ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስድሳ በላይ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችን ያገኛሉ

አቶ ነብያት ጌታቸው

በሚቀጥለው ሰኞ ጥር 6ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች እና በዓለም ዙርያ በተለያዩ ሚሲዮኖች ኢትዮጵያን ከሚወክሉ ከስድሳ በላይ አምባሳደሮች እንደሚወያዩ ተገለፀ።

ውይይቱ በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን በተለይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እየተካሄደ ያለው የመዋቅር ማሻሻያ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ እንዲሁም ባለፉት አስር ወራት በውጭ ግንኙነት መስክ የተከናወኑ እርምጃዎች ይገመገማሉ ሲል ተሰናባቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ዛሬ ተናግረዋል።

በቅርቡ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አቶ መለስ ከአስር በላይ የአገር መሪዎች ባለፉት አስር ወራት ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን አስታውሰዋል።

"የመከላከያ ሰራዊትን እንቅስቃሴ የሚያግድ ስራ አንቀበልም" ዶ/ር ደብረፅዮን

ኢትዮጵያ በዲፕሎማቶቿ ላይ ሽግሽግና ለውጥ ልታደርግ ነው

ተሿሚው አምባሳደር ላለፉት ሁለት ዓመታት ያገለገሉበትን የቃል አቀባይነት የሥራ ኃላፊነት ለበርካታ ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ያገለገሉት አቶ ነብያት ጌታቸው ተረክበዋል።

በተያያዘ የኢትዮጵያ ቀን መርኃ ግብር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ከተማዋን በማስጎብኘት ይከበራልም ተብሏል።