የናይጀሪያ ወታደሮች ዴይሊ ትረስት የተባለውን የጋዜጣ ቢሮ ከበቡ

ወታደሮች በናይጀሪያዋ መዲና አቡጃ Image copyright AFP

የናይጀሪያ ወታደሮች ዴይሊ ትረስት የተባለውን የግል ጋዜጣ ዋና ቢሮ በመክበብ ኮምፒውተሮችን ወስደዋል።

በሀገሪቷ ውስጥ ስመ ጥርና ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ዴይሊ ትረስት እንዳሳወቀው ወታደሮቹ በመዲናዋ አቡጃ የሚገኘውን ቢሮ ዋነኛ በር ገንጥለው እንደገቡ ነው።

ወታደሮቹ ታጥቀው የነበረ ሲሆን በሶስት ሚኒባስም ተጭነው ነበር።

የአይን እማኞች ለቢቢሲ እንደገለፁት የጋዜጣውን ሰራተኞች ያላቸውን ኮምፒውተር እንዲያስረክቡ ካዘዟቸው በኋላ ቢሮውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውታል።

የሪፐብሊኩ ጠባቂ ሃይል መቋቋም ምን ያመለክታል?

"አቶ ጌታቸው አሰፋን ሜክሲኮ አግኝቻቸው ነበር" ነጋ ዘርዑ

ከዚህም በተጫማሪ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ማዕከል በምትባለው ማይድጉሪ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን ቢሮ በመክበብ የጋዜጣውን የቀጠና አርታኢ ኡትማን አቡባከርና ሪፖርተሩን ኢብራሂም ሳዋብ ታስረዋል።

ጋዜጣው እንዳሳወቀው ይህ ከበባ የተካሄደው እሁድ እለት ወታደሮቹ ያጧቸውን ግዛቶች ለማስመለስ ተልዕኮ ጀምረዋል የሚለው ፅሁፍ መታተም ጋር የተያያዘ እንደሆነ ነው።

ሰራዊቱ በበኩሉ ሁለት ከተሞቹን ለታጣቂዎች አጥቷል የሚለውን ቢክድም ዴይሊ ትረስት ላይ ሰራዊቱ ለምን እንዲህ አይነት ድርጊት ፈፀመ ለሚለው ምክንያት ከመስጠት ተቆጥቧል።

በናይጀሪያ ሰሜናዊ ምስራቅ አካባቢ ግዛቱን ከአውሮፓውያኑ 2009 ጀምሮ እያጠናከረ ያለው ይህ ታጣቂ ቡድን መንግሥትን በኃይል ገርስሶ እስላማዊ ሀገርን የመመስረት አላማን አንግቦ የተነሳ ነው።

ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ?

ባለፈው ሳምንት የአይን እማኞች ለቢቢሲ እንደገለፁት ከአይኤስ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂ ቡድኖች ባጋ በምትባለው ግዛት ሰንደቅ አላማቸውን ከተከሉ በኋላ በመቶ የሚቆጠሩ ነዋሪዎቿን ከከተማዋ እንዲወጡ አድርገዋል።

በዴይሊ ትረስት ፅሁፍም ላይ እንደተጠቀሰው ባጋ፣ ዶሮን ባጋ የመሳሰሉ ከተሞችን ከታጣቂዎች ለማስመለስ በሰራዊቱ በኩል ከፍተኛ ወታደራዊ ተልዕኮ እንደታቀደ ነው።

በቦታው ያሉ ዘጋቢዎች እንዳሳወቁት ሰራዊቱ ለትችት ስስ ብልት እንዳለውና ታጣቂዎችን ማሸነፍ ያለመቻላቸውን ውድቀት እንደማይቀበሉት ነው።