ሞሃመድ ሳላህ፣ ሉዊዝና አሊሰን ምርጥ ቡድኑ ውስጥ ገብተዋል

በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ማንቸስተር ሲቲ በቼልሲ ሲሸነፍ፤ ሊቨርፑል ቦርንማውዝን 4 ለምንም በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ተረክቧል።

በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት የሳውዝሃምፕተኖች አዲሱ አሰልጣኝ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ሽንፈትን ሲቀምሱ፤ በርንሌዮች ደግሞ ከመስከረም ወር ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ድል ቀንቷቸዋል።

ነገር ግን የትኞቹ ተጫዋቾች ድንቅ ብቃታቸውን በማሳየት በጋሬት ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ መካተት ቻሉ?

ሳዑዲ የካሾግጂን ተጠርጣሪ ገዳዮች አሳልፌ አልሰጥም አለች

በሱዳን ሄሊኮፕተር ተከስክሶ አራት ባለሥልጣናትን ገደለ

Image copyright BBC Sport

ግብ ጠባቂ - አሊሰን (ሊቨርፑል)

Image copyright Rex Features

ሊቨርፑሎች ከሊጉ አናት ላይ የተቀመጡት ያለምክንያት አይደለም። እስካሁን የተቆጠረባቸው የግብ ብዛት ስድስት ብቻ ነው። አሰልጣኙ በወጣቱ ግብ ጠባቂ ላይ እምነታቸውን እየጣሉ ይመስላል።

ቦርንማውዝን 4 ለምንም ሲያሸንፉ ግቡን ሳያስደፍር መውጣት ችሏል።

ተከላካዮች - ዲዬጎ ዳሎ (ዩናይትድ)ዴቪድ ሊዊዝ (ቼልሲ)ያንግ (ዩናይትድ)

Image copyright Rex Features

ዲዬጎ ዳሎ : ይህ ወጣት የመስመር ተከላካይ ወደፊት በመውጣት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ማሻማት የቀለለው ይመስላል። ለማን እንደሚያቀብልና የቱጋ ኳሱን ማስቀመጥ እንዳለበት ያውቃል።

ምንም እንኳን 19 ዓመቱ ቢሆንም፤ በቅዳሜው ጨዋታ ግን አስገራሚ ብቃቱን ማሳየት ችሏል። ዩናይትዶች ከፉልሃም ሲጫወቱ አምስት የተሳኩ ኳሶችን ሲያሻሙ አራቱ ከዳሎ የተገኙ ነበሩ።

ዴቪድ ሉዊዝ : ሲቲዎች ያለፊት መስመር አጥቂ መግባታቸው ለቼልሲዎች ተመችቶ ነበር። በተለይ ደግሞ ሉዊዝ፤ ራሂም ስተርሊንግን መቆጣጠር ቀላል ሥራ ሆኖለታል።

በቼልሲ ግብ ክልል ውስጥ በሲቲ ተጫዋቾች የተላኩ ሰባት ኳሶችን በቀላሉ ከግብ ክልል ማራቅ ችሎ ነበር።

በዓይነ ስውሯ የተሠራው የሚያይ ሻንጣ

አፍሪካ የተሰጣትን ጨለምተኛ እይታ ለመቀየር ያለመው አዲስ ፎቶ ፌስት

አሽሊ ያንግ : ከአስር ወራት በላይ ጥበቃ በኋላ ፉልሃም ላይ ያስቆጠራት ግብ አስገራሚ ነበረች። በአዲስ መልክ የተነሳሳው ያንግ እግር ኳስ በማቆሚያ እድሜው ውስጥ ሆኖ እንኳን የቡድኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ ተጫዋች ሆኗል።

አማካዮች- ዴል አሊ (ቶተንሃም)ንጎሎ ካንቴ (ቼልሲ)ሉካስ ቶሪዬራ (አርሰናል) ፊሊፔ አንደርሰን (ዌስትሃም)

Image copyright Rex Features

ዴል አሊ: ቶተንሃሞች የፊት መስመር አጥቂያቸው ሃሪ ኬንና አማካዩ ክርስቲያን ኤሪክሰን በሌሉበት ቡድን ውስጥ ዴል አሊ ቡድኑን በተገቢው መልኩ ሲያገለግል ነበር። እንዲያውም በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ወደፊት የቡድኑ አምበል የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም።

በሁሉም ውድሮች 50ኛ ግቡንም አስቆጥሯል።

ንጎሎ ካንቴ : ማንቸስተር ሲቲዎች የዳቪድ ሲልቫን አይነት የተሟላ አማካይ ቢይዙም፤ ወደግብ ብዙ መድረስ ግን አልቻሉም ነበር። በተቃራኒው ቼልሲዎች በሲቲ የግብ ክልል ውስጥ ያገኙትን አጋጣሚ በካንቴ አማካኝነት ወደ ግብነት ቀይረውታል።

ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን?

ሉካስ ቶሪዬራ : ይህ አዲስ ፈራሚ በኡናይ ኤምሪ ከተገዙ አዳዲስ ተጫዋቾች በፍጥነት የተላመደና ልዩነት መፍጠር የቻለ ነው። በባለፈው ሳምንት የቶተንሃም ጨዋታም ልዩነት ሆኖ ያመሸው እሱ ነበር።

በቅዳሜው የሃደርስፊልድ ጨዋታም ይህንኑ መድገም ችሏል።

ፊሊፔ አንደርሰን : እጅግ የተካነ አማካይ ከመሆኑ በተጨማሪ ብራዚላዊው አንደርሰን ግብ ማስቆጠርም ጀምሯል። እስካሁን በስድስት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

አጥቂዎች - ሞሃመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)ማርኮስ ራሸፎርድ (ዩናይትድ)ሶን ሂዩንግ ሚን (ቶተንሃም)

Image copyright Rex Features

ሞሃመድ ሳለህ: ግብጻዊው አጥቂ ወደ አስፈሪው አቋሙ የተመለሰ ይመስላል። ቦርንማውዝ ላይ ሦስት ግቦች አስቆጥሮ ሃትሪክ መስራት ችሏል።

ሳላህ በዚህ ብቃቱ መቀጠል ከቻለ ቡድኑ ሊቨርፑል ያለምንም ጥርጥር ዋንጫውን የማንሳት አቅም አለው።

ማርከስ ራሽፎርድ : ባለፈው ሳምንት ዩናይትዶች ከሳውዝሃምፕተን 2 ለ2 አቻ ሲለያዩ ለሁለቱም ግቦች አመቻችቶ ያቀበለው ራሽፎርድ ነበር።

በዚህ ሳምንትም ሁዋን ማታ ላስቆጠራት ግብ ኳሱን አመቻችቶ ከማቀበሉ በተጨማሪ አንድ ግብም በስሙ ማስመዝገብ ችሏል።

ሶን ሂዩን ሚን : ኮሪያዊው የፊት መስመር ተጫዋች ከሌስተር በነበራቸው ጨዋታ የመጀመሪያዋን ግብ ሲያስቆጥር ሁለተኛዋን ደግሞ ለዴል አሊ አመቻችቶ አቀብሏል።