ማንቸስተርና ሊቨርፑል ተፋጠዋል

ማንቸስተር ዩናይትዶች ወደ አንፊልድ ተጉዘው ሊቨርፑልን በገጠሙባቸው ሁለት የመጨረሻ ጨዋታዎች አስፈላጊውን ውጤት ይዘው መመለስ አልቻሉም። እሁድ ዕለት በሚያደርጉት ፍልሚያ የተለየ ውጤት ይዘው መመለስ ይችሉ ይሆን?

በዚህ ጨዋታ የማንቸስተሩ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ የተለየ አጨዋወት ይዘው የሚመጡ አይመስለኝም ይላል የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን።

ሊቨርፑሎች ይህ ጨዋታ ስለሚመቻቸው ኳስ ይዘው በመጫወት ግብ ለማስቆጠር እንደሚጥሩ አስባለው ብሏል።

ከጦርነት ይልቅ ለብዙዎች ሞት ምክንያት የሆኑት አይጦች

ልብ የረሳው አውሮፕላን

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ማንቸስተር ሲቲ ከኤቨርተን

ሲቲዎች ረቡዕ ዕለት በሻምፒዮንስ ሊጉ ሆፈኒየምን በማሸነፋቸው ጨዋታ ምክንያት ሊዳከሙ ይችላሉ። ነገር ግን ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ አይከብዳቸውም ይላል ላውሮ።

ኤቨርተኖች ባለፈው ሳምንት ከዋትፎርድ አቻ መለያታቸው ትንሽ ጫና የሚያሳድርባቸው ይመስለኛል። ነገር ግን ሁሌም ቢሆን ኤቨርተኖች ለትልቅ ቡድን በቀላሉ እጅ አይሰጡም።

ሲቲዎች የደብራይነ እና አጉዌሮ መጎዳት ቢያሳስባቸውም፤ የስተርሊንግና ሳኔ ጥሩ አቋም ላይ መገኘት ደግሞ ጥሩ መነቃቃትን ይፈጥርላቸዋል ብዬ አስባለው ሲል ጨዋታውን ሲቲ እንደሚያሸንረፍ ገምቷል ላውሮ።

የላውሮ ግምት: 2-0

ክሪስታል ፓላስ ከሌስተር

ፓላሶች በሜዳቸው እስካሁን አሳማኝ የሚባል እንቅስቃሴ ማድረግ ያልቻሉ ሲሆን፤ በደረጃ ሰንጠረዡ 16ኛ ላይ መገኘታቸው ደግሞ ይበልጥ ውጥረት ውስጥ ከቷቸዋል።

ሌስተሮች በበኩላቸው ባለፈው ሳምንት በቶተንሃም መሸነፋቸው ነገሮችን ከባድ አድርጎባቸዋል።

የላውሮ ግምት: 1-1

በበረራ ላይ ሴት የተነኮሰው ህንዳዊ ዘብጥያ ወረደ

በጥሞና ላይ የነበሩት መነኩሴ በአቦሸማኔ ተገደሉ

ሃደርስፊልድ ከኒውካስል

ባለፈው ሳምንት ኒውካስሎች በዎልቭስ መሸነፋቸው ዕድለቢስነት ነው ይላል ላውሮ። ቡድኑ ብዙ ግብ የሚያስቆጥር አይነት ባይሆንም፤ የሶሎሞን ሮንዶን አይነት አጥቂ ይዞ የግብ ዕድሎችን መፍጠር አለመቻል አሳሳቢ ነው።

ሃደርስፊልድ ደግሞ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠረባቸው ግብ በአርሰናል ተሸንፈው ነበር።

የላውሮ ግምት: 0-2

Image copyright BBC Sport

ቶተንሃም ከበርንሌይ

ቶተንሃሞች ጥሩ የሚባል ሳምንት ነበር ያሳለፉት። በፕሪምየር ሊጉ ሌስተርን አሸንፈው በሻምፒዮንስ ሊጉ ደግሞ ከባርሴሎና አቻ ተለያይተው ከምድባቸው በሁለተኝነት ማለፋቸውን አረጋግተዋል።

ለቶተንሃም ቀላል ጨዋታ እንደሚሆን አስባለው ሲል የማሸነፍ ግምቱን ለቶተንሃም ሰጥቷል ላውሮ።

የላውሮ ግምት: 2-0

ዋትፎርድ ከካርዲፍ

ካርዲፎች በሜዳቸው ያደረጓቸውን አራት ጨዋታች ያሸነፉ ሲሆን፤ ካለፉት ሰባት ጨዋታዎች ግን መሰብሰብ የቻሉት አንድ ነጥብ ብቻ ነው።

ዋትፎርድ ደግሞ እስካሁን በስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

የላውሮ ግምት: 2-0

ዎልቭስ ከቦርንማውዝ

ቦርንማውዞች ካሉም ዊልሰን ከተጎዳ በኋላ የማጥቃት አጨዋወታቸው ቀንሷል። ባለፈው ሳምንት ከሊቨርፑል ሲጫወቱም ይህንን ማስተዋል ችዬ ነበር ይላል ላውሮ።

ዎልቭሶች ኒውካስል ላይ ባለፈው ሳምንት የተቀዳጁት ድል መነሳሳት ፈጥሮላቸዋል።

የላውረ ግምት: 2-1

ፉልሃም ከዌስትሃም

ፉልሃሞች እጅግ የተዳከመ የተከላካይ መስመር ነው ያላቸው። ለዌስትሃሞች ግን በቀላሉ እጃቸውን ይሰጣሉ ብዬ አላስብም ባይ ነው ላውሮ።

የዌስትሃም ተጫዋቾች አሁንም የድሮ የታጋይነት መንፈሳቸው የተመለሰ አይመስልም።

የላውሮ ግመት: 2-1

እሁድ

Image copyright BBC Sport

ብራይተን ከቼልሲ

ብራይተኖች በሜዳቸው ካደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች የተሸነፉት በአንዱ ብቻ ሲሆን፤ እሄኛው ግን እንደሌሎቹ የሚሆን አይመስልም።

ባለፈው ሳምነት ሲቲዎችን 2 ለምን ካሸነፉ በኋላ በምርጥ መነሳሳት ላይ የሚገኙት ቼልሲዎች እንደሚያሸንፉ አልጠራጠርም ብሏል።

የላውሮ ግምት: 0-2

የሜቴክ የህዳሴ ግድብ ውል ለፈረንሳይና ጀርመን ኩባንያዎች ሊሰጥ ነው

Image copyright BBC Sport

ሳውዝሃምፕተን ከአርሰናል

አዲሱ የሳውዝሃምፕተን አሰልጣኝ ራልፍ ሃሴኑት ባለፈው ሳምንት በመጀመሪያ ጨዋታቸው በካርዲፍ ተሸንፈው ነበር። ሁለተኛ ጨዋታቸውም እጅግ ከባድ ፈተና እንደሚሆንባቸው ይታሰባል።

በፕሪምየር ሊጉም በአውሮፓ ሊግም ድል የቀናቸው አርሰናሎች ከሳውዝሃምፕተን ከባድ ፍልሚያ ሊገጥማቸው ይችላል።

የላውሮ ግምት: 0-1

Image copyright BBC Sport

ሊቨርፑል ከማንቸስተር ዩናይትድ

ሊቨርፑሎች አሁን እየተጫወቱት ባለው አይነት ጨዋታና ተቀናቃኞችን እያሸነፉበት ባለው አካሄድ በዚህኛውም እንደሚያሸንፉ ብዙዎች ገምተዋል። ነገር ግን መርሳት የሌለብን ለመጨረሻ ጊዜ በአንፊልድ ከማንቸስተር ሲገናኙ የተለመደ ጨዋታቸውን ማሳየት አልቻሉም ነበር።

ማንቸስተሮች ደግሞ ከተሻለ ቡድን ጋር ሲጫወቱ ጥሩ ውጤት የማስመዝገብ ልማድ አላቸው። የቼልሲውንና ጁቬንቱሱን ውጤት መጥቀስ ይቻላል።

በእሁዱ ጨዋታ ሞሪንሆ የሊቨርፑልን ጨዋታ ለማበላሸትና ተጫዋቾቹን ጫና ውስጥ ለማስገባት ተዘጋጅቶ እንደሚጣ አስባለው ብሏል ላውሮ።

የላውሮ ግምት: 1-1