ሞ ሳላሕ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች በመሆን ለ2ኛ ጊዜ ተመረጠ

ሞ ሳላህ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ኾኖ ተመረጠ

የግብጽ ብሔራዊ ቡድን እና የሊቨርፑል አጥቂ የሆነው ሞሐመድ ሳላህ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የቢቢሲ የዓመቱ የአፍሪካ ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል።

የ26 ዓመቱ አጥቂ ሜዲ ቤናቲያ፣ ካሊዱ ኩሊባሊ፣ ሳዲዮ ማኔ እና ቶማስ ፓርቴይን አሸንፎ ነው ሽልማቱን ያገኘው።

"ታላቅ ስሜት ነው፤በሚቀጥለው ዓመትም ለማሸነፍ እፈልጋለሁ። " ሲል ሳላህ ሐሳቡን ለቢቢሲ ገልጿል።

የዘንድሮ የቢቢሲ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ዕጩዎች

የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋቾች ባለፈው ዓመት ለሊቨርፑል 52 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 44 ጎሎችን ከማስቆጠርም ባለፈ ቡድኑ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ እንዲደርስ አግዟል።

"በእያንዳንዱን ጊዜ ጎሎችን በማስቆጠር ቡድኑ ነጥብ እንዲያገኝ በማድረግ ቡድኑ በሊጉ አናት እንዲቀመጥ እንዳገዝኩ ይሰማኛል. . . ይህ ደግሞ ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት ይሰጣል።" ይላል ሳላህ።

ሩሲያው የዓለም ዋንጫ ሁለት ጎሎችን ለግብጽ ብሔራዊ ቡድን አስቆጥሯል።

ቢቢሲ ዘንድሮ በሽልማቱ ታሪክ ክብረወሰን የሆነ ከ650,000 በላይ ድምፆችን ተቀብሏል።

ሳላህ ከናይጄሪያዊው ጄይ-ጄይ ኦኮቻ ቀጥሎ በተከታታይ ዓመት ሽልማቱን ያሸነፈ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።

የቀድሞው የቼልሲተጫዋች በቨውሮፓዊያኑ 2017 ከሮማ ወደ ሊቨርፑል ያቀናው።

በሮም ቆይታው 15 ጎሎችን አስቆጥሮ 11 ደግሞ ለጎል አመቻችቶ አቀብሏል። በዚህም ቡድኑ ከሰባት ዓመት በኋላ በሴሪአው ሁለተኛው ሆኖ አጠናቋል።

ሳላህ የሊቨርፑል ሕይወቱ በድንቅ ሁኔታ ነው የጀመረው። በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው 24 ጨዋታዎች19 ግቦችን አስቆጥሯል።

ሉዊስ ሱዋሬዝ (2013 -14)፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ (2007-08) እና አለን ሺረር (1979-1996) በአንድ ውድድር ዓመት ካስቆጠሯቸው 38 ጎሎች ጋር እኩል በማስቆጠር ክብረወሰኑን ተጋርቷል።

ሞሐመድ ባራክት (2005) እና ሞሃመድ አቡታሪካ (2008) ሽልማቶችን ያገኙ ሌሎች ግብፃውያን ናቸው።