በነፍስ ማጥፋት እድሜ ልክ የተፈረደባት አሜሪካዊት በነጻ ተሰናበተች

ሲንቶያ ብራውን Image copyright CBS News

በአሜሪካዋ ቴነሲ ግዛት የምትገኝ አንዲት ሴት ጥቃት ሊያደርስባት የነበረን ግለሰብ በመግደሏ ከ15 ዓመታት የማረሚያ ቤት ቆይታ በኋላ በግዛቲቱ አስተዳዳሪ ትእዛዝ በነጻ እንድትሰናበት ተወሰነላት።

ሲንቶያ ብራውን በአውሮፓውያኑ 2004 ዓ.ም. በ16 ዓመቷ በቀረበባት ክስ ጥፋተኛ ተብላ የነበረ ሲሆን በሰላሳ አመቷ ደግሞ ጥፋተኛ አይደለችም ተብላለች።

በወቅቱ የ16 ዓመት ታዳጊ የነበረችው ብራውን በህገወጥ የሴቶች ዝውውር ተጠቂ የነበረችና እራሷን ለመከላከል ስትል ግለሰቡን ተኩሳ እንደገደለችው ጠበቆቿ ቢገልጹም፤ ፍርድ ቤቱ ግን ጥፋተኛ ናት በማለት የእድሜ ልክ እስራት በይኖባት ነበር።

ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ተፈለሰፈ

ሴቶች በሰሜን ኮሪያ ሠራዊት ውስጥ

''ወደቤቱ ከወሰደኝ በኋላ በሃይል ጥቃት ይሰነዝርብኝ ነበር፤ በመጨረሻም ከአልጋው ስር የሆነ ነገር ሊያወጣ ሲሞክር ሽጉጥ ሊሆን ይችላል ብዬ ስለፈራሁ እራሴን ለመከላከል ተኩሼ ገደልኩት'' ብላለች ብራውን ሁኔታውን ስታብራራ።

የቴነሲ ግዛት ዋና አስተዳዳሪ ሰኞ እለት እንዳስታወቁት ብራውን ከመጪው ሃምሌ ወር ጀምሮ በነጻ እንድትሰናበት ማዘዛቸውን ገልጸዋል።

"ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ

በማረሚያ ቤት ቆይታዋ ትምህርት በመከታተል የመጀመሪያ ዲግሪዋን ማግኘት የቻለችው ብራውን፤ ጥሩ ዜጋ በመሆን አስተዳዳሪውን ለማኩራት እንዳሰበችና ለእሷ መብት ሲታገሉ ለነበሩ በሙሉ ምስጋና ማቅረብ እንደምትፈልግ ገልጻለች።