በሱዳን ሄሊኮፕተር ተከስክሶ አራት ባለሥልጣናትን ገደለ

ካርታ

በምስራቃዊ ሱዳን ሄሊኮፕተር ተከስክሶ የከተማዋን አስተዳዳሪና ሌሎች አራት ባለሥልጣናት እንደተገደሉ ተዘግቧል።

ሄሊኮፕተሩ አልቃድሪፍ የሚባል ቦታ ላይ ለማረፍ ትግል ቢያደርግም አንድ የመገናኛ ግምብ መትታ በእሳት መያያዟን ኤኤፍፒ ያናገራቸው የአይን እማኞች ገልፀዋል።

እስካሁንም ሄሊኮፕተሩ የተከሰከሰበትን ምክንያት ከሱዳን ባለሥልጣናት በኩል የተገለፀ የለም።

የሀገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው በአደጋው የቆሰሉ ሰዎች ሆስፒታል እንደተወሰዱ ገልፆ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች

አፍሪካ የተሰጣትን ጨለምተኛ እይታ ለመቀየር ያለመው አዲስ ፎቶ ፌስት

በርካቶችን ግራ ያጋባው ፎቶ

ከሟቾቹም መካከል የአልቃድሪፍ አስተዳዳሪ የሆኑት ሚርጋኒ ሳልህ፣ የካቢኔቱ ኃላፊ፣ የከተማው የፖሊስ ኃላፊና የግብርና ሚኒስትሩ እንደሚገኙበት ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጿል።

የሱዳን የወታደራዊ የጦር አውሮፕላኖች ብዙዎቹ ከቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት የተገዙ ናቸው።

በጥቅምት ወርም በመዲናዋ ካርቱም በሚገኘው አየር መንገድ ሁለት አውሮፕላኖች ተጋጭተው ስምንት ሰዎች ተጎድተዋል።

በተጨማሪም በመስከረም ወር በመዲናዋ ካርቱም በምትገኘው ኦምዱርማን ከተማ የጦር ጀት ተከስክሶ የሁለት ፓይለቶች ህይወት ጠፍቷል።

ተያያዥ ርዕሶች