ከወንበርና ከሲጋራ የቱ ይገድላል?

ወንበር ላይ ተቀምጦ በቄንጥ በማጨስ ላይ ያለ ሰው Image copyright Getty Images

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለ ወንበር ብዙም የለም። የሆሜር ስንኞችም ላይ አልተጻፈም። በሼክስፒር ሐምሌትም ላይ አልተገኘም።

ልክ 19ኛው ክፍለ ዘመን ሲጋመስ ወንበሮች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። ለምሳሌ በቻርለስ ዲከንስ ሥራዎች።

ስለ ገጸ ባሕሪ አይደለም የምናወራው፤ መቀመጫ፣ የወገብ ማሳረፊያ ስለሆነው ወንበር ነው የምናወራው።

ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?

ሰው ተቀምጦ በሽታ መሸመት ጀምሯል እየተባለ ነው። የትም ሳይሄድ። ወንበሩ ላይ ሳለ።

ጥናቶች መቀመጥ እንደማጨስ ያለ ነው ይላሉ። ልዩነታቸው አንዱ ሳንባን፣ ሌላው ነርቭን ከጥቅም ውጭ ያደርጋሉ።

የወንበር አጭር የሕይወት ታሪክ

እኛው ፈጥረናቸው እኛኑ የሚፈጁን መሣሪያዎች ብዙ ናቸው። አንዱ ኒክሊየር ነው። አንዱ ደግሞ ወንበር ነው።

በጥንታዊ ታሪክ ወንበር ብዙም አልነበረም። ምናልባት ነገሥታት አካባቢ...።

ዛሬ ዛሬ ግን ወንበር የሌለበት ቦታ የለም። ጥቂቱን ከዚህ እንደሚከተለው እንዘረዝራለን።

ሻይ ቤት፣ ምግብ ቤት፣ ቡና ቤት፣ መኪና ውስጥ፣ ቢሮ ውስጥ፣ ሲኒማ ቤት፣ ሆስፒታል፣ ጸሎት ቤት፣ ትምህርት ቤት፣ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የገዛ መኝታ ቤታችን ሳይቀር ወንበሮች አሉ። ወንበር ጨረሰን እኮ ጎበዝ!

አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች

ሰው ሥልጣን ይወዳል ለማለት "ሰው ወንበር ይወዳል" እንላለን። ያለ ምክንያት አይደለም።

እንደው በዓለማችን ላይ ስንት ወንበሮች ይኖራሉ? ብለን ብናስብ በግምት "አንድ ሰው ስንት ወንበር አለው?" ብሎ ማሰብ ነው። ከላይ በተዘረዘሩት ቦታዎች ሁሉ ወንበር ካለ እያንዳንዱ ዜጋ በነፍስ ወከፍ 10 ወንበር አይኖርም? ይኖረዋል እንጂ!

የዓለም ሕዝብ 6 ቢሊዮን ነው ብንል ከ60 ቢሊዮን በላይ ወንበሮች ምድርን አጨናንቀዋታል ማለት ነው።

ልማድ ሆኖ ለዘመናት የተለየ ስም እንሰጣለን። ለምሳሌ የበረዶ ዘመን። ይህን ዘመን ምን ብለን እንጥራው? "የወንበር ዘመን?"

ዓለማችን ድንገት እንዲህ ወንበር በወንበር የሆነችበት ምስጢር ግን ምንድነው?

Image copyright Getty Images

ሕዝቦች ሆይ! ወንበር አትውደዱ!

ከ16ኛው እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩት ወንበሮች ቁጥራቸው በድንገት ማሻቀብ የጀመረው በኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን እንደሆነ ይታመናል።

ከዚያ በፊት ወንበር አልነበረም ባንልም አብዛኛው ሕዝብ ወንበር ነበረው ለማለት የታሪክ ሰነዶች አልተገኙም። ወንበር ድሮም የነገሥታትና የመኳንንት ንብረት ነበር።

እንኳን ያኔ ይቅርና ዛሬም እኮ በቆንጆ ጣውላ የተላገ ምቹ ወንበር ያለው ሕዝብ ስንቱ ነው? ውድ ነዋ!

ነገር ግን በ18ኛው ክፍለ ዘመን በፈረንሳይ ፍርድ ቤት ዘና ለጠጥ ብሎ መቀመጥ ለተራ ዜጎች በመፈቀዱ ወንበሮች ዝነኛ እየሆኑ መጡ።

ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ

ከዚያ በፊት ግን ለዘመናት ወንበሮች ከሥልጣን ፣ ከብልጽግናና ከኑሮ ደረጃ ጋር ብቻ ነበር የሚዛመቱት።

ድሮ ንጉሥ በወንበር ላይ ይቀመጥና አሽከሮቹ ከነወንበሩ ነበር ከቦታ ቦታ የሚያንቀሳቅሱት።

ዛሬ ዛሬ እንኳ ያ የለም። ነገሥታትም አንድ ጊዜ ወንበሩ ላይ ከተቀመጡ በኋላ ማንም እንዲያንቀሳቅሳቸው አይፈቅዱም።

Image copyright Getty Images

ወንበርና ሥልጣን

ወንበር "ሥልጣን" ለሚለው ቃል አቻ ነው። በእንግሊዝኛ ሥራ አስኪያጅ የሚለው ቃል «ቼይር ፐርሰን» የሆነውም ለዚሁ ነው።

ድሮ የአገሪቱ ቆንጆውና ግዙፉ ወንበር የንጉሡ ነበር። በዚህ ዘመን ደግሞ ተሽከርካሪውና ባለቆዳው ወንበር የሥራ አስኪያጁ ነው።

ድሮ ወንበር እምብዛምም ነበር ብለናል። በቪክቶሪያ ዘመን አብዛኛው ሥራ ፋብሪካ ውስጥ ስለነበር ወንበር አይታሰብም ነበር።

በሳተላይቶች ዙሪያ ሰባት አስደናቂ እውነታዎች

ከፈረንሳይ አብዮት በኋላ ግን የሥራ ሁኔታ እየተቀየረ መጣ።

በተለይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጀምሮ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ብቅ ብቅ ማለት ሲጀምሩ እነ መተየቢያ፣ እነ ስልክ፣ እነ ኤሌክትሪክ ሲመጡ ሥራ የሚሠራበትም መንገድም በዚያው መጠን እየተቀየረ ሄደ።

ጋዜጣ፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ መጻሕፍት፣ ቪዲዮ መጫወቻ፣ ኢንተርኔት ወዘተ ወደ ሕይወታችን ብቅ ብቅ ማለት ሲጀምሩ ነገሩ ሁሉ መልኩን ቀየረ። ከወንበራችን ተጣብቀን መዋል ጀመርን።

Image copyright Getty Images

ወንበር እና ሲጃራ

በአሁን ዘመን ያለ ወንበር ሥራ መሥራት ይቻላል? ወንበሮች እጅግ አስፈላጊ እየሆኑ መጥተዋላ።

የብሪታኒያ የልብ ጤና ፋውንዴሽን ባስጠናው ጥናት በቀን ውስጥ በአማካይ 9.5 ሰዓት እንቀመጣለን፤ በሥራም ይሁን በሌላ። ይህ ማለት ሲሶውን የሕይወታችንን ዘመን በሥልጣን ባይሆንም በወንበራችን ላይ እናሳልፈዋለን።

ይህ በፍጹም መልካም ዜና አይደለም። ለምን?

አጥንታችንና ጡንቻችን ስንቀመጥና ስንንቀሳቀስ ባሕሪያቸው ይለያያል። ስንንቀሳቀስ ወጠርጠር፣ ጠንከርና ፈርጠም ይላሉ። ቁጭ ካልን ደግሞ ይልፈሰፈሳሉ።

የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች

ዘለግ ላለ ሰዓት በወንበር ለጠጥ ብሎ መቀመጥ ወገባችንን የሚያደቅ ተግባር ነው።

ለዚህም ይመስላል በዓለም ላይ ለጀርባ ሕመም አንደኛው አጋላጭ ምክንያት አብዝቶ መቀመጥ የሆነው።

በቀደመው ዘመን ወረርሽኝ ገዳይ ነበር። በዚህ ዘመን ደግሞ ቁጭ ማለት በሚያመጣው ጣጣ ሕዝብ እያለቀ ነው።

ስኳር፣ የልብ ሕመም፣ ካንሰር ወዘተ አንድ ቦታ በመወዘፍ የሚመጡ ናቸው።

መቀመጥ አደጋ አለው!

ከስድስት ዓመት በፊት አንድ ጥናት ተደረገ።

8ሺህ የሚሆኑ ሴቶች ላይ ነበር ጥናቱ ያተኮረው። ውጤቱ አስገራሚ ነበር። ዘለግ ላለ ሰዓት ወንበር ላይ ቁጭ ያሉት ሴቶች ሕዋሶቻቸው በፍጥነት ገረጀፉ። የማርጀት ምልክቶች ጎልተው ታዩባቸው።

በደንብ ከሚንቀሳቀሱና ብዙም የማይቀመጡት ሴቶች ጋር ሲነጻጸሩ በ8 ዓመት ገርጅፈው ነው የተገኙት።

ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን?

ረዥም ሰዓት ቁጭ የሚል ሰው ጉዱ ፈላ ይላሉ ተመራማሪዎች።

አንዳንድ ጥናቶች እንደውም ረዥም ሰዓት በመቀመጥ የሚመጣው ፍዳ ኃይለኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ቢደረግም የሚፈታ አይደለም ይላሉ።

እና ምን ተሻለ?

በየሩብ ሰዓቱ ከወንበራችን እየተነሳን በሰበብም ያለሰበምም መንቀሳቀስ ነው የሚበጀን። እግረኞች ተስፋ አላቸው። ባለመኪኖች ግን በጊዜ መላ ፈልጉ ተብላችኋል።

ተያያዥ ርዕሶች