የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር በአለም ላይ ጥቃት የሚደርስባቸው ክርስቲያኖች ጉዳይ እንዲጠና አዘዙ

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጀርሚ ሐንት እና ሌሎች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀርሚ ሐንት በአለም ዙሪያ ስቃይ ስለሚደርስባቸው ክርስቲያኖች እና እንግሊዝ እነርሱን ለመርዳት ያደረገቻቸውን ጥረቶች እንዲጠኑ አዘዙ።

ጥናቱ በቢሾፕ ትሩሮ የሚመራ ሲሆን በዓለም ላይ ባለፈው ዓመት ብቻ ጥቃትና መገለል የደረሰባቸውን 215 ሚሊዮን ክርስቲያኖችን ለመርዳት መንግሥት ምን እንዳደረገ ይመረምራል።

የእንግሊዝ ባለስልጣናት በአለም ክርስትያኖች ላይ የሚደርስ ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን ተናግረው በየወሩ 250 ሰዎች ይገደላሉ ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀንት እነዚህን ክርስቲያኖች ለመታደግ "የተሻለ መስራት አለብን" ብለዋል።

"ብሪቴይን በአለም አቀፍ ደረጃ በእምነት ነፃነት የተመሰከረላት ናት" ካሉ በኋላ ክርስቲያኖች ላይ የሚደርስ ጥቃትም በቁጥር አነስተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚደረግ ጥቃት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው ብለዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ "ጥናቱ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችና የፖሊሲ ሀሳቦችን ይይዛል" ብለዋል።

የፎቶው ባለመብት, Handout

ጥናቱ ተጠናቅቆ ለፋሲካ እንደሚደርስ ይጠበቃል።

በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ቸል ተብለዋል የሚለው ስሞታ እየበረታ የመጣው የፓኪስታናዊቷ ክርስቲያን ቢቢ የሞት ፍርድ ከተሰማ በኋላ ነው።

ቢቢ የሞት ፍርድ ከተፈረደባት ከስምንት አመት በኋላ የፓኪስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔውን መቀልበሱ ይታወሳል።

የቢቢ ቤተሰቦች ህይወት አደጋ ላይ ነው ያለው በማለት ባለቤቷ እንግሊዝ፣ አሜሪካ ወይንም ካናዳ ጥገኝነት እንዲሰጡት የሚጠይቅ ሰልፍ ተደርጎ ነበር።

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ በሕዝብ እንደራሴዎች የቢቢ ባለቤት ጥገኝነት እንዳያገኝ ተከላክለው እንደሆነ ተጠይቀው አስተባብለዋል።

ሜይም ለጠየቃቸው የሕዝብ እንደራሴ ሲመልሱ "በጋዜጣ ላይ የተፃፈውን ሁሉ ማመን የለብዎትም" በማለት ቀዳሚው ጉዳይ የቢቢ ቤተሰብ ደህንነት ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።