አልሸባብ አይኤስ ላይ ጦርነት አወጀ የሚሉና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

የአልሸባብ ወታደሮች

የፎቶው ባለመብት, MOHAMED ABDIWAHAB

ኢትዮጵያ

• ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፥ ከግብር ጉዳይ ጋር በተያያዘ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ቀኑ ከመጨለሙ በፊት ወደ ስርዓት ይግቡ ሲሉ አሳስቡ።

ጠቅላዩ ይህንን ያሉት የገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀውና ሃገራዊ የታክስ ገቢ ማሰባሰብ ስርዓት መዘርጋት ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።

ሶማሊያ

• በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን አልሸባብ አይሲስ ላይ ጦርነት አወጀ።

አይኤስ ኢስላማዊ ጂሃድን መጠቀሚያ አድርጎታል፤ ለአላማችንም ጠንቅ ነው ሲል አልሸባብ አስታውቋል።

ግብጽ

• የግብጽ ፍርድ ቤት ከውጪ ሃገራት ገንዘብ ተቀብላችኋል ተብለው በእስር ላይ የነበሩ 43 የረድኤት ድርጅት ሰራተኞችን በነጻ አሰናበተ።

ከሰራተኞቹ መካከል ሶስት ግጻውያን፣ አንድ አሜሪካዊና አንድ ጀርመናዊ ዜጎች ይገኙበታል።

ደቡብ አፍሪካ

• ደቡብ አፍሪቃዊው የጃዝ ሙዚቃ ተጫዋች ሙሳ ማንዚኒ ስድስት ሰዓታትን የፈጀ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እየተደረገለት ጊታር መጫወቱ ብዙዎችን አስገርሟል።

የጭንቅላት ቀዶ ጥገናው የጣቶቹ እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመየት ያስችል ዘንድ ነው ጊታር እንዲጫወት የተፈቀለደት።

ላይቤሪያ

• ላይቤሪያውያን የገና በአልን ለማክበር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ሃገሪቱ ከፍተኛ የወረቀት ገንዘብ እጥረት አጋጥሟታል።

ባለፈው መጋቢት ወር ላይ ታትሞ የገባበት ያልታወቀው 100 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው የወረቀት ገንዘብ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ተገልጿል።

እንግሊዝ

• እንግሊዝ ውስጥ በስህተት በዘር ፍሬው ላይ የቀዶ ህክምና የተደረገለት አንድ የሁለት ዓመት ህጻን እንደመከነ ተገለጸ።

የልጃችንን የወደፊት ህይወት አበላሽታችሁብናል ሲሉ ቤተሰቦቹ ቅሬታ ያሰሙ ሲሆን፤ ሆስፒታሉ ጉዳዩን እየመረመረው ነው።

አልባኒያ

• አልባኒያ የደህንነት ስጋት ፈጥረውብኛል ያለቻቸውን የኢራን አምባሳደርና ሌሎች ዲፕሎማቶች ከሃገሯ አባረረች።

የኢራን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በበኩሉ ባልተረጋገጠና ሃሰተኛ በሆነ መረጃ ላይ ተመስርቶ የአልባኒያ መንግስት የወሰደው እርምጃ ተገቢ አይደለም ብሏል።

ህንድ

• ህንድ ውስጥ የ48 ዓመት እንግሊዛዊት ጎብኚን አስገድዶ ደፈረው ግለሰብ በሰአታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ግለሰቡ ከጾታዊ ጥቃቱ በተጨማሪ ጎብኚዋ ይዛቸው የነበሩ ሶስት ቦርሳዎችንም ነጥቆ ከአካባቢው ተሰውሮ ነበር።

• በህንድ በሚተዳደረው የካሽሚር ግማሽ ግዛት ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች ባህላዊ ልብሶችን መልበስ የሚከለክለው ህግ ተነሳ።

የአካባቢው ነዋሪዎችና ሰራተኞች ውሳኔውን በመቃወም ሲታገሉ የነበረ ሲሆን፤ የህጉ መነሳት እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

አሜሪካ

• አሜሪካ 7 ሺ የሚደርሱ ወታደሮቿን ከአፍጋኒስታን ልታስወጣ እንደሆነ አስታወቀች።

የዘርፉ ባለሙያዎች ግን ውሳኔው ለታሊባን ታጣቂዎች ነገሮችን ምቹ ያደርግላቸዋል በማለት ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።