የዚምባብዌ ወታደሮች ሰልፈኞችን በተለያየ መንገድ ሲያሰቃዩ ነበር ተባለ

የዚምባብዌ ተቃውሞ Image copyright Getty Images

በዚምባብዌ መንግሥት የተቋቋመው የሰብአዊ መብት ቡድን የሃገሪቱ ወታደሮች በግልጽ የማይስተዋሉ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም የተቃውሞ ሰልፎችን ሲበትኑና አዘጋጆቹን ሲያፍኑ እንደነበረ ገለጸ።

የዚምባብዌው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንዳስታወቀው ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን ለመበተን መንግሥት ወታደሮችን መጠቀሙ የተሳሳተ እርምጃ ነበር ብሏል።

የተቃውሞ ሰልፎቹ የጀመሩት ባለፈው ሳምንት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መናሩ ነበር።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የአውሮፓ ጉብኝት

ቀብሩን አዘጋጅቶ ራሱን ያጠፋው አርሶ አደር

ከወደ ሃራሬ የሚሰሙ ዜናዎች እንደሚዘግቡት ወታደሮቹ ሰልፈኞች ላይ ያልታሰቡና ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ጥቃቶችን በተደጋጋሚ ፈጽመዋል። አንድ ቢቢሲ ያነጋገረው የዋና ከተማዋ ነዋሪ እንደገለጸው ወደ 30 የሚጠጉ ሰልፈኞች በድንገት በወታደሮች ተከበው ከፍተኛ ድብደባ ሲደርስባቸው ተመልክቷል።

ከ14 ወራት በፊት በወታደሮች እርዳታ ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሙሉ ወታደራዊ ስልጣን መያዛቸው ደግሞ በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬን ፈጥሯል።

ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመውን የኃይል እርምጃ እንደማይታገሱ ገልጸዋል።

የሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ እስካሁን 8 ሰዎች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን የሞታቸው ምክንያት ደግሞ በተፈጸመባቸው ጥቃት ነው።

የተቃውሞ ሰልፎቹ በተካሄዱባቸው አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ዜጎች ደግሞ ዋነኛ ሰለባዎች ነበሩ ብሏል ሪፖርቱ።

መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች

ሱዳን ሁለት የውጪ ሃገር ጋዜጠኞችን አገደች

የዚምባብዌ መከላከያ ኃይል አባላትና የሪፐብሊኩ ፖሊስ ሃይል አባላት አንድ ላይ በመሆን በፈጸሙት የማሰቃየት ተግባር እድሜያቸው እስከ 11 ዓመት የሚደርሱ ህጻናትም ጭምር በሌሊት ከቤታቸው ተወስደው መሬት ላይ እንዲተኙ በማድረግ ድበደባና ማሰቃየት ደርሶባቸዋል ሲል ኮሚሽኑ አገኘሁት ያለውን መረጃ ይፋ አድርጓል።

ምንም እንኳን የሰብአዊ መብት ኮሚሸኑ የሟቾች ቁጥር 8 ነው ቢልም አንዳንድ ሰዎች ግን በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 12 ይደርሳል በማለት ይከራከራሉ።