የኒካራጓው ቄስ በኑዛዜ ሥነ ሥርዓት ላይ የአሲድ ጥቃት ተፈፀመባቸው

ጥቃቱ የተፈፀመው በማናጓ ሜትሮፖሊታን ካቴድራል ቤተክርስቲያን ነው Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ጥቃቱ የተፈፀመው በማናጓ ሜትሮፖሊታን ካቴድራል ቤተክርስቲያን ነው

በመካከላኛው አሜሪካ የኒካራጓ ዋና መዲና በሆነችው ማናጓ የ59 ዓመቱ ቄስ በተፈፀመባቸው የአሲድ ጥቃት ክፉኛ እንደተጎዱ ተዘገበ። ቄስ ሚጌል ጉቫራ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በሜትሮፖሊታን ካቴድራል ውስጥ አማኞች የሰሩትን ኃጢያት ኑዛዜ ተቀብለው ሲጨርሱ ነበር።

የጀርመን ቄሶች ቅሌት ሲጋለጥ

የኦሮሞ ፓርቲዎች የጋራ ፎረም ለማቋቋም ከስምምነት ላይ ደረሱ

በአሲዱ ፊታቸው፣ ክናዳቸው ላይና ትከሻቸው አካባቢ ቃጠሎ ያጋጠማቸው ሲሆን የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።

በወቅቱ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የነበሩ አምላኪዎች ፖሊስ በአፋጣኝ እስከሚደርስ አሲዱን በመወርወር የደፋችባቸውን ሴት በቁጥጥር ስር አውለዋታል።

ፖሊስ እንዳለው ጥቃት አድራሿ ጥቃቱን ለማድረስ ምን እንዳነሳሳት እያጣራ ሲሆን፤ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ግን ጥቃት አድራሿ በማህፀን ውስጥ ያለ ሽል የተሳለበት ካናቴራ ለብሳ የነበረች የሩሲያ ዜጋ ናት።

"ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ

ቤተክርስቲያኑ ፀረ መንግሥት እንቅስቃሴዎች መደረግ ከጀመሩበት ካለፈው ሚያዚያ ጀምሮ እንቅስቃሴውን በመግታት ረገድ የሚጫወተው ሚና እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ተብሎ በመንግሥት ወቀሳ ሲደርስበት ቆይቷል። ጥቃቱም ሆን ተብሎ የተፈፀመ እንደሆነ ፖሊስ አስረድቷል።

በተቃዋሚዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፤ በዚህም ወቅት ቤተክርስቲያኗ ለመንግሥት ተቃዋሚዎች መሸሸጊያ ሆናለች በሚል በመንግሥት ደጋፊዎች ተከቦ ነበር።

ባለፈው የፈረንጆቹ ሐምሌ ወርም የኒካራጓ ቀሳውስት መንግሥትን ለመገልበጥ ለሚታገሉ ተቃዋሚዎች መጠጊያ ሆነዋል ሲሉ ፕሬዚደንት ኦርቴጋ ተችተዋል።

"ቀሳውስቱ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ አይተኙም" ሲሉም ፕሬዚደንቱ አክለው ተናግረዋል።