ሆዜ ሞሪንሆን የሚተካው የዩናትዶች ቋሚ አሰልጣኝ ማን ይሆን?

ራይን ጊግስ፣ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር እና ዴቪድ ቤካም እአአ 2002 ዩናይትዶች ሊድስ ዩናይትድ ላይ ጎል አስቆጥረው ደስታቸውን ሲገልጹ Image copyright PAUL BARKER
አጭር የምስል መግለጫ ራያን ጊግስ፣ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር እና ዴቪድ ቤካም በፈረንጆቹ 2002 ዩናይትዶች ሊድስ ዩናይትድ ላይ ጎል አስቆጥረው ደስታቸውን ሲገልጹ

ማንችሰተር ዩናይትድ ኦሌ ጉናር ሶልሻየርን የቡድኑ ጊዜያዊ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።

ማክሰኞ ምሽት ላይ ክለቡ በድረ-ገጹ ላይ በስህተት ሶልሻየር ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙን ካሳወቀ በኋላ መልሶ መግለጫውን ከድረ-ገጹ ላይ ሰርዞት ነበር። ይሁን እንጂ ከደቂቃዎች በፊት ክለቡ በይፋዊ ድረ-ገጹ ላይ ሶልሻየር የክለቡ ጊዜያዊ አሰልጣኝ መሆኑን አስረግጧል።

ማንችሰተር ዩናይትድ በግሪጎሪ አቆጣጠር 1999 ላይ የቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ውድድር ላይ ሶልሻየር ጎል ሲያስቆጥር የሚያሳይ ቪዲዮ ከጫነ በኋላ ''ጊዜያዊ አሰልጣኛችን'' ሲል ገልጾት ነበር።

የኖርዌይ ዜጋ የሆነው የቀድሞ የዩናይት የፊት መስመር ተጫዋች ቀያይ ሰይጣኖቹ ቋሚ አሰልጣኝ እስኪያገኙ ተጠባባቂ አሰልጣኝ ሆኖ ይቆያል።

የዩናይትዶች ቋሚ አለቃ ማን ሊሆን ይችላል? የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል። ከዚያ በፊት ግን ዩናይትዶች ቋሚ አድርገው ከሚቀጥሩት አሰልጣኝ ምን ይፈልጋሉ የሚለውን እንመልከት።

ዩናይትዶች ቋሚ አድረገው የሚቀጥሩት አሰልጣኝ፤

  • ለክለቡ ተስማሚ የሆኑ አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም የሚችል
  • ወጣት ተጫዋቾችን ማብቃት የሚችል
  • የክለቡን ፍልስፍና፣ የክለቡን የቆየውን የማጥቃት ባህል እና እሴቶች መረዳት የሚችል
  • ከተጫዋቾች እና ከአጠቃላይ የክለቡ ሰራተኞች ጋር መልካም ግኑኘነት መፍጠር የሚችል

ስለዚህ ማን ሊሆን ይችላል?

1. ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ

ከፍተኛ ቅድመ-ግምት የተሰጠው ለቶተንሃሙ አሰልጣኘኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ነው። ቶተንሃሞች ድንቅ ኳስ ይጫወታሉ። ቶተንሃምን የመሰለ ቡድን ያዋቀረው እሱ ባላስፈረማቸው ተጫዋቾች ነው። ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንም ጠንካራ ተጫዋቾችን ማምረት ችሏል።

ከተጫዋቾች እና ከመላው የቶተንሃም ክለብ ሰራተኞች ጋርም መልካም ግነኙነት አለው።

ፖቼቲኖ በሌላ ክለቦችም ተፈላጊ የሆነ አሰልጣኝ ነው። ሪያል ማድሪድ ይፈልገው ነበር። ማክሰኞ ዕለት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ወደ አዲስ ስታዲያም ሊሄድ ስለመሆኑ ለቀረበለት ጥያቄ ፖቼቲኖ ሲመልስ፤ ''ብዙ እውነት ያልሆኑ መላምቶች ሊሰጡ ይችላሉ። በመሰል መላምቶች ላይ ተንተርሼ ምላሽ መስጠት አልፈልግም። እኔ ትኩረቴ እዚህ ባለው ስራዬ ላይ ብቻ ነው'' ብሏል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት

2. ዚነዲን ዚዳን

ውጤታማ የእግር ኳስ ዘመን፣ ሶስት የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎች፣ ኃያሉን ሪያል ማድሪድን በማሰልጠን የሶስት ዓመታት ልምድ። ለማንችስተር ዩናይትድ አይመጥንም ይላሉ?

ዚዳን ከማድሪድ ጋር ከተለያየበት ሰዓት ጀምሮ ቀጣዩ ክለብ ዩናይትድ ሊሆን እንደሚችል በስፋት ሲነገር ቆይቷል። ዚዳን ወደ ኦልድ ትራፎርድ ቢያቀና ከሃገሩ ልጆች ፖል ፖግባ እና አንቶኖዮ ማርሻል ጋር ጥሩ ግነኙነት ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል።

ይሁን እንጂ ዚዳን ወጣት ተጫዋቾችን የማብቃት አቅሙ እና የቴክኒክ አሰለጣጠን ክህሎቱ ጥያቄ ይነሳበታል። ይህ ብቻም አይደለም የዚዳን ደሞዝ ለዩናይትድ የማይቀመስ ሊሆን ይችላል።

ዚዳን ወደ ዩናይትዶች ሜዳ የሚመጣ ከሆነ የውድድር ዘመኑ እስኪጠናቀቀ መጠበቅ አይኖርበትም።

''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ

3. ዲዬጎ ሲሚዮኒ

ከዚህ ቀደም ዩናይትዶች አሰልጣኝ በሚፈልጉበት ወቅት ሲሚዮኒን አነጋግረውት ነበር።

ሲሚዮኒ በታክቲክ እጅጉን የተደራጀ አሰልጣኝ ነው። በላሊጋው ስኬታማ ጊዜዎችን እያሳለፈ ነው። እንደ ዩናይትዶች ታላቁ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ሁሉ ሲሚዮኒም የአሸናፊነት ስሜትን በማጫር ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሲሚዮኒ ከሞሪንሆ ጋር ተመሳሳይ የእግር ኳስ ፍልስፍና እንዳላቸው በርካቶች ይስማሙበታል። ታዲያ ዩናይትዶች ሆዜን አሰናብተው ከተሰናባቹ ጋር ተመሳሳይ የኳስ ባህሪ ያለውን አሰልጣኝ ወደ ኦልድትራፎርድ ያመጣሉ?

አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ

ተያያዥ ርዕሶች