የላውሮ ግምት፡-ማንቸስተር ከዩናይትድ ከቶተንሃም ማን ያሸንፍ ይሆን?

እሁድ በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ጥሩ አቋም ላይ የሚገኙት ማንቸስተር ዩናይትዶችና በደረጃ ሰንጠረዡ ሶስተኛ ላይ የሚገኘው ቶተንሃም ይጫወታሉ።

በጊዜያዊው አሰልጣኝ ሶልሻየር የሚመራው ዩናይትድ በፕሪምየር ሊጉ ተከታታይ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበ ሲሆን በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ግንኙነታቸው ቶተንሃም ነበር ያሸነፈው።

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ዌስትሃም ከአሰናል

ዌስትሃሞች በፕሪምየር ሊጉ ጥሩና ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት የተሳናቸው ሲሆን አርሰናሎችም ቢሆኑ አስፈሪ የሚባለው አጨዋወታቸው እየራቃቸው የመጣ ይመስላል ይላል ላውሮ።

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ከቀረበበት የመድፈር ክስ ጋር በተያያዘ የዘረመል ናሙና እንዲያቀርብ ታዘዘ

በጥዋት ከእንቅልፍ መነሳት ውጤታማ ያደርጋል?

ይህንን ጨዋታ አርሰናሎች እንደሚያሸንፉ ምንም አልጠራጠርም የሚለው ላውሮ፤ አሰልጣኙ ኡናይ ኤምሪ ግን ብዙ የቤት ስራ እንደሚጠብቃቸው ይገልጻል።

የላውሮ ግምት: 1-2

Image copyright BBC Sport

ብራይተን ከሊቨርፑል

ሊቨርፑሎች በመሃል ተከላካይ መስመር ችግር አጋጥሟቸዋል። ዲጃን ሎቭረንና ጆዌል ማቲፕ ጉዳት ማስተናገዳቸው በዎልቭስ በተሸነፉበት የኤፍ ኤ ካፕ ውድድር አማካዩ ፋቢንዮ የመሃል ተከላካይ እንዲሆን አስገድዶት ነበር።

ሊቨርፑሎች በዚህ ሳምንት ብራይተንን አሸንፈው የፕሪምየርሊጉን መሪነት የሚያስጠብቁ አይመስለኝም ይላል ላውሮ።

ብራይተኖች ደግሞ በሜዳቸው ብዜ ጨዋታዎችን አቻ በመለያየት ነው የሚታወቁት። ሰለዚህም ጨዋታው አቻ በሆነ ውጤት እንደሚጠናቀቅ አስባለው ብሏል ላውሮ።

ላውሮ ግምት: 1-1

በርንሌይ ከፉልሃም

በርንሌዮች በኤፍ ኤ ካፕ ውድድርና በፕሪምየር ሊጉ ሶስት ጨዋታዎችን አሸንፈዋል። ከዚህ በተጨማሪ ይላል ላውሮ፤ በርንሌዮች የማሸነፍ ጥማታቸውና ጉልበታቸው በአስገራሚ ሁኔታ ጨምሯል።

ፉልሃም ከዚህ ጨዋታ ነጥብ ይዞ የሚወጣ አይመስልም።

የላውሮ ግምት: 2-0

13 አስደናቂ የፓስፖርት እውነታዎች

በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው?

ካርዲፍ ከሃደርስፊልድ

ሁለቱም ቡድኖች ከኤፍ ኤ ካፕ ውድድሩ ውጪ ስለሆኑ በፕሪምየር ሊጉ ለመቆየት የሚያደርጉትን ትግል ያጠናክራሉ ብዬ አስባለው ይላል ላውሮ።

''ስለዚህ የቅዳሜው ጨዋታ እጅግ አዝናኝ እንደሚሆን አልጠራጠርም።''

የላውሮ ግምት: 2-0

ክሪስታል ፓላስ ከዋትፎርድ

ክሪስታል ፓላሶች በመጨረሻም ወደ አቋማቸው እየተመለሱ ይመስላል። ማንቸስተር ሲቲዎችን ካሸነፉ ወዲህ ደግሞ ጥሩ መነቃቃት ይታይባቸዋል። ዋትፎርዶች ደግሞ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት እየተሰናቸው ይመስላል።

የላውሮ ግምት: 1-2

ሌስተር ሲቲ ከሳውዝሃምፕተን

ሌስተሮች በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ቀን ኤቨርተንን ማሸነፋቸው በደረጃ ሰንጠረዡ ሰባተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧቸዋል። ሳውዝሃምፕተኖች ደግሞ አስተማማኝ የሚባል አቋም ላይ አይደለም የሚገኙት።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport

ቼልሲ ከኒውካስ

የኒውካስትሉ አሰልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ አጣብቂኝ ውስጥ እየገቡ ይመስላል። በሊቨርፑል የደረሰባቸው አይነት ሽነፈት ግን በቼልሲ የሚደርስባቸው አይመስለኝም የሚለው ላውሮ፤ የማሸነፉን ግምት ለቼልሲ ሰጥቷል።

የላውረሮ ግምት: 2-0

ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች

ዕሁድ

ኤቨርተን ከበርንማውዝ

ሁለቱም ቡድኖች እስካሁን ጥሩ የሚባል ጨዋታ ማሳየት የከበዳቸው ሲሆን በደረጃ ሰንጠረዡም በተመሳሳይ 27 ነጥብ 11ኛ እና 12ኛ ላይ ተቀምተዋል።

ሁለቱን ቡድኖች ማወዳደር ካለብን ግን የበላይነቱን ለኤቨርተን እሰጣለው ብሏል ላውሮ።

የላውሮ ግምት: 2-1

Image copyright BBC Sport

ቶተንሃም ከማንቸስተር ዩናይትድ

ለአዲሱ ጊዜያዊ የማንቸስተር አሰልጣኝ ይሄኛው ጨዋታ ከእስካሁኖቹ ሁሉ በተለየ መልኩ ፈተና እነደሚሆንበት ይገመታል። የተለመደውን የማጥቃት አጨዋወት ይዞ ይመጣ ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።

በሳምንቱ በጉጉት በሚጠበቀው ይህ ጨዋታ ዩናይትዶች ብዙ ኳስ ይዘው የሚጫወቱ አይመስለኝም የሚለው ላውሮ ቶተንሃሞች ጨዋታውን ይቆጣጠሩታል ብሏል።

ቶተነሃሞች በዌምብሌይ ስታዲየም ተስማምቷቸው እየተጫወቱ ይመስላል።

የላውሮ ግምት: 2-1

ሰኞ

Image copyright BBC Sport

ማንቸስተር ሲቲ ከዎልቭስ

ማንቸስተር ሲቲዎች በኤፍ ኤ ካፕ ውድድር ሮተርሃም ላይ 9 ግቦችን ማስቆጠር የቻሉ ሲሆን በዚህኛውስ ጨዋታ ዎልቭስ ላይ ስንት ግብ እንደሚያስቆጥሩ መገመት ይከብደኛል ይላል ላውሮ። ምናልባትም 11 ሊሆን ይችላል ሲል ቀልድ መሰል አስተያየቱን ጣል አድርጓል።

ዎልቭሶች በደረጃ ሰንጠረዡ ዘጠነኛ ላይ ሲሆን የሚገኙት እስካሁን ብዙም የሚያስከፋ አጨዋወት አልነበራቸውም።

የላውሮ ግምት: 3-0