወንጀለኛ ተጠቂዎቹን በኃይል በቡጢ ይመታል። ከዚያም እራሳቸውን ሲስቱ አንቆ ይገድላቸዋል። አስክሬኖቹ በስለት የመወጋት ወይም በጥይት የመመታት ምልክቶች ስለሌላቸው ዕጽ በብዛት በመውስድ፣ በአደጋ ወይም ተፍጥሯዊ ሞት የሞቱ ለማስመሰል ይጥራል'' ይላል 'የኤፍቢአይ' ሪፖርት።

"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ

ትዊተር የፑቲንን ሀሰተኛ ገጽ ዘጋ

ፖሊስ እንደሚለው አብዛኛዎቹ ወንጀሎቹ የተፈጸሙት የዘረ መል ምረመራ ቴክኖሊጂ እውን ሳይደረግ በፊት በ1970ዎቹ እና 1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው።

'ኤፍቢአይ' የ78 ዓመቱ አዛውንት ሳሙኤል ሊትል የጤና ሁኔታ እክል እንዳለበት በመጠቀስ ቀሪ ዘመኑን ቴክሳስ ግዛት ውስጥ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ሊያሳልፍ እንደሚችል አስታውቋል።

ተያያዥ ርዕሶች