ደቡብ አፍሪካ፡ ግርዛት የ21 ታዳጊ ወንዶችን ህይወት ቀጠፈ

Image copyright CARL DE SOUZA

ኢትዮጵያ

• የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን አስመልክቶ ብሄራዊ የሃዘን ቀን አወጀ።

በዚህም መሰረት የቀድሞ ፕሬዝዳንቱ ግብአተ መሬት የሚፈጸምበት ረቡዕ ታህሳስ 10/2011 ዓ.ም ብሄራዊ የሀዘን ቀን ሆኖ ይውላል።

ጋና

• የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ በሙስና ወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉ ሶስት ከፍተኛ የፍርድ ቤት ዳኞችን ከስራ አሰናበቱ።

ዳኞቹ በድብቅ ምርመራ ሲደረግባቸው የነበረ ሲሆን፤ ከገንዘብ እስከ ፍየል ድረስ ያገኙትን ይቀበሉ ነበር ተብሏል።

በይገባኛል ጥያቄ እሳት የምትለበለበው ሞያሌ

ኢትዮጵያዊያን ዛምቢያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ደቡብ አፍሪካ

• ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ባለፈው ህዳር ወር ከተጀመረ ዓመታዊ የግርዛት ስነስርአት ጋር በተያያዘ 21 ታዳጊ ወንዶች መሞታቸው ተገለጸ።

ታዳጊዎቹ የሞቱት መንግስት ክልከላ የጣለባቸው ባህላዊ ስነስርአቶች ላይ መሆኑ ደግሞ ጥያቄ አስነስቷል።

ሞሮኮ

• ሞሮኮ ሁለት ሴት ጎብኚዎችን በመግደል ጠርጥሬዋለው ያለችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዋለች።

ከሟቾቹ አንዷ ዴንማርካዊ መሆኗ ሲረጋገጥ፤ ታዋቂው ቶብካል ተራራን ለመጎብኘት ነበር የመጡት ተብሏል።

እንግሊዝ

• የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ ከሁለት ዓመት ተኩል አስቸጋሪ ቆይታ በኋላ ከስራቸው ተሰናበቱ።

ክለቡ ባወጣው መግለጫ አሰልጣኙ ለሰሩት ስራ በማስመስገን ቡድኑን በአደራ ተቀብሎ የሚያሰለጥን ሰው በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ብሏል።

• አዲስ የተወለደ ልጃቸውን አዶልፍ ሂተለር የሚል ስያሜ የሰጡት እንግሊዛውያን የአምስትና የስድስት ዓመት እስር ተፈደባቸው።

ብያኔውን ያስተላለፈው ፍርድ ቤት ባለትዳሮቹ ማዕቀብ የተጣለበት አሸባሪ ቡድን አባልም ነበሩ ብሏል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በቅዳሜው ውይይት ላይ ምን አሉ?

ምግብ አመላላሿ ሮቦት በእሳት ተያያዘች

ቱርክ

• የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ሃገራቸው በማንኛውም ሰዓት ሶሪያ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ልትጀምር እንደምትችል አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ የቱርክ ጦር በሰሜናዊ ሶሪያ በኤፍራጠስ ወንዝ አካባቢ በሚገኙት የኩርድ ሃይሎች ላይ ወታደራዊ ዘመቻ እንደሚጀምር ተናግረዋል።

ኤል ሳልቫዶር

• የሃገሪቱን ጥብቅ የፀረ-ውርጃ ሕግ ጥሰሻል በሚል ክስ ተፈርዶባት የነበረችው ኤል ሳልቫዶራዊት ሴት እሥሩ እንዲነሳላት ተወሰነ።

ኢሜልዳ ኮርቴዝ የተሰኘችው የ20 ዓመት ወጣት ብዙ ወሲባዊ በደል በሚያደርስባት እንጀራ አባቷ ተደፍራ ነበር ጽንሱን ያስወረደችው።

የመን

• የመናዊቷ እናት በካሊፎርኒያ በሞት አፋፍ ላይ የሚገኝ ህፃን ልጇን ለማየት ወደ አሜሪካ እንዳትገባ ተከለከለች።

የህፃኑ እስትንፋስ ያለው በህክምና መሳሪያ ድጋፍ ሲሆን መሳሪያው ተነስቶ እስትንፋሱ እንዲቋረጥ ከመደረጉ በፊት እናቱ ለመጨረሻ ጊዜ ልታየው ፈልጋ ነበር።

አሜሪካ 62 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገደልኩ አለች

• ተግባራዊ በሆነ በደቂቃዎች ውስጥ የተኩስ አቁም ስምምነቱ የተጣሰባት የየመኗ ሁደይዳህ ከተማ መረጋጋቷ ተጠቀሰ።

ሁለቱ የየመን ተዋጊ ሃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነቱን ያደረጉት በተባበሩት መንግስታት አስተባባሪነት ባለፈው ሳምንት ስዊድን ውስጥ ነበር።