በባልደረቦቻቸው ታግዘው ያመለጡት ተጠርጣሪ ፖሊሶች

Image copyright CORBIS NEWS

ኢትዮጵያ

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአፍሪካ ዋነኛ መግቢያ በርነትን ሚና ከዱባይ አየር መንገድ ተረከበ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች ጋር ድርሻ ወስዶ መስራቱ ደግሞ የተጓዦችን ቁጥር 40 በመቶ አሳድጎታል።

ኬንያ

ኬንያ ውስጥ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ ሲካሄድባቸው የነበሩ ሁለት ፖሊሶች በስራ ባልደረቦቻቸው አጋዥነት አመለጡ።

ፖሊሶቹ 100 ሺህ የኬንያ ሺልንግ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆን፤ ባልደረቦቻቸው ወደ ሰማይ በመተኮስ አስመልጠዋቸዋል።

"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ

አሜሪካዊው ወንጀለኛ '90 ሰዎች መግደሉን አመነ'

ጋምቢያ

ለብዙ ዓመታት ጠፍቶ የቀረው ጋምቢያዊ ጋዜጠኛ ኤብሪማ ማኔህ ቤተሰቦች 100 ሺ ዶላር ካሳ ተሰጣቸው።

ጋዜጠኛው የጠፋው በቀድሞው ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ጊዜ ሲሆን፤ ሳይገደል እንዳልቀረ ብዙዎች ገምተዋል።

ናይጄሪያ

ናይጄሪያ በቅርቡ ከሚካሄደው ምርጫ በፊት ሃሰተኛ ዜናዎችን የሚቆጣጠር ክሮስ ቼክ የተባለ ድረ ገጽ ይፋ አደረገች።

ድረ ገጹ ጋዜጠኞችና ማንኛውም ሰው በተለይ ደግሞ ከማህበራዊ ሚዲያዎች ትክክለኛ መረጃዎችን እንዲያገኙ ይረዳል ተብሏል።

አሜሪካ

በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ የሚገኝ አንድ አሜሪካዊ ከተከሰሰበት ወንጀል በተጨማሪ ከ1970 እስከ 2005 ድረስ 90 ሴቶችን መግደሉን አመነ።

የ78 ዓመቱ ሰው በአሜሪካ ታሪክ ትልቅ ከሚባሉት ገዳዮች መካከል አንዱ ሆኗል ተብሏል።

'ምን ለብሳ ነበር?'

ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች

ህንድ

ህንድ ውስጥ አንዲት እናት የገበያ አዳራሽ ውስጥ ጡት ማጥባት አትችይም መባሏ ቁጣን ቀስቅሷል።

የገበያ አዳራሹ ኃላፊዎች ለጡት ማጥቢያ የሚሆን ቦታ የለንም ስለዚህ ቤትሽ ሄደሽ ማጥባት ትችያለሽ ነበር ያሏት።

ፊሊፒንስ

ፊሊፒንስ ውስጥ የሚገኙ ሶስት ፖሊሶች የ17 ዓመት ታዳጊን በመግደል ወንጀል ተከሰው እያንዳንዳቸው 40 ዓመት ተፈረደባቸው።

ፖሊሶቹ ራሳችንን ለመከላከል ነው የገደልነው ቢሉም፤ ፍርድ ቤቱ ግን ያለ አግባብ ኃይል ተጠቅማችኋል ብሏል።

ዓለም አቀፍ

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ተቋም ዩኔስኮ የሬጌ የሙዚቃ ስልትን የዓለም ባህላዊ ሃብት ብሎ መዘገበው።

በአውሮፓውያኑ በ1960ዎቹ ጃማይካ ውስጥ የተጀመረው የሙዚቃ ስልት፤ የዓለምን ቀልብ እንደገዛ እስካሁን ቆይቷል።

***

ያለፉት አራት ዓመታት በአለማችን ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገቡባቸው እንደነበሩ የዓለማቀፉ የአየር ትንበያ ድርጅት ገለጸ።

ቁጥሩ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ በአውሮፓውያኑ 2021 ዓለማችን ከ3 እስከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ ጭማሪ ሙቀት ታስተናግዳለች ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች