የፖላንዷ ዳንስክ ከተማ ከንቲባ በስለት ተወግተው ሞቱ

Image copyright EPA

ኢትዮጵያ

• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተለያዩ ሃገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጋር በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ተወያዩ።

ዲፕሎማቶች የመንግስት ፖሊሲን የመተግበር፣ የሚመደቡበትን ሃገር ፖሊሲ የመገንዘብና በሃገራቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መብት የማስጠበቅ ግዴታ አለባቸው ብለዋል።

በምዕራብ ኦሮሚያ እና በቄለም ወለጋ ከአሥር በላይ ባንኮች ተዘረፉ

ሳይንቲስቱ በዘረኛ ንግግራቸው ማዕረጋቸውን ተቀሙ

ኬንያ

• ከአምስት ዓመት በፊት በኬንያዋ ዋና ከተማ ናይሮቢ ዌስትጌት የገበያ ማዕከል ውስጥ የሽበር ጥቃት ላደረሱ ሰዎች ከለላ ሰጥተዋል የተባሉ ሶስት ተጠርጠሪዎች ለፍርድ ቀረቡ።

በፈረንጆቹ 2013 በተሰነዘረውና ለአራት ቀናት በቆየው የአጋች ታጋች ሁኔታ 67 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

ናይጄሪያ

• የናይጄሪያው ዋና የፍትህ ሃላፊ ዋልተር ኦኖግኀን ንብረት በማሸሸ ወንጀል በቀረባበቸው ክስ ዘብጥያ ሊወርዱ ይችላሉ ተባለ።

ዋና ሃላፊው ዛሬ ጠዋት ፍርድ ቤት መቅረብ የነበረባቸው ቢሆንም መገኘት እንዳልቻሉ ተገልጿል።

ዚምባብዌ

• ዚምባቤያውያን በእጥፍ የጨመረውን የነዳጅ ዋጋ በመቃወም ትልቅ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።

ተቃውሞውም መልኩን ቀይሮ ወደ ብጥብጥ እነዳያድግ የፈራው ፖሊስ ደግሞ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሟል።

የሱዳን ተቃዋሚዎችን ባለመደገፋቸው ተቃውሞ የገጠማቸው ኢማም

"ጫትን ማገድ ፈፅሞ የሚቻል አይደለም" ዶ/ር ዘሪሁን መሃመድ

ሱዳን

• በሱዳን መንግስት ላይ እየተካሄደ ያለውን ተቃውሞ ባለመደገፋቸውና ባለመምራታቸው አንድ ኢማም ከመስጅድ ተባረሩ።

ባለፈው አርብ ዕለት ከስግደት በኋላ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ "አገዛዙ መውደቅ አለበት" የሚል ተቃውሞዎች ተሰምተዋል።

ኢራን

• በኢራኗ ዋና ከተማ ቴህራን አንድ አውሮፕላን ለማረፍ ሲሞክር ከግድግዳ ጋር ተጋጭቶ በደረሰ አደጋ 15 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።

አደጋው የተከሰተው በወቅቱ በነበረው ከባድ የአየር ንብረት ምክንያት እንደሆነ የሃገሪቱ መከላከያ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

አሜሪካ

• አሜሪካዊው ሳይንቲስት ዶ/ር ጄምስ ዋትሰን በቴሌቭዥን መሰናዶ ላይ ዘረኛ ንግግር ካደረጉ በኋላ ለሥራቸው የተሰጣቸውን የዕውቅና ማዕረግ ተነጠቁ።

በዘረ መል ምርምር የሚታወቁት የኖቤል ተሸላሚው ሳይንቲስት፤ የጥቁሮችና ነጮች የማሰላሰል ብቃት በዘረ መላቸው ይወሰናል የሚል ዘረኛ ንግግር አድርገው ነበር።

ፖላንድ

• የፖላንዷ ዳንስክ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ፓወል ኣዳሞዊክዝ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ በስለት ተወግተው ህይወታቸው አለፈ።

የ53 ዓመቱ ከንቲባ አምስት ሰአት የፈጀ ቀዶ ህክምና የተደረገላቸው ሲሆን አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በ500 መዥገሮች የተወረረው እባብ የደም ህዋስ ማነስ አጋጠመው

ካናዳ

• የካናዳ የአየር መቆጣጠሪያ መስሪያ ቤት ሰራተኞች የፌደራል መንግሰት ቢሮዎች ለሚሰሩ አሜሪካውያን እንደ ፒዛ ያሉ ምግቦችን መላክ ጀመሩ።

በአሜሪካ የፌደራል መስሪያ ቤቶች መዘጋት ጋር በተያያዘ 800 ሺ ሰራተኞች ቀጥተኛ ተጎጂዎች እንደሆኑም ተገልጿል።

ተያያዥ ርዕሶች