ዩቲውብ አደገኛ 'ፕራንክ' ሊያግድ ነው

ዩቲውብ አደገኛና አስደንጋጭ 'ፕራንክ' ሊያግድ ነው Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ዩቲውብ አደገኛና አስደንጋጭ 'ፕራንክ' ሊያግድ ነው

ዩቲውብ አደገኛና አስደንጋጭ የ 'ፕራንክ' ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ሊያግድ ነው። 'ፕራንክ' ፤ አንድ ሰው ሌላ ሰውን ለማሸበር ወይም ለማስደንገጥ በማሰብ ሆነ ተብሎ የሚፈጸም ተግባር ነው።

ዩቲውብ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በድረ ገጹ በስፋት የሚሰራጩ ሞትና የአካል ጉዳት ያስከተሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመቆጣጠር ነው።

ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ

ዩቲውብ "መሰል ቪድዮዎች በዩቲውብ ቦታ የላቸውም" የሚል መልዕክት አስተላልፏል።

ዩቲውብ ከቀድሞውም አደገኛ ይዘት ያላቸው መረጃዎችን ለመከላከል የወጣ ሕግ ቢኖረውም እየተከበረ አይደለም። ብዙ ጊዜ አደገኛ ይዘት ያላቸው ምስሎችን ከድረ ገጹ እንዲነሱ ተጠይቆ ለወራት ምላሽ አለመስጠቱም ተቋሙን ያስተቸዋል።

ዩቲውብ የበርካታ 'ፕራንኮች' መገኛ መሆኑ ይታወቃል። 'ፕራንኮች' ብዙ ሚሊዮን ተመልካችም የያገኛሉ። ሆኖም ዩቲውብ፤ የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በትጋት እሠራለሁ ብሏል።

ፌስቡክ የትራምፕን ክስ ውድቅ አደረገ

ፌስቡክ ግላዊ መረጃን አሳልፎ በመስጠት ተከሰሰ

"አስቂኝ የሚባል ቪድዮ መስመሩን አልፎ አደገኛ እንዳይሆን የምንከላለከልበት ፖሊሲ አለን" የሚል መልዕክት ከዩቲውብ ተላልፏል። ከዚህ በኋላ ሰዎች ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ማንኛውም አይነት 'ፕራንኮች' እንደማይስተናግዱም አስረግጠው ተናግረዋል።

አንድ ሰው በእውን አደጋ ውስጥ ሳይሆን፤ አደጋ ውስጥ እንዳለ በማስመሰል የሚሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የሚታገዱ ይሆናል። በተጨማሪም ህጻናትን የሚያስጨንቅና የሚያስፈራ ማንኛውም 'ፕራንክ' ስርጭቱ ይገታል ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች