መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች

ስልክ የሚጠቀም ጎሬላ Image copyright Getty Images

የሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ብዙ ርቀት ቢጓዝም የውጦቹ ፍጥነት እጅግ ቀርፋፋ ሆኖዋል።

የሰው ልጅ ጥንት ያደርጓቸው እና ይጠቀሙባቸው የነበሩ ነገሮች ከጊዜ ብዛት እየጠፉ መጥተዋል። እነዚህ በዝግመተ ለውጥ ውስጥ የሚጠፉ መገለጫዎች አብረውን ቢኖሩም እንኳን የማስተዋል እድላችን ጠባብ ነው።

''ሰውነታችን የተፈጥሮ ታሪክ ሙዚየም ነው'' ይላሉ የዝግመተ ለውጥ አንትሮፖሎጂስቷ ዶርሳ አሚር።

13 አስደናቂ የፓስፖርት እውነታዎች

የአስር ደቂቃ እንቅስቃሴ የማስታወስ ችሎታን እንዴት ይጨምራል?

ታዲያ እኚህ የሰውነት አካላትና ባህሪያት ለምን አብረውን ይቆያሉ? ምክንያቱም ዝግመተ ለውጥ በአንድ ጊዜ ለውጡን የሚያሳየን ነገር ስላልሆነ ነው።

የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት አንዳንድ የሰውነታችን አካላት በጊዜ ብዛት መጀመሪያ ከሚሰጡት አገልግሎት የተለየ አይነት ጥቅም ሊኖራቸው ይችላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰው ልጅ መጠቀም ያቆማቸው ስድስት ክፍሎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።

1. ከመዳፋችን ስር ያሉ ስስ አጥንቶች

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ይህ የሰውነት ክፍል ለቀደምት የሰው ልጆች ፍጡር ዛፍ ላይ መንጠላጠል የሚያስችላቸው ነበረ።

እስቲ ይህን ይሞክሩት፤ በአውራ ጣትዎ የውስጠኛ ክፍል ትንሿን ጣቶን ይንኩ። ልክ አውራ ጣትዎ ትንሿን ጣት ሲነካ ከመዳፍዎ ስር ያሉ ለስላሳ አጥንቶች ጎላ ብለው ይታያሉ። ይህ ግን ለሁሉም ሰው አይሰራም።

በቅርቡ በተደረጉ ጥናቶች መሰረት ከዓለም ህዝብ 18 በመቶ የሚሆነው እነዚህ ስስ አጥንቶት የሉትም። ስስ አጥንቶቹ ባይኖሮዎት አይጨነቁ። አጥንቶቹ ኖሩም አልኖሩም የሚያጎድሉት ነገር የለም።

ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች

በሳይንሱ መሰረት ይህ የሰውነት አካል በዝግመተ ለውጥ ሂደት ውስጥ ጥቅሙን አጥቷል አልያም ጭራሹን ጠፍቷል ማለት ነው። ይህ የሰውነት ክፍል ለቀደምት የሰው ልጆች ፍጡር ዛፍ ላይ መንጠላጠል የሚያስችላቸው ነበረ። ዋነኛ ጥቅሙም የዛፍ ቅርንጫፎችን ቆንጥጦ ለመያዝ ነው።

2. አበጥ ያለው የጆሮ ክፍል (The Darwin's tubercle)

Image copyright Getty Images

"ጆሮዎትን ማንቀሳቀስ ከቻሉ ለዝግመተ ለውጥ ሂደት ማሳያ ነዎት ማለት ነው'' ይላሉ ዶርሳ አሚር ዝግመተ ለውጥ ለምን እውነት ሆነ በሚለው መጽሃፋቸው።

ዶርስ አሚር ከራስ ቅላችን ስር ስለሚገኙ ሶስት ጡንቻዎች ሲናገሩ በመጸሃዳቸው ያና ያሉት።

ጆሮዎትን ማንቀሳቀስ ይችላሉ?

ማንቀሳቀስ ከቻሉ የዝግመተ ለውጥ ሂደትን ሙሉ በሙሉ አልጨረሱም እንደማለት ሊሆን ይችላል ይላሉ ዶርሳ አሚር። መረሳት የሌለበት ነገር አሁን እየኖርነው ባለነው አይነት ህይወት ይህ የጆሯችን ክፍል ምንም ጥቅም እንደሌለው ነው።

እንደ ድመትና ፈረስ ያሉ እንስሳት ጆሯቸውን በማንቀሳቀስ ጠላቶቻቸውን ለመለየትና ልጆቻቸውን ለመፈለግ ይጠቀማሉ።

ቀብሩን አዘጋጅቶ ራሱን ያጠፋው አርሶ አደር

3. የጭራ አጥንት

Image copyright Getty Images

ዶርሳ አሚር እንደሚሉት ይህ የጭራ አጥንት በመባል የሚታወቀው የሰውነታችን ክፍል ዋነኛው የዝግመተ ለውጥ ማሳያ ነው።

''ጭራዎቻችን በጊዜ ብዛት መጥፋታቸውን የሚያሳይ ምልክት ሲሆን ዛፎች ላይ ስንጠላጠል እንዳንወድቅ እና ሚዛናችንን እንድንጠብቅ የሚረዳን የሰውነት ክፍል ነበር።''

የዝግመተ ለውጥ ባለሙያዎች እንደሚሉት የሰው ልጅ ከዛፍ ዛፍ እየተንቀሳቀሰና ፍራፍሬዎችን እየለቀመ በሚኖር ጊዜ ጭራዎቹ ከፍተኛ ጥቅም ነበራቸው። አሁን ላይ ግን ጭራዎቹ ጠፍተው ርዝራዥ አጥንቶች ብቻ ነው የቀሩት።

4. ሶስተኛው የአይን ሽፋን

Image copyright Getty Images

በምስሉ ላይ በቀስት የተመለከተውና ሮዝማ ቀለም ያለው የአይን ከፍል ይታዮታል? በዝግመተ ለውጥ ሂደት ውስጥ ከጥቅም ውጪ የሆነ ሶስተኛ የአይን ሽፋን ነው።

ይህ ሶስተኛ የአይን ሽፋን ከላይና ከታች ካሉት የአይን ሽፋኖች በተለየ መልኩ ወደ ጎን ነው የሚከፈተውና የሚዘረጋው።

ነገር ግን ጥቅም ላይ ሲውል መቼም ልናየው አንችልም። ወፎችና ድመቶች ግን አሁን ይጠቀሙበታል።

ጣልያን አፍሪካን በተመለከተ የሰጠችው አስተያየት ፈረንሳይን አስቆጣ

5. የቆዳ መወጣጠር (መነፋፋት)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ድመት ከውሻ ስትፋጠጥ ሰውነቷን እንደምትወጣጥረው ሁሉ የሰው ልጆችም ሲበርዳቸውና ሲደነግጡ ይህንን ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይችሉ ነበር።

ድመቶች ከውሻ ጋር ሲፋጠጡ ሰውነታቸውን እንዴት እንደሚወጣጥሩት አስተውለው ያውቃሉ?

የሰው ልጆችም ሲበርዳቸውና ሲደነግጡ ይህንን ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይችሉ ነበር። ሳይንቲስቶች ይህንን ተግባር ' ፒሎሬክሽን ሪፍሌክስ' በማለት ይጠሩታል።

ስንደነግጥና ሲበርደን ብቻም አይደለም ይህንን የምናደርገው። ሊያጠቁን የሚመጡ እንስሳትን ለማስፈራራትና ትልቅ መስሎ ለመታየትም እንጠቀምበት ነበር ይላሉ ባለሙያዎቹ።

የሰው ልጅ ከጊዜ ብዛት የሰውነቱን ጸጉሮች መሸፈን ሲጀምር ይህ ተግባር እየቀነሰና ጥቅም አልባ እየሆነ መጣ ማለት ነው።

6. የማንቆጣጠራች እንቅስቃሴዎች

Image copyright Getty Images

በተለየ መልኩ አዲስ የተወለዱ እንስሳት እናቶቻቸው ጀርባ ላይ በሚንጠለጠሉበት ወቅት ወደታች እንዳይወድቁ ከቁጥጥራቸው ውጪ በሆነ መልኩ የእናቶቻቸውን ጀርባ ጥብቅ አድርገው ይይዛሉ።

አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች

ምንም እንኳን የሰው ልጆች ይህንን ተፈጥሮአዊ ችሎታ ከጊዜ ወደጊዜ እየተዉት ቢመጡም አዲስ የተወለዱ ህጻናት የእናቶቻቸውንና የማንኛውንም ሰው እጅ ጥብቅ አድርገው የመያዝ ባህሪ ያሳያሉ።

ይህ የሚሆነው ደግሞ ተፈጥሮአዊውና ከቁትጥራቸው ውጪ የሆነው ሰዋዊ ባህሪ ስለሚያስገድዳቸው ነው።

እያደጉ ሲመጡ ግን ለእንደዚህ አይነቱ ከቁጥጥር ውጪ ለሆነ ባህሪ ተገዢነታቸው እየቀነሰ ይመጣል።