ግብጽ የሴቶችን የወሲብ ፍላጎት ለማሳደግ 'የሴቶች ቫያግራን' ለገበያ ማቅረብ ጀመረች

Flibanserin pill sold in Egypt
አጭር የምስል መግለጫ ግብጽ የሴቶችን የወሲብ ፍላጎት ለማሳደግ በማሰብ 'የሴቶች ቫያግራን' በማምረት እና ለገብያ በማቅረብ የመጀመሪያዋ አረብ ሃገር ሆነች።

ግብጽ የሴቶችን የወሲብ ፍላጎት ለማሳደግ በማሰብ 'የሴቶች ቫያግራን' በማምረት እና ለገብያ በማቅረብ የመጀመሪያዋ አረብ ሃገር ሆነች። ወግ አጥባቂ በሆነችዋ ሃገረ ግብጽ፤ የምርቱ ፈላጊዎች ቁጥር ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል የሚሉ በርካቶች ቢሆንም አምራቾች ግን ገበያው ደርቶልናል እያሉ ነው።

''እንቅልፍ እንቅልፍ አለኝ፤ ልቤም በፍጥነት ይመታ ነበረ።'' ግብጻዊቷ ላይላ ይህን ያለችው ''የሴቶች ቫያግራ'' ከወሰደች በኋላ ነበር።

የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው?

ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው?

'ፈሊባንሴሪን' የተሰኘው ኬሚካል ለአሜሪካ ገብያ የቀረበው ከሶስት ዓመታት በፊት ነበር። በቅርቡም አንድ የግብጽ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ ምርቱን አምርቶ ለገበያ ማቅረብ ጀምሯል።

ላይላ- ስሟ የተቀየር- ወግ አጥባቂ በ30ዎቹ አጋማሽ ላይ የምትገኝ የቤት እመቤት ናት። ላይላ በግብጽ ስለ ግብረ ስጋ ግንኙትም ሆነ ስለ ወሲብ ፍላጎት በግልጽ ማውራት እጅግ ሲባዛ ነውር ነው ትላለች።

ምንም አይነት የጤና እክል የሌለባት ለይላ ከ10 ዓመታት የትዳር ቆይታ በኋላ ይህን መድሃኒት ለመጠቀም ፍላጎቱ አደረብኝ ትላለች።

ላይላ መድሃኒቱን ያለ ሃኪም የመድሃኒት ማዘዣ ከመድሃኒት ቤት መግዛቷን ታስረዳለች።

''ፋርማሲስቱ ለጥቂት ሳምንታት አንድ እንክብል ከመኝታ በፊት እንድወስድ ነገርኝ። ምንም አይነት የጎንዮሽ ችግሮችን እንደማያስከትል ጨምሮ ነግሮኛል'' ትላለች። ''እኔ እና ባለቤቴ ምን ሊከሰት እንደሚችል ማየት ፈለግን። አንዴ ሞከርኩት። ከአሁን በኋላ ግን ዳግመኛ አልሞክረውም።''

በግብጽ የፍቺ መጠን እያሻቀበ ነው። ለፍቺ ቁጥር መጨመር እንደ ምክንያት እየቀረቡ ካሉ ምክንያቶች መካከል ደግሞ አንዱ በጥንዶች መካከል በወሲብ አለመጣጣም ነው።

የሴቶች ቫያግራ አምራች ኩባንያው እንደሚለው ከሆነ ከአስር የግብጽ ሴቶች ሶስቱ ለወሲብ አነስተኛ ፍላጎት ያሳያሉ። ኩባንያው በግብጽ እንዲህ ባሉ ጉዳዮች ላይ ትክክለኛውን ቁጥር ማወቅ አዳጋች መሆኑን በመግለጽ ይህ አሃዝ ግምታዊ መሆኑን ያሳስባል።

አጭር የምስል መግለጫ መድሃኒቱን እየሸጡ የሚገኙ ፋርማሲዎች ከአሁኑ ግበያው እየደራላቸው እንደሆነ ይናገራሉ።

ለወሲብ አነስተኛ ፍላጎት ያላቸው ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ በሆነባት ሃገር ''ይህ አይነት ህክምና እጅግ ወሳኝ ነው'' በማለት የኩባንያው ተወካይ አሽራፍ አል ማራጋይ ይናገራሉ።

አሽራፍ አል ማራጋይ መድሃኒቱ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደማያስከትል እና ውጤታማ እንደሆነ በመግለጽ የድብርት እና የድካም ስሜቶች ከጊዜ በኋላ እንደሚጠፉ ይናገራሉ። የመድሃኒቱ አምራች ኩባንያ ይህን ይበሉ እንጂ በርካታ ፋርማሲስቶች እና ሃኪሞች በሃሳባቸው አይስማሙም።

በጉዳዮ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ የፋርማሲ ባለሙያ እንደሚሉት ከሆነ፤ እንክብሉ ለአነስተኛ የደም ግፊት ሊዳርግ ይችላል። የልብ እና የጉብት ችግር ያለባቸው ሴቶች ላይም ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ይላሉ።

በግብጽ መዲና ካይሮ የፋርማሲ ባለሙያ የሆኑት ሙራድ ሳዲቅ መድሃኒቱን ለሚገዙ ደንበኞቻቸው እንክብሉ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ቢያስረዱም ''ሰዎች ግን መድሃኒቱን ለመግዛት ይገዳደራሉ'' ይላሉ።

''በቀን ቢያንስ 10 ሰዎች መድሃኒቱን ይገዛሉ። በርካቶቹ ደግሞ ወንዶች ናቸው። በመድሃኒት ቤቶች ውስጥ ሴቶች መድሃኒቱን መጠየቅ ያፍራሉ።''

ኬንያዊው በኮንዶም ምክንያት መንግሥትን ከሰሰ

ስለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚነገሩ 8 የተሳሳቱ አመለካከቶች

'ሁሉም ነገር አእምሯችን ውስጥ ነው'

በሙራድ ሳዲቅ መድሃኒት ቤት ውስጥ የሴቶች ቫያግራ ''ሃምራዊው እንክብል'' በማለት የሚያስተቃውቅ ምስል ይታያል። በግብጽ ለወንዶች ታስቦ የሚሰራው ቫያግራ ''ሰማያዊው አንእክብል'' ተብሎ በግብጻዊያን ዘንድ ይጠራል።

የአንክብሉ አምራች ''የሴቶች ቫያግራ'' የሚለው ሐረግ ትክክል አይደለም ይላሉ። የአምራች ኩባንያው አምራች አሽራፍ አል ማራጋይ ይህን ስያሜ ይዞ የመጡት መገናኛ ብዚሃን እንጂ እኛ አይደለንም ይላሉ።

ለወንዶች ታስቦ የሚሰራው እንክብል ወደ ብልት የሚሄደወን የደም ዝውውር በማሻሻል የብልት አለመቆም ችግርን ይቀርፋል፤ ለሴቶች ታስቦ የተፈበረከው 'ፈሊባንሴሪን' ደግሞ በአእምሮ ውስጥ የንጥረ ነገሮችን ውህድ በማመጣጠን የወሲብ ስሜትን ከፍ ያደርጋል።

አጭር የምስል መግለጫ 'ፈሊባንሴሪን' በአእምሮ ውስጥ የንጥረ ነገሮችን ውህድ በማመጣጠን የወሲብ ስሜትን ከፍ ያደርጋል።

'' 'የሴቶች ቫያግራ' አሳሳች ቃል ነው'' ትላለች የወሲብ አማካሪዋ ሄዳ ቆትባ። የወሲብ አማካሪዋ እንደምትለው በእንክብሉ ላይ እምነት ስላላደረባት ታካሚዎቿ እንክብሉን እንዲጠቀሙ አትመክርም።

''አካላዊ ወይም አእምሯዊ ችግር እያጋጠሟት ላለች ሴት፤ ይህ እንክብል በምንም አይነት ሁኔታ መፍትሄ ለሆን አይችልም'' ትላላች ሄዳ ቆትባ።

''ለሴት ልጅ ወሲብ ስሜታዊ ሂደት ነው። ሁሉም ነገር የሚጀምረው አእምሮ ውስጥ ነው። አንዲት ሴት ባሏ እንክብካቤ የማያደርግላት ከሆነ በወሲብ ሊጣጣሙ አይችሉም። ይህን አይነት ችግር ደግሞ መድሃኒት አይቀርፈውም።''

የወሲብ አማካሪዋ እንደምትለው ከሆነ ይህ እንክብል ከሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳት ጋር አንጻር መጥፎ ጎኑ ያመዝናል በማለት ታስጠነቅቃለች።

በርካታ ግብጻውያን ሴቶች አሁንም ቢሆን ስለ ወሲብ ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በግልጽ አያወሩም።

ለይላም ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በወሲብ ያመይጣጣሙ በርካታ ባለትዳር ሴቶችን ታውቃለች።

ላይላ ''አፍቃሪ እና ተንከባካቢ የሆነ ባለቤትሽ በወሲብ ደካማ ቢሆን የሚያስፈልገውን የህክምና ድጋፍ እንዲያገኝ ትረጂዋለሽ። በሌላ በኩል ደግሞ ተንከባካቢ እና አፍቃሪ ያልሆነ ባል አልጋ ላይ ምንም ያክል ጎበዝ ቢሆን እንኳ ከእሱ ጋር የሚኖርሽ የወሲብ ፍላጎት እየቀነሰ ይሄዳል። ወንዶች ግን ይህ የሚገባቸው አይመስለኝም'' ብላለች።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ