ሱዳን ሁለት የውጪ ሃገር ጋዜጠኞችን አገደች

የሱዳን ተቃውሞ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የሱዳን ተቃውሞ ስድሰተኛ ሳምንቱን ይዟል

የሱዳን ባለስልጣናት ለስድስት ሳምንታት የቆየውን የተቃውሞ ሰልፍ ሲዘግቡ የነበሩ ሁለት የውጪ ሃገር ጋዜጠኞችን የስራ ፈቃድ ሰርዘዋል።

'አል አረቢያ' ለተባለ የሳዑዲ አረቢያ የዜና ተቋምና ለቱርኩ አናዶሉ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ናቸው በሱዳን መንግሥት የስራ ፈቃዳቸውን የተነጠቁት።

ባለስልጣናቱ የጋዜጠኞቹን ሁኔታ ለማጣራት ነው ከማለት የዘለለ ተጨማሪ መረጃ በጉዳዩ ላይ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ቀብሩን አዘጋጅቶ ራሱን ያጠፋው አርሶ አደር

'የሴቶች ቫያግራ' በአፍሪካዊቷ ሃገር

ባለፉት አስር ዓመታት ያልተቀየሩ እውነታዎች

ለጋዜጠኞች የስራ ፈቃድ የሚሰጠው የሱዳኑ የውጭ መረጃ ካውንስል እንዳስታወቀው ማጣራቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የጋዜጠኞቹ የስራ ፈቃድ ታግዶ ይቆያል።

በሱዳን ባለው ያልተረጋጋ ኢኮኖሚያዊ ስርአት ምክንያት ባለፈው ወር የተጀመረው ተቃውሞ አሁን መልኩን ቀይሮ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽርን ከስልጣን ማስወገድ ላይ ትኩረቱን አድርጓል።

የተረጋጋጠ ቁጥር እስካሁን ባይገኝም መንግስት ከሰልፉ ጋር በተያያዘ 26 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ሲል፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ግን የሟቾች ቁጥር ከ40 ይበልጣል እያሉ ነው።