እንዴት የእንቁላል ምስል ኢንስታግራም ላይ 46 ሚሊዮን 'ላይክ' አገኘ ?

እንቁላሉና ኬሊ ጄነር Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ እንቁላሉና ኬሊ ጄነር

እንደው የኢንተርኔት ነገር ድንቅ አይሎትም?

ከ46 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ኢንስታግራም ላይ የተለጠፈ የእንቁላል ምስልን ወደውታል ወይም 'ላይክ' አድርገውታል።

የዚህ እንቁላል ባለቤት ማን እንደሆነ፣ ፎቶው መቼ እንደተነሳ፣ እንቁላሉ ጫጩት ይሁን ወይም ተጠብሶ አሊያም ተቀቅሎ ይበላ የሚቃወቅ ነገር የለም። የሚታወቀው ከ46 ሚሊዮን በላይ ሰዎች 'ላይክ' እንዳደረጉት ብቻ ነው።

ከሽብር ጥቃቱ በኋላ ምን ተከሰተ?

"በብሔር ግጭት ወደ 900 ሰዎች ገደማ ተገድለዋል"

ኮማንድ ፖስቱ በምዕራብ ኢትዮጵያ 835 ታጣቂዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ

የእንቁላሉ ፎቶ ከመለጠፉ በፊት፤ የቴሌቪዥን መሰናዶ አዘጋጇ ኬሊ ጄነር አምና የተወለደ ልጇን ያስተዋወቀችበት ዜና 18 ሚሊዮን 'ላይክ' በመሰብሰብ ሪከርዱን ይዞ የነበረው።

ከቀናት በፊት ማለትም ታህሳስ 26፤ ማንነቱ ያልተወቀ የኢንስታግራም ተጠቃሚ፤ ዎርልድ_ሪኮርድ_ኤግ ("world_record_egg") የሚል የኢንስታግራም ገጽ በመፍጠር የእንቁላሉን ፎቶ በመለጠፍ 46.8 ሚሊዮን 'ላይክ' ማግኘት ችሏል።

ከእንቁላሉ ጋር አብሮ የተለጠፈው ጽሁፍ ''በኢንስታግራም ገጽ ላይ ብዙ 'ላይክ' በማስገኘት የዓለም ሪኮርድን አብረን እናስመዝግብ'' ይላል።

እንደተባለውም ሆነ። ከሁለት ቀናት በፊት ሪኮርዱ ተሰብሯል።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የኢንስታግራም ገጹን ማን እንደሚያስተዳድረው አይታወቅም

ሪኮርዱን የተቀማችው ኬሊ ጄነር፤ እንቁላል ስትሰብር የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ''ይህን ደቃቃ እንቁላል አንሳው/ሺው'' ከሚል ጽሁፍ ጋር በኢንስታግራም ገጿ ላይ ለቃለች።

ኬሊ ጄነር በኢንስታግራም ገጿ ላይ በስፖንሰር ለምትለጥፈው አንድ ማስታወቂያ አንድ ሚሊዮን ዶላር ታስከፍላለች።