ግብጽ ከሽብር ጥቃት ጋር በተያያዘ 40 ታጣቂዎችን ገደለች

የግብጽ ወታደር Image copyright Getty Images

የግብጽ ፖሊስ ባለፈው አርብ ከደረሰው የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ 40 ታጣቂዎችን እንደገለ የሃገር ውስጥ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ አሰታወቀ።

አርባዎቹ ታጣቂዎች ቅዳሜ ዕለት የተገደሉት ጊዛ በተባለ ቦታና በሰሜናዊ ሲናይ ሲሆን፤ በአብያተ ክርስቲያናትና ጎብኚዎች ላይ ሌላ ጥቃት ለማድረስ ዝግጅት ሲያደርጉ ነበር ብሏል ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ።

ጊዛ ውስጥ ባለፈው አርብ በጎብኚዎች ማጓጓዣ አውቶቡስ ላይ በተሰነዘረው የቦምብ ጥቃት አራት ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፤ አስራ አንድ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች

የኮንጎ ምርጫ መጓተት ህዝቡን አስቆጥቷል

በግብጽ መስጊድ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 235 ሰዎች ሞቱ

አስራ አራት የቬትናም ዜግነት ያላቸው ጎብኚዎችንና አንድ ግብጻዊ አስጎብኚን ይዞ ሲጓ የነበረው አውቶቡስ ላይ ለደረሰው ጥቃት እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ ቡድን የለም። ግብጽ ውስጥ ጎብኚዎች ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩ ታጣቂዎች ግን በርካታ እንደሆኑ ይነገራል።

በጊዛ ከተማ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 30 ታጣቂዎችን የደመሰሰ ሲሆን፤ በሰሜናዊ ሲናይ ግዛት ዋና ከተማ ኤል አሪሽ በተደረገ ሌላ ወታደራዊ ዘመቻ ደግሞ ተጨማሪ 10 ታጣቂዎች መገደላቸውን መግለጫው ያትታል።

ከዚህ በተጨማሪ ቦምብ ለመስራት የሚያገለግሉ መሳሪያዎችንም ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ተገልጿል።

የጎብኚዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ በሆነበት በዚህ ሰዓት ግብጽ የጥበቃ ስራዋን ከሌላ ጊዜው በተለየ ጠበቅ ያደረገች ሲሆን፤ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮችና ቤተ አምሎኮዎቻቸው እንዲጠበቁ እየተደረገ ነው።

የትራምፕ አማካሪ፡ የግንቡ ውጥን ውድቅ ከተደረገ ሰነባብቷል

በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል?

ጥቃት የተሰነዘረበት አውቶቡስ ከታሰበለት የጉዞ መስመር ውጪ ሄዶ እንደነበር የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢናገሩም፤ አሽከርካሪው ግን ምንም የማውቀው ነገር የለም ብሏል።