ኮማንድ ፖስቱ በምዕራብ ኢትዮጵያ 835 ታጣቂዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ

የኦነግ ወታደሮች Image copyright Jonathan Alpeyrie

በምዕራብ ኢትዮጵያ ታጥቀው የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ ነበሩ ያላቸውን 835 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በዛሬው መግለጫው አስታውቋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመከላከል የተቋቋመው ይህ ኮማንድ ፖስት ከአካባቢው ፖሊስ ከሚሊሻና ከዕቃግምጃ ቤት ተዘርፈው የነበሩ በርካታ ዘመናዊና የቆዩ የጦር መሳሪያዎች፤ መኪኖችና የተለያዩ እቃዎችን መያዙን አስታውቋል።

ኦነግ ከመንግሥት ጋር ያደረኩት ስምምነት አልተከበረም አለ

"ጫትን ማገድ ፈፅሞ የሚቻል አይደለም" ዶ/ር ዘሪሁን መሃመድ

ሰላምን የማስፈን ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል፤ የሰላም እንቅፋት የሚሆኑ ግለሰቦችንም ህብረተሰቡ ለመንግሥትና ለኮማንድ ፖስቱ አስፈላጊውን ጥቆማ እንዲያደርግ ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል።

ከሰሞኑም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የግል ተቋማት ዝርፊያና የማቃጠል ሙከራዎችን በሚመለከት የተጋነነ መረጃ እየተሰጠ መሆኑን መግለጫው አትቶ ተዘረፉ የተባሉ ባንኮች ብዛት፣ የተዘረፈው የገንዘብ መጠንና የዘራፊዎቹን ማንነት በቀጣይ ለህዝቡ ግልፅ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ከሰሞኑ በምዕራብ ኦሮሚያ ላይ የአየር ጥቃት ተደርጓል በሚል የወጣው መረጃም ሐሰት እንደሆነ ገልፆ ሄሊኮፕተሮቹ በተለያዩ ቦታዎች የተሰማራውን የሰራዊት ክፍል ለማገልገል፣ አመች ባልሆኑና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እያገዙ እንደሆነ ጠቅሶ የሎጅስቲክ አቅርቦት ከመስጠት የዘለለ ለአየር ኃይል ውጊያ የሚያበቃ ነገር እንደሌለ አስታውቋል።

"የአየር ኃይሉ በሂሊኮፕተር ሆነ በአውሮፕላን ተኩስ እንደከፈተ ነው የሚራገበው። ለዚህ የሚያበቃ የጠላት ኃይል ይቅርና ከመከላከያ አነስተኛ የእግረኛ ኃይል ጋር ፊት ለፊት የሚገጥም ፀረ-ሠላም ኃይል አልገጠመንም" ብሏል

"ትጥቅ ትግል ወደ ዴሞክራሲ አያመራም" አቶ ሌንጮ ለታ

ኮማንድ ፖስቱ ጨምሮ ማህበረሰቡ የፀጥታ ኃይሉን በቅርበት እየደገፈ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በኮማንድ ፖስቱ በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎችን በተመለከተ ከፌደራል የተላኩ አቃቢ ህግ እና መርማሪ ባለሙያዎች ወደ ቦታው እንደሄዱና ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችላቸውን የቅድመ ሁኔታ ያጠናቀቁ በመሆኑ በቅርብ ጊዜ ስራ እንደሚጀምሩ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ተያያዥ ርዕሶች