ሱዳን ውስጥ የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ንሮብናል ያሉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ የሚሉና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

Image copyright Dmitry Feoktistov

ሱዳን

• ሱዳን ውስጥ የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ንሮብናል ብለው ተቃውሞ የወጡ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ።

ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲሆን፤ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ደቡብ አፍሪካ

• በፈረንጆቹ 2016 በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ የነበረው የሶስት ዓመት ደቡብ አፍሪካዊ ህጻን ገዳይ የእንጀራ አባቱ እንደሆነ ተገለጸ።

ቤቢ ዳኒኤል የተባለው ህጻን 60 በመቶ የሚሆነው ሰውነቱ የተቃጠለ ሲሆን፤ ጭንቅላቱ ላይም ከባድ ጉዳት ደርሶበት ነበር።

"በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው" የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ

ኮሚሽኑ ለምን አስፈለገ? ስልጣን እና ተግባሩስ?

ዩጋንዳ

• የአፍሪካ የቁንጅና ውድድርን ያሸነፈችው ዩጋንዳዊቷ ኩዊን አቤናክዮ ከፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ትችት ተሰነዘረባት።

ተፈጥሮአዊ ውበቷን በመተው ከህንድ የመጣ የሌላ ሰው ጸጉር መጠቀሟ ተገቢ አይደለም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

ሴኔጋል

• ሴኔጋል በፈረንጆቹ 2018 የፊፋ የሃገራት ደረጃ ሰንጠረዥ ከአፍሪካ አንደኛ ሆነች።

ኢትዮጵያ ደግሞ ከዓለም 151ኛ በመሆን ዓመቱን ታጠናቅቃለች።

የመን

• በሞት አፋፍ ላይ የነበረ ልጇን ለማየት ወደ አሜሪካ እንዳትገባ የተከለከለችው የመናዊ እናት በመጨረሻ ተፈቀደላት።

የሁለት ዓመቱ ልጇ ባጋጠመው የአእምሮ በሽታ ምክንያት በህይወት እንደማይቆይ ዶክተሮች ተናግረው ነበር።

እንግሊዝ

• እንግሊዝ ውስጥ ማን እንደሚያበራቸው ባልታወቁ ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች ምክንያት 760 በረራዎች ተስተጓጎሉ።

110 ሺ የሚሆኑ የጋትዊክ አየር ማረፊያ ደንበኞች ለቀናት በረራቸው ሊራዘም እንደሚችልም ተገልጿል።

ደቡብ ኮሪያ

• ተንበርክኮ ይቅርታ እንዲጠይቅ የተገደደው የኮሪያ አየር መንገድ ሰራተኛ ግማሽ ሚሊዮን ብር ካሳ ተሰጠው።

ለአየር መንገዱ ስራ አስኪያጅ ልጅ የለውዝ ፍሬ በላስቲክ በማቅረቡ ነበር ይቅርታ እንዲጠይቅ ተደርጎ የነበረው።

አሜሪካ

• የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወታደሮቻቸው ከሶሪያ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ማዘዛቸው ብዙዎችን አስገርሟል።

ትራምፕ ኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ተሸንፏል ቢሉም፤ ቡድኑ የበለጠ እንዳይጠናከር ግን ከፍተኛ ስጋት አለ።

1550 ተማሪዎች ለኩረጃ ሲሉ ስማቸውን ለውጠዋል

"ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ

ጃፓን

• ጃፓን ለንግድ አገልግሎት የሚውል የአሳ ነባሪዎች አደንን ልትፈቅድ ነው።

የአሳ ነባሪዎች አደን በፈረንጆቹ 1986 ሲሆን የታገደው፤ ህጉ በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ጀርመን

• ዴር ስፒገል የተባለ የጀርመን የዜና መጽሄት ባልደረባ የነበረ ጋዜጠኛ ሃሰተኛ ዜናዎችን በመፈብረክ ከስራው ተባረረ።

ክላስ ሬሎቲስ በዘገባዎች ላይ ሃሰተኛ መረጃዎችን አካቷል፤ እንዲሁም ገጸ ባህሪዎችን ፈጥሯል የሚሉ ክሶች ቀርበውበታል።

ተያያዥ ርዕሶች