የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የሙዚቃ አልበም ሊለቁ ነው

ጃኮብ ዙማ Image copyright Getty Images

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የሙዚቃ አልበም ለማውጣት ከአሳታሚዎች ጋር መስማማታቸው አዲስ ፖሊቲካዊ ንትርክን አስነስቷል።

ኢተክዊኒ የተባለው የሃገሪቱ ግዛት የተቃውሞ ዘፈኖች የሚበዙበትን የፕሬዝዳንቱ አልበም ሙሉ ወጪ እሸፍናለው ማለቱ ብዙዎች ያስደሰተ አይመስልም።

የሃገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲ ዴሞክራቲክ አላያንስ በበኩሉ ውሳኔው የህዝብን ሃብት ያለአግባብ ማባከን ነው ብሎታል።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት በስልጣን ዘመናቸው ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ 'ብሪንግ ሚ ማይ ማሽን ጋን' የሚለውን ዘፈናቸውን በመድረክ ላይ ይጫወቱ ነበር። ትርጓሜውም መትረየሴን አቀብሉኝ እንደማለት ነው።

13 አስደናቂ የፓስፖርት እውነታዎች

ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ተወልደው ያደጉባት መንደር በኢተክዊኒ ግዛት የምትገኝ ሲሆን፤ ብዙ ደጋፊዎቻቸውም የሚገኙት እዚሁ አካባቢ ነው።

ዝዋኬሌ ምክዋንጎ የተባለ የተቃዋሚ ፓርቲው አመራር እንደተናገረው የሃገሪቱ ወጣቶች ሙዚቃን በመጠቀም ባህላቸውን ለማሳደግ በገንዘብ እጥረት በሚሰቃዩባት ሃገር፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በሃገር ሃብት ተጠቅመው ይህንን ለማድረግ መወሰናቸው ተገቢ አይደለም ብሏል።

የ76 ዓመቱ ጃኮብ ዙማ በፈረንጆቹ ህዳር 2018 ላይ ነበር በፓርቲያቸው 'ኤኤንሲ' ከስልጣናቸው እንዲለቁ የተደረጉት። ከስልጣን ዘመናቸው በኋላ ከሙስና ጋር የተያያዙ ክሶች ቀርበውባቸዋል።

በአዲስ ዓመት 4 ቢሊየን ብር በሎተሪ ያገኘው እንግሊዛዊ

የቀድሞው ፕሬዝዳንት የነጮች የበላይነት በነበረበት ወቅት የሚዜሙ የትግል ዘፈኖችን ጥንቅቅ አድርገው ስለሚያውቁ ነው ሙሉ ወጪያቸውን ለመሸፈን የወሰንነው ብለዋል አንድ የኢተክዊኒ ግዛት ባለስልጣን።

ዘፈኖቹም ወጣቶች ለመብታቸው እንዲታገሉ የሚያነሳሳ በመሆኑ ምንም ተቃውሞ ሊቀርብበት አይገባም ሲሉም ተደምጠዋል።

ተያያዥ ርዕሶች