ዓይነ ስውሯ ሰዎችን ለመርዳት ስትል በርካታ ፈጠራዎችን አበርክታለች

የፎቶው ባለመብት, IBM
ቺዬኮ አሳካዋ በተደራሽነት ዙሪያ ለሠራችው ጥናትና ላደረገችው አስተዋጽዖ የጃፓን የክብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆናለች
በ14 ዓመቷ የዋና ገንዳ ውስጥ ባጋጠማት አደጋ ነበር ቺዬኮ አሳካዋ ዓይኖቿ የታወሩት። ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ደግሞ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችንና 'አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ' በመፍጠር ማየት የተሳናቸውን ሰዎች ሕይወት ለማሻሻል እየጣረች ነው።
የጃፓናዊቷ ዶ/ር ቺዬኮ "ስጀመር ምንም ዓይነት አጋዥ ቴክኖሎጂዎች አልነበሩም" ትላለች።
"ብቻዬን ምንም ዓይነት መረጃ ማንበብ አልችልም ነበር። በተጨማሪም ብቻዬን መንቀሳቀስ አልችልም ነበር"
እነዚህ ተግዳሮቶች ነበሩ አሁን እየሰራች ወዳለው ነገር የመሯት። ለዓይነ ስውራን የተዘጋጀ የኮምፕዩተር ሳይንስ ትምህርቶችን ተከታትላ እንዳበቃች ወዲያው አይቢኤም በተሰኘው ድርጅት ውስጥ ሥራ አግኘች። ዶክትሬቷን እያጠናች ሥራዋን የጀመረችውም የመሥሪያ ቤቷን ለአካል ጉዳተኞች ምቹነት በማጥናት ነበር።
የመጀመሪያዎቹ የብሬል ዲጂታል ፈጠራዎችና ከኢንተርኔት የድምጽ ፍለጋ በስተጀርባ ዶ/ር ቺዬኮ ትገኝበታለች። እነዚህ የፍለጋ ዘዴዎች በአሁኑ ዘመን በጣም የተስፋፉ ቢሆኑም እንኳን የዛሬ 20 ዓመታት በፊት ግን ለዓይነ ስውር ጃፓናውያን ከዚያ ቀደም የማያገኟቸውን መረጃዎች እንዲያገኙ ዕድል ፈጥራላቸዋለች።
አሁን ከሌሎች ቴክኖሎጂስቶች ጋር በመሆን የተሌኣዩ 'አርቲፊሻል ኢንቴሌገንሶችን' በመጠቀም የተለያዩ መሣሪያዎችን ሊሠሩ ነው።
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ብሬል እና በድምጽ የሚታዘዙ ቱክኖሎጂዎች ለዓይነ ስውራን ዋና መሣሪያዎች ናቸው
'ማይክሮ ማፒንግ'
ለምሳሌ ዶ/ር ቺዬኮ 'ናቭኮግ' የተሰኘውን በአስቸጋሪ ቦታዎች ላይ ለመንቀሳቀስ የሚያግዝ በድምጽ የሚታገዝ የዘመናዊ ስልክ መተግበሪያ ለዓይነ ስውራን ፈጥራለች።
ይህም መለስተኛ ኃይል ያላቸው የብሉቱዝ የምልክት ምንጮች የቤት ውስጥ ካርታ ለመዘርጋት በየ10 ሜ.ር ርቀት ላይ ይቀመጣሉ። የቦታውንም ዱካ ማውጣት ናሙና መረጃዎች ይሰበሰባሉ።
"ያለንበትን ቦታ ለማወቅ የናሙናውን ዱካ ካለንበት ጋር በማነፃፀር ለማወቅ ይረዳናል" ትላለች።
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የመንቀሳቀሻ መተግበሪያዎች ዓይነ ስውራን በትር መጠቀም ያቆማሉ ማለት ነው?
ብዙ መረጃዎችን መሰብሰባችን በጉግል ማፕስ ላይ ካሉ ካርታዎች በበለጠ መረጃ ሊሰጥ ቢችልም ይህ በቤት ውስት ግን ብዙም ጠቃሚ አይደለም ምክንያቱም ለዓይነ ስውራን የሚያስፈልገውን መረጃ አይሰጥም።
አምስት የኖቤል ተሸላሚዎችን ባበቃው አይቢኤም ውስጥ ተጋባዥ አጥኚ የሆነችው ዶ/ር ቺዬኮ "ጠቃሚ ቢሆንም በተገቢ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አይረዳንም" ትላለች።
'ናቨኮግ' ገና ጅማሬው ላይ ቢሆንም በአሜሪካ የተለያዩ ቦታዎች ላይና በቶክዮ ደግሞ በአንድ ቦታ ላይ አለ። መተግበሪያው ለሕዝብ ግልጋሎት ሊቀርብ ትንሽ እንደቀረው አይቢኤም ገልጿል።
"ቁጥጥር ሰጥቶኛል"
የፒትስበርግ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የ70 ዓመቷ ክሪስቲን ሃሲንገርና የ65 ዓመት ባለቤታቸው ዳግላስ ሃሲንገር ለዓይነ ስውራን ተብሎ በተዘጋጀ ኮንፍረንስ ላይ ተገኝተው 'ናቭኮግ'ን ሞክረውታል።
ለመንግሥት ለ40 ዓመታት አገልግለው ጡረታ የወጡት ክሪስቲን "ሁኔታዬ በእራሴ ቁጥጥር ውስጥ እንደነበር ነው የተሰማኝ" ይላሉ።
ሌሎች መተግበሪያዎችን ለመንቀሳቀስ እንደሚጠቀሙና 'ናቭኮግ'ን ሲጠቀሙ በትር ይዘው ቢሆንም በማያውቁት ቦታ ላይ ለመንቀሳቀስ ይበለጥ ነፃነት እንደሰጣቸው ይናገራሉ።
ባለቤታቸው ዳግለስም በቤት ውስጥ ስንንቀሳቀስ "የምንገምተውን" ነው መተግበሪያው የቀነሰለን ይላሉ።
"በእራሴ መንቀሳቀስ መቻሌ እፎይታ እንዲሰማን አድርጓል።"
የፎቶው ባለመብት, IBM
ዶ/ር ቺዬኮ ቀለማት ትውስታዋ ናቭኮግን ለመሥራትና ሌሎች ሥራዎቿም ላእ እንደጠቀማት ትናገራለች
ቀለል ያለ ሻንጣ ሮቦት
የዶ/ር ቺዬኮ ቀጣዩ ሥራ የ'አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ' ሻንጣ ነው ይህም ለእንቅስቃሴ የሚረዳ ሮቦት ነው።
ዓይነ ስውር የሆነን ሰው እንደ ኤርፖርት ዓይነት ለእንቅስቃሴ የሚከብድ ቦታ ላይ አቅጣጫ፣ የበረራና የበር ለውጥ መረጃዎችን በመስጠት ይመራል።
ሻንጣው በውስጡ ሞተር ያለው ሲሆን በእራሱ መንቀሳቀስና ዕቃዎችን ለመለየት የሚያስችለው ካሜራና 'ሊዳር' በተሰኘ ቴክኖሎጂ ብርሃንና ርቀትን እንዲለካ ታስቦ የተሠራ ነው።
ደረጃ ሲኖር ሻንጣው በተጠቃሚው እንዲነሳ ያሳውቃል።
"አብረን ብንሠራ ሮቦቱ አነስ፣ ቀለልና ርካሽ መሆን ይችላል" ትላለች ዶ/ር ቺዬኮ።
ለሙከራ የተሠራው ሮቦት "በጣም ከባድ" ነው ትላለች። አይቢኤም ቀጣዩን ሮቦት ቀላል የማድረግና ቢያንስ የእጅ ኮምፕዩተር እንዲችል ተደርጎ ተሠርቶ በሁለት ዓመት ውስጥ ለማድረስ ዕቅድ እንዳለው ተናገሯል።
"ብቻዬን መጓዝ በጣም ነው የምፈልገው። ለዚያም ነው ምንም ያህል ጊዜ ቢፈጅም በአርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ የሮቦት ሻንጣ ላይ ማተኮር የምፈልገው" ትላለች።
በአይቢኤም ለሙከራ የተሠራውን ሻንጣ አሳይተውኛል ግን ለሕዝብ ለማቅረብ ዝግጁ ባለመሆኑ ምስሉን እንኳን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደሉም።
የፎቶው ባለመብት, Microsoft
የማይክሮሶፍት ሠራተኛው ሳቂብ ሸይክ በድምጽ ትእዛዝ የሚቀበለውን ዘመናዊ ስልክ አሠራር ሲያሳይ
አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስን ለማህበረሰቡ ጥቅም
ምንም ፍላጎት ቢኖረው አይቢኤም ከማይክሮሶፍትና ከጉግል አንፃር በጣም ወደኋላ ቀርቷል።
ማይክሮሶፍት 115 ሚሊዮን ፓውንድ 'አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ ፎር ጉድ' ለተሰኘው ፕሮግራም የመደበ ሲሆን 25 ሚሊዮን ፓውንድ ደግሞ ለ'አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ' ለተደራሽነት መድቧል። ለምሳሌ 'ሲዪንግ አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ' የተሰኘው በድምጽ ትዕዛዝ የሚቀበል ካሜራ ሲሆን በዋናነት የሚያተኩሩበት ሥራ ነው።
በዚህ ዓመት መጨረሻ ደግሞ ጉግል ዓይነ ስውራንን ለመምራት ታስቦ የተሠራውን ሉካውት የተሰኘውን መተግበሪያ ለሕዝብ ያቀርባል።
ለሲሲኤስ ኢንሳይት የአርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ ዋና ኃላፊ የሆነው ኒክ ማክዋየር "አካል ጉዳተኞች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተረስተዋል" ይላል።
በዚህ ዓመት ውስጥ ግን ብዙ ድርጅቶች ለአርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ ገንዘብ እየመደቡ በመሆኑ ነገሮች እየተቀየር እንደሆነ ይናገራል።
ከሌሎች የተለያዩ ድርጅቶችም ብዙ የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚመጣ አልጠራጠርም ብሏል።
በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት
በ 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ዘርፍ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ ባለሙያዎች አንዷ ነች። አሁን ካሊፎርንያ ውስጥ የምትኖረው ትምኒት ጉግል ውስጥ ሪሰርች ሳይንቲስት ናት።