ብቻቸውን ምግብ የሚመገቡ ሴቶች ለምን ትኩረት ይስባሉ

ብቻዋን ያለች ሴት A woman sits alone with a drink Image copyright Getty Images

ስለሴቶች መብትና እኩልነት ብዙ ነገሮች በሚባሉበትና ተግባራዊ በሚደረጉበት ዘመን አንዲት ሴት ብቻዋን ሬስቶራንት ውስጥ መቀመጥ ብዙም የሚያስገርም ላይመስል ይችላል።

ነገር ግን በአብዛኛዎቹ የዓለማችን ክፍሎች ያደጉትንም ጨምሮ አንዲት ሴት ብቻዋን ምግብ አዝዛ ስትመገብ አልያም መጠጥ ስትጠጣ መመልከት ብዙዎችን ያስገርማል። አንዳንዴም የተለየ ትርጉም ሊሰጠው ይችላል።

ታዋቂዋ ክለመንቲን ክሮውፎርድ በአሜሪካዋ ኒውዯርክ ከተማ ነዋሪ ነች። በጽሁፏ እንደገለጸችው በጣም በምትወደው የማንሃተን ሬስቶራንት ውስጥ ብቻዋን መቀመጥ እንደማትችል ተነግሯታል። በመጀመሪያ መልእክቱ ስላልገባኝ ግራ ገብቶኝ ነበር ትላለች።

ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ?

በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት

''ይባስ ብሎም ከእኔ በኋላ ለመጡ ወንድ ደንበኞች ወንበር ይመቻችላቸዋል፤ ትእዛዛቸውንም ወዲያው ይቀበላሉ።''

በሁኔታው ግራ የተጋባችው ክለመንቲን ምን አጥፍቼ ነው ብላ ስትጠይቅ የተሰጣት መልስ ያልጠበቀችው ነበር። እዚህ ሬስቶራንት ውስጥ ሴተኛ አዳሪዎችን እንዳናስተናግድ ትእዛዝ ተሰጥቶናል ነበር ያገኘችው መልስ።

''ብቻዬን በመሄዴና ዘንጬ ስለነበረ ሁሉም ሰው ያሰበው ሴተኛ አዳሪ እንደሆንኩ ነው።''

ምንም እንኳን ለብዙ ዓመታት ደንበኛ ብሆንም፤ ምንም እንኳን ጥሩ የሚባል ገቢ ያለኝ ሴት ብሆንም፤ ብቻዬን ከመጣሁ ትርጉሙ ሌላ መሆኑ እጅግ ያሳዝናል ትላለች።

Image copyright Getty Images

አንዲት ሴት ብቻዋን ወጥታ መዝናኛ ቤት ጊዜ ማሳለፍ አሁንም እጅግ ፈታኝ ነው። ነገር ብዙ ሴቶች ይህንን ፈተና ለመቋቋምና አካባቢያቸውን ለመርሳት መጽሃፍ ማንበብና ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ ጊዜ ማሳለፍ ያዘወትራሉ።

ክለመንቲን ይህንን አጋጣሚዋን በጽሁፍ ካሰፈረችው ወዲህ ብዙ የኒውዮርክና ሌሎች ትልልቅ ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ሴቶች ተመሳሳይ ነገር እንዳጋጠማቸው ጽፈዋል።

ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ?

በሬስቶራንቶችና በመዝናና ስፍራዎች የሚታየው የተሳሳተ አመለካከት ሴቶች ምን ያክል ፈተናዎችን እንደሚያልፉ ማሳያ ከመሆኑ ባለፈ በቤት ውስጥ ደግሞ ከዚህም የባሱ ነገሮችን እንደሚጋፈጡ መገንዘብ ይገባናል ትላለች ክለመንቲን።

''አንዲት ሴት ብቻዋን ምግብ አዝዛ መመገብ ከቻለች እንደ ጀግና ነው የምትቆጠረው። ይሄ እስከመቼ ነው የሚቀጥለው?''

Image copyright Gloria Atanmo

ሌላናዋ በዚህ ጉዳይ ላይ ታሪኳን ያካፈለችው ለአምስት ዓመታት ዓለምን ስትዞር ነበረችው ግሎሪያ አታንሞ ናት።

''በሄድኩባቸው የዓለም ክፍሎች ሁሉ ብቻዬን ተቀምጬ ሰዎች አትኩረው ያልተመለከቱኝ አልያም ምን ፈልጌ እንደሆነ ያልተጠየቅኩበትን ጊዜ አላስታውስም።'' ትላለች።

በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ

ሴቶች ብቻቸውን ሲሆኑ እንደ ሴተኛ አዳሪ የሚቆጠሩት በሬስቶራንቶች ወይም በመጠጥ ቤቶች ውስጥ ብቻ አይደለም። በተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያዎች ላይ እንኳን ብቻቸውን ቆሙ ሴቶች ከብዙ ወንዶች የተለያዩ ጥያቄዎች ይቀርቡላቸዋል።

ለምሽቱ ስንት ልክፈልሽ ከሚሉት እስከ ብቻሽን ከምትሆኚ ከእኔ ጋር ብንሄድስ እስከሚሉት ድረስ እንዳጋጠሟት ሼሪ ኮሊንስ የተባለች ሴት ተናግራለች።