ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ከቀረበበት የመድፈር ክስ ጋር በተያያዘ የዘረመል ናሙና እንዲያቀርብ በፖሊስ ታዘዘ

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ Image copyright Getty Images

የላስ ቬጋስ ፖሊስ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ከቀረበበት የመድፈር ክስ ጋር በተያያዘ የዘረመል ናሙና እንዲያቀርብ የሚያዝ ደብዳቤ ከፍርድ ቤት ማህተም ጋር አያይዞ እንዳስገባ ተገለጸ።

የ33 ዓመቱ ጠበቃ የሆኑ ፒተር ክሪስቲያንሰን እንደገለጹት የፖሊስ ጥያቄ የተለመደና በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች የሚያገለግል የህግ አሰራር ነው ብለዋል።

'ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል' የተባለ ጋዜጣ እንደዘገበው የላስ ቬጋስ ፖሊስ ጥያቄ እሱ በሚጫወትበት ሃገር ጣልያን ለሚገኝ ፍርድ ቤት ተልኳል። በጎርጎሳውያኑ 2009 ዓ.ም. ፈጽሞታል ተብሎ የቀረበበትን ክስ የጁቬንቱሱ የፊት መስመር ተጫዋች ጉዳዩ ሀሰት ነው በማለት ተከራክሯል።

ሮናልዶ "ደፍሮኛል" ያለችው ሴት ከመብት ተሟጋቾች ድጋፍ አገኘች

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ወሲባዊ ጥቃት አላደረስኩም አሉ

ሞርጋን ፍሪማን በፆታዊ ትንኮሳ ለቀረበባቸው ውንጀላ ይቅርታ ጠየቁ

በ2009 የተከሰተው ጉዳይ በሁለቱም መካከል በመፈቃቀድ ነው እንጂ ደንበኛዬ ምንም አይነት አስገድዶ ያደረገው ነገር የለም ብሏል ጠበቃው።

'ዴር ስፒግል' የተባለ የጀርመን ጋዜጣ ነበር ማዮርጋ የተባለችው ሴት ለላስ ቬጋስ ፖሊስ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ክስ መመስረቷን ለመጀመሪያ ጊዜ የዘገበው። እንደ ጋዜጣው ከሆነም ማዮርጋ በጎርጎሳውያኑ 2010 ክሪስቲያኖ ሮናልዶ 375 ሺ ዶላር እንዲከፍላት ተስማምታ ነበር።

የሮናልዶ ጠበቃ እንደሚለው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ የቀረቡት ማስረጃዎች በሙሉ የውሸትና የተቀነባበሩ ናቸው።

ወይዘሪት ማዮርጋና ሮናልዶ በ2009 በላስቬጋስ ፓልም ሆቴልና ቁማር ቤት በሚገኘው ሬይን የምሽት ጭፈራ ቤት ይገናኛሉ። ከዚያም ጨዋታ ሲደራ ሮናልዶ ወደ ራሱ ማደሪያ እንደወሰዳትና እንደደፈራት ገልጻ ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች