አርጀንቲናዊቷ ከ32 አመታት ጠለፋ ነፃ ወጣች

ከ32 አመታት ጠለፋ በኋላ ነፃ የወጣችው ሴት ከልጇ ጋር

የፎቶው ባለመብት, Argentine police

በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ተጠልፋ የነበረች አርጀንቲናዊ ከ32 ዓመታት በኋላ ነፃ ወጥታ ከቤተሰቦቿ ጋር ተገናኝታለች።

ይህም የሆነው በአርጀንቲናና በቦሊቪያ ፖሊሶች ጥምረት ኃይል እንደሆነም ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት 45ተኛ ዓመቷን የያዘችው ሴት ያለችበትን ቦታ ለዘመናት ማወቅ ሳይቻል ቢቀርም በቅርቡ ግን ፖሊስ በደቡባቢዊ ቦሊቪያ ትገኛለች የሚል ጥቆማ በማግኘቱ ነፃ ልትወጣ ችላለች።

ተይዛበት የነበረበትንም ቤት ማመላከት በመቻሉም እሷንም ሆነ የዘጠኝ ዓመት ልጇን ነፃ ማውጣት ተችሏል።

የሴትዮዋም ሆነ የልጇ ማንነታቸውም አልተገለፀም።

በትናንትናው ዕለት የአርጀንቲና ፖሊስ በሰጠው መግለጫ በመጨረሻም ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ተመልሳ እንደሄደች ነው።

መግለጫው ከ32 ዓመት በፊት ማን እንደጠለፋትም ሆነ ሊጠየቁ የሚገቡ አካላትን ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥቧል።