አልሸባብ ኬንያ ውስጥ የቦንብ ጥቃት አደረሰ የሚሉና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

አሳነባሪ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

አፍሪካ

• አልሸባብ ኬንያ ውስጥ ማንዴራ በተባለች ከተማ በፈጸመው የቦንብ ጥቃት አራት ፖሊሶች ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ።

ኬንያን ከሶማሊያ በምታዋስነው ከተማ ድንበር ጠባቂዎች ላይ የሚፈጸሙ ይህ አይነት ጥቃቶች አዲስ አይደሉም ብሏል የሃገሪቱ ፖሊስ።

• የዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ ምርጫ ቦርድ የፊታችን እሁድ የሚካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በጸጥታ ችግርና በኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት በአራት ከተሞች ሊያራዝመው እንደሆነ ገለጸ።

ምርጫው ከተራዘመባቸው ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው ቡቴምቦ ከተማ ነዋሪዎችን ግን ውሳኔው የመንግሥት ሴራ ነው ብለዋል።

ደቡብ አሜሪካ

• ለ32 ዓመታት በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ተጠልፋ የቆየችው አርጀንቲናዊ ነፃ ወጥታ ከቤተሰቦቿ ጋር መገናኘቷ ተሰምቷል።።

በአሁኑ ወቅት 45ተኛ ዓመቷን የያዘችው ሴት በቅርቡ በደቡባቢዊ ቦሊቪያ ትገኛለች የሚል ጥቆማ ፖሊስ በማግኘቱ ነፃ ልትወጣ ችላለች።

• በአሜሪካ ድንበር ላይ ተይዞ በሕግ ጥላ ስር የነበረው የስምንት አመቱ ጓቲማላዊ ስደተኛ ፌሊፔ አሎንዞ ህይወቱ እንዳለፈች ተገለጸ።

የሜክሲኮና የአሜሪካን ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ ተይዘው ከነበሩ ህፃናት መካከል በዚህ ወር ብቻ ይህ ህፃን ሲሞት ሁለተኛው ነው።

መካከለኛ ምስራቅ

• የሶሪያዋ ዋና ከተማ ዳማስከስ ከትላንት ምሽት ጀምሮ በከባድ ፍንዳታዎች ስትናወጥ እንደቆየች ተገለጸ።

ሶስት ወታደሮች ላይ ጉዳት ያደረሰው ጥቃት የተፈጸመው በእስራኤል ወታደሮች እንደሆነ የሃገሪቱ መከላከያ ሃይል አስታውቋል።

• በአምስት ጀልባዎች ተሳፍረው የነበሩ አርባ ስደተኞች ከቀናት እንግልት በኋላ በእንግሊዝ የባህር ጠባቂዎች ተገኙ።

ስደተኞቹ ከኢራቅ፣ ኢራንና አፍጋኒስታን ሲሆኑ፤ ሁለት ህጻናትም ይገኙበታል ተብሏል።

ጃፓን

• ጃፓን ለንግድ አገልግሎት አሳነባሪዎችን ማጥመድ ከመጪው ሃምሌ ጀምሮ ልትፈቅድ እንደሆነ አስታወቀች።

ሃገሪቱ ከአለማቀፉ የአሳነባሪ ኮሚሽን ራሷን ልታገልም እንደሆነ የገለጸች ሲሆን፤ ከአሁኑ ከባድ ትችት እየደረሰባት ነው።

ጣልያን

• የጣልያኗ ራስ ገዝ ደሴት ሲሲሊ 4.8 ማግኒቲዩት በተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች።

የከተማዋ አንዳንድ ህንጻዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ ኢትና በተባለው የእሳተ ገሞራ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ አከባቢውን በፍጥነት ለቅቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል።