የሱዳን ፖሊስ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል

የሱዳን ተቃውሞ እየተጋጋለ አምስተኛ ቀኑን ይዟል Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ የሱዳን ተቃውሞ እየተጋጋለ አምስተኛ ቀኑን ይዟል

የሱዳንን መንግሥት በመቃወም ወደ አደባባይ የወጡ ሰዎችን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሟል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ከፖሊሶች ጋር ከመጋጨታቸው በፊት በሱዳን መዲና ካርቱም ውስጥ የሚገኝ መንገድ ዘግተው ነበር።

የአይን እማኞች እንዳሉት፤ ተቃዋሚዎች "ፈጽሞ አንራብም" በማለት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ ተኩሰውባቸዋል።

አል-በሽር ካቢኔያቸውን በተኑ

በሱዳን እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ

ተቃዋሚዎች ካለፈው ሳምንት ረቡዕ ጀምሮ 22 ሰዎች ተገድለዋል ቢሉም፤ የመንግሥት ባለስልጣኖች የሟቾች ቁጥር ተጋኗል ብለዋል።

'ሴንትራል ሱዳኒዝ ኮሚቴ ኦፍ ዶክተርስ' የተባለ ተቋም አባላት እንዳሉት ከሆነ፤ ብዙ ሟቾች፣ በጥይት ተመተው የቆሰሉና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተቃዋሚዎች በህክምና መስጫዎች ታይተዋል።

የሱዳን ተቃውሞ የተቀሰቀሰው የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ነበር።

ባለፈው ዓመት የተለያዩ ሸቀጦች ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል። የዋጋ ንረት70 በመቶ ሲያሻቅብ፤ የሱዳን መገበያያ ዋጋ በጣም አሽቆልቁሏል።

የሱዳኑ ፕሬዘዳንት ኦማር አል-በሽር ላይ ጫና ለማሳረፍ ሀኪሞች በዚህ ሳምንት አድማ እንደሚመቱ ተናግረዋል።

ተቃውሞውን ተከትሎ 'ናሽናል ኮንሰንሰንስ ፎርስስ' የተባለው የተቃዋሚዎች ጥምረት 14 አመራሮች ያሳለፍነው ቅዳሜ ታስረዋል። የጥምረቱ ቃል አቀባይ፤ መንግሥት ተቃውሞውን ለማዳፈን አመራሮቹን ማሰሩን ተናግረው "በአፋጣኝ ይፈቱ" ብለዋል።

ሱዳን ውስጥ የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ንሮብናል ያሉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ

የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር አልተሳካም

ጠ/ሚ ዐብይ አልበሽርን የድንበር ግጭቱን አብረን እንፍታ አሉ

'ኡማ' የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሳዲቅ አል-ማዲ፤ ሕዝቡ ወታደራዊ ጭቆና እንዳስመረረው ተናግረዋል። የአል-በሽር አስተዳዳር በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን መልቀቅ አለበትም ብለዋል።

አል-ማዲ ሁለት ጊዜ የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩ ሲሆን፤ ከአንድ ዓመት ስደት በኋላ በቅርቡ ወደ ሱዳን ተመልሰዋል። አል-በሽር መፈንቅለ መንግሥት እስካደረጉባቸው ጊዜ ድረስ፤ የሳቸው አመራር በሱዳን ለመጨረሻ ጊዜ የተመረጠው ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ነበር።

ለሱዳን ኢኮኖሚ መላሸቅ እንደ ምክንያት ከሚጠቀሱት መካለከል፤ እንደ አውሮፓውያኑ በ1990ዎቹ አሜሪካ "የአል-በሽር መንግሥት ሽብርተኞችን ይደግፋል" በሚል እስከ 2017 ድረስ ጥላው የነበረው የንግድ ማዕቀብ ይጠቀሳል። ደቡብ ሱዳን በ2011 ስትገነጠል የሀገሪቱን አብላጫ የነዳጅ ሀብት ይዛ መሄዷም ይገኝበታል።

ተያያዥ ርዕሶች