አርሰናል እና ቼልሲ ተፋጠዋል

የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት Image copyright Mark Leech/Offside

23ኛው የፕሪሚየር ሊጉ ሳምንት አርሰናል እና ቼልሲን አፋጧል።

ይህ ጨዋታ የመጀመሪያዎቹ አራት ውስጥ ሆኖ ለመጨረስ ለሚደረገው ተጋድሎ ወሳኝነት አለው ይላል ላውሮ። ጨዋታውን ማን ይረታል?

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ፤ ሰማያዊዎቹ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ አርሰናልን አስተናግደው ማሸነፋቸውን አስታውሶ፤ መድፈኞቹ በሜዳቸው በቀላሉ እጃቸውን አይሰጡም ይላል።

ላውሮ አርሰናል ከቶተንሃም ጋር ያደረገውን ጨዋታ ዋቢ በማድረግ አርሰናሎች እንዲህ ባሉ ትልልቅ ግጥሚያዎች ላይ ጥሩ አቋም እንደሚያሳዩ ያስረዳል።

ከሽብር ጥቃቱ ጋር በተገናኘ 9 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የላውሮ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተው ይቀርባል

ዎልቭስ ከ ሌስተር

ሌሰተሮች ባሳለፍነው ሳምንት በሳውዝሃምተን ተሸንፈዋል። በአሰልጣኙ ደስተኛ ያልሆኑ የቀበሮዎቹ ደጋፊዎች በርካቶች ናቸው።

አፍሪካ ህብረት የኮንጎ ምርጫ ውጤት እንዲዘገይ ጠየቀ

በበዓል ሰሞን ጨዋታዎች፤ ሌስተሮች ማንችሰተር ሲቲን እና ቼልሲን ማሸነፍ ችለው የነበረ ቢሆንም፤ ዎልቭስን ግን ማሸነፍ አይችሉም ይላል ላውሮ።

የላውሮ ግምት፡ ዎልቭስ 2 - 0 ሌስተር

ርንማውዝ ከ ዌስት ሃም

ዌስት ሃም ቅዳሜ ዕለት አርሰናልን በማሽነፍ ትለቅ ድል ማስመዝገብ ችለዋል። በርንማውዝ በበኩላቸው በኤቨርተን ተሸንፈዋል። በርንማውዞች በቅርብ ካደረጓቸው 12 ጨዋታዎች በዘጠኙ ተሸንፈዋል ማለት ነው። ይሁን እንጂ ላውሮ በርንማውዞች በዌስት ሃሞች ላይ የተሻለ ሪከርድ እንዳላቸው ይናገራል።

የላውሮ ግምት፡ ብርንዝማውዝ 2 - ዌስት ሃም 1

ሊቨርፑል ከ ክርስታል ፓላስ

ላውሮ ሊቨርፑሎች ይህን ጨዋታ የማያሸንፉበት ምንም ምክንያት አይታየኝም ይላል።

"በብሔር ግጭት ወደ 900 ሰዎች ገደማ ተገድለዋል"

የላውሮ ግምት ሊቨርፑል 2 - 0 ክርስታል ፓላስ

ማንችሰተር ዩናይትድ ከ ብራይተን

ብራይተኖች ባለፈው ሳምንት ከሊቨርፑል በዚህኛው ዙር ደግሞ ከማንችሰተር ዩናይትድ ጋር እንደመገናኘታቸው ይህ ለእነሱ ቀላል ጊዜ አይደለም።

ብራይተኞች ከማንስተር ዩናይትድ የሚያገኙት ነጥብ እንደማይኖር ባውቅም፤ ለቀያይ ሰይጣኖች ፈተና እንደሚሆኑባቸው እርግጠኛ ነኝ ይላል ላውሮ።

የላውሮ ግምት ማንችስተር ዩናይትድ 3 - 0 ብራይተን

ኒውካስትል ከ ካርዲፍ

ኒውካስትል እና ካርዲፍ ከመጨረሻዎቹ አራት ቡደኖች መካከል ይገኙበታል። ላውሮ የጨዋታው ውጤት ምንም ይሁን ምን በወራጅ ቀጠናው አካባቢ በሚገኙ ቡድኖች ደረጃ ላይ ለውጥ አያመጣም ይላል።

የላውሮ ግምት፡ ኒውካስትል 2 - 0 ካርዲፍ

ሳውዝሃምፕተን ከኤቨርተን

ሁለቱም ቡድኖች በቀደመ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ጥሩ እንቅስቃሴዎችን አሳይተዋል ይላል። በማርኮ ሲልቫ የሚመራው ኤቨርተን አንድ የሆነ የጎደለው ነገር እንዳለ ይሰማኛል ይላል ላውሮ።

በመከላከሉ ረገድ የተሻሉ ሆነው መገኘት ነበረባቸው የሚለው ላውሮ፤ ሪቻርልሰን እና ሲጉርድሰን ኳስ እየደረሳቸው ስላልሆነ ጨዋታ ተቆጣጥሮ መጫወት አልቻሉም ይላል ላውሮ።

የላውሮ ግምት፡ ሳውዝሃምፕተን 1 - 1 ኤቨርተን

ዋትፎርድ ከ በርንሌይ

ዋትፎርዶች ጥሩ ናቸው ሲባል ይወርዳሉ። ተዳክመዋል ሲባል ደግሞ አስገራሚ አቋም ያሳያሉ የሚለው ላውሮ፤ ይህን ጨዋታ እንግዳዎቹ በርንሌዎች እንደሚያሸንፉ ይገምታል። ፉልሃምን ማሸነፍ የቻሉት በርንሌዎች ይህን ጨዋታ በድል ያጠናቅቃሉ ይላል።

የላውሮ ግምት፡ ዋትፎርድ 0 - 1 በርንሌይ

Image copyright BBC Sport

አርሰናል ከቼልሲ

አርሰናሎች የተከላካይ መስመራቸውን ካላጠናከሩ በስተቀር አሁንም የመጀመሪያዎቹ አራት ውስጥ ሆኖ መጨረስ ህልም ሆኖ ነው የሚቀረው ይላል።

አርሰናል ይህን ጨዋታ የማያሸነፍ ከሆነ በማንችሰተር የመቀደም ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

የላውሮ ግምት፡ አርሰናል 2 - 1 ቼልሲ

እሁድ

ሃደርስፊልድ ከ ማንችስር ሲቲ

ማንችስተር ሲቲዎች ከዎልቨስ ጋር የነበራቸው ጨዋታ ከመቅለሉ የተነሳ ሲቲዎች ልምምድ እያደረጉ ያሉ ነበር የሚመስሉት ይላል ላውሮ። ፔፕ ጋርዲዮላ ይህ ጨዋታ የሚከብደው አይመስለኝም ሲልም ያክላል።

የላውሮ ግምት፡ ሃደርስፊልድ 0 - 2 ማንችስተር ሲቲ

ፉልሃም ከ ቶተንሃም

ቶተንሃሞች በደጋፊዎቻቸው ፊት በማንችስተር ዩናይትድ ከመሸነፋቸው በተጨማሪ ሃሪ ኬን እና ሙሳ ሲሶኮ ተጎድተዋል።

ከሁለቱ በተጨማሪ ሰን የእስያ ካፕ ውድድር ላይ እንደመገኘቱ ቶተንሃም ችግር ውእጥ እንዳለ ይሰማኛል ይላል ላውሮ። ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን ቶተንሃሞች ፉልሃምን ማሸነፍ ይችላሉ።

የላውሮ ግምት፡ ፉልሃም 0 - 2 ቶተንሃም

ተያያዥ ርዕሶች