ጓደኛውን ለወራት ሲመርዝ የነበረው ቻይናዊና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

ቻይናዊው ተማሪ

የፎቶው ባለመብት, Pennsylvania Police

ኢትዮጵያ

• የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ደብረጺሆን ገብረሚካኤል ክልላቸው ለስፖርተኞች ደህንነት ሃላፊነት እንደሚወስድ ገለጹ።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጫወቱ የአማራና የትግራይ ክለቦች በሜዳቸው ለሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ሁለቱም ክልሎች የደህንነት ዋስትና እንዲሰጡ ፌዴሬሽኑ ጠይቆ ነበር።

ሱዳን

• ሱዳን ውስጥ በሸቀጦች ዋጋ መናር ምክንያት የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ እስካሁን ቀጥሎ የ22 ዜጎችን ህይወት ቀጠፈ።

ተቃውሞው ባለፈው አርብ ነበር የዳቦና የነዳጅ ዋጋ መጨመር እጅጉን አስመርሮናል ብለው ወደ መንገድ በወጡ ሰልፈኞች የተጀመረው።

ናይጄሪያ

• በናይጄሪያዋ ዛማፋራ ግዛት 17 ሰዎች ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን የናይጄሪያ ፖሊስ አስታወቀ።

ታጣቂዎቹ በሞተር ሳይኮሎች በመሆን ወደ ተሰበሰቡ ሰዎች ይተኩሱ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ፈረንሳይ

• የፈረንሳዩ የገንዘብ ተቆጣጣሪ ተቋም የሃገሪቱን የፖስታ አገልግሎት ሰጪ 50 ሚሊዮን ዩሮ ቀጣ።

ምክንያቱ ደግሞ መንግስት እንዳይነቀሳቀሱ ያገዳቸው የ75 አሸባሪዎችን ገንዘብ አዘዋውሯል በሚል ነው።

ጃፓን

• ጃፓንን ለ30 ዓመታት የመሩት የ85 ዓመቱ ንጉስ አኪሂቶ ዙፋኑን ከመልቀቃቸው በፊት የመጨረሻ የስንብት ንግግር አደረጉ።

ንጉሱ ህዝባቸውንና ባለቤታቸውን ያመሰገኑ ሲሆን፤ በሚቀጥለው ዓመት ለመጀመሪያው ወንድ ልጃቸው ስልጣኑን የሚያስረከቡ ይሆናል

አውስትራሊያ

• አውስትራሊያ ውስጥ አዲስ የተሰራ የመኖሪያ ህንጻ የመደርመስ አደጋ ሊያጋጥመው ይችላል በሚል 3000 ነዎሪዎች እንዲወጡ ተደረገ።

ነዋሪዎቹ የግድግዳዎች መሰነጣጠቅ ድመጽ በመስማታቸው ለፖሊስ አመለክተው ነበር።

ቻይና

• ለትምህርት አሜሪካ የሄደው ቻይናዊ አብሮት የሚኖር ጓደኛውን ለብዙ ወራት በመመረዝ ወንጀል ተከሶ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ተማሪው ለምን እንዳደረገው ባይታወቅም ጓደኛው በተለያዩ ጊዜያት ከፍተኛ ህመም እያጋጠመው ወደ ሆስፒታል ይሄድ ነበር ተብሏል።

ህንድ

• የህንድ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በጎርፍ የተከበቡ 15 የማእድን አውጪ ሰራቶኞችን ለማዳን እያከናወኑት ያለው ስራ ከባድ ነው ተባለ።

በማዕድን ማውጫው ውስጥ ለ11 ቀናት የቆዩትን ሰራተኞች ለማውጣት የፈጣሪ ተአምር እየጠበቅን ነው ብለዋል የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹ።

ጣልያን

• በጣልያን ስደተኞች መጠለያ ውስጥ አንድ የሁለት ዓመት ህጻን በህገወጥ መንገድ ሲገረዝ ብዙ ደም በመፍሰሱ ህይወቱ አለፈ።

ግርዘቱን የፈጸመው የ66 ዓመት ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፤ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

ኢንዶኔዢያ

• ኢንዶኔዢያ ውስጥ እሳተ ገሞራ ባስከተለው ከፍተኛ የባህር ውሃ ግፊት ምክንያት 373 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።

የሃገሪቱ የአደጋ መከላከል መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው 1459 ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ ነዋሪዎችንም ከአካባቢው እያስወጡ ነው።