ጋምቢያ ከሴኔጋል ጋር የሚያገናኛትን ድልድይ ገነባች

የተገነባው ድልድይ Image copyright AFP

በጋምቢያ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የንግድ ግንኙነት የሚያሳልጥ ነው።

ጋምቢያ ኢፖኒሞስ በተሰኘ ወንዝ አቅራቢያ የምትገኘው ጋምቢያ በሶስቱም አቅጣጫዎቿ ከሴኔጋል ጋር ትዋሰናለች።

1.9 ኪሎሜትር ( 1.2 ማይል) ርዝመት ያለው ይሄው የጋምቢያ-ሴኔጋል ድልድይ ግማሽ ያህሉን የጋምቢያን ክፍልና በሰሜናዊ ሴኔጋል የሚገኙ ህዝቦችን ወደ ደቡባዊው ሴኔጋላዊ ግዛት በቀላሉ እንዲጓጓዙ ያስችላቸዋል።

አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ወደ ባህር ዳር ተወሰዱ

ታማሚዋን ያስረገዘው በቁጥጥር ስር ዋለ

ድልድዩ ከመሰራቱ አስቀድሞ ሰዎች አስተማማኝ ያልሆነና ለህይወታቸው አስጊ የሆነ የእቃና የሰው ማጓጓዣ መርከብ ይጠቀሙ ነበር ። ይህንን ካላደረጉም ረጂም ጊዜ የሚወስደውን የጋምቢያን መንገድ መጠቀም ግድ ይላቸዋል።

የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችም ቀናት አሊያም ሳምንታት ሊወስድባቸው ይችላል - ሴኔጋል ለመድረስ ፤ ይህም የሚያጓጉዟቸው ምግብ ነክ ቁሳቁሶች እንዲበላሹ ምክንያት ይሆን ነበር።

በአሁኑ ሰዓት ከሴኔጋል መዲና -ዳካር ወደ ካሳማንቼ ዚጉንቾር ለመድረስ የሚፈጀውን የአንድ ቀን አሊያም ከዚያ በላይ ጉዞ ወደ አምስት ሰዓት ዝቅ አድርጎታል።

ይሄው 7 ዓመታትን የፈጀው ድልድይ ባሳለፍነው ሰኞ በጋምቢያው ፕሬዚዳንት አዳማ ባሮውና በሴኔጋሉ ፕሬዚደንት ማኪ ሳል ተመርቆ የተከፈተ ሲሆን የአገራቱ ዜጎችም ደስታቸውን ገልጸዋል። ሰዎችም ለመጀመሪያ ጊዜ በድልድዩ የመሻገር እድልን አግኝተዋል።

በወቅቱም ሴኔጋላዊው ታዋቂው ሙዚቀኛ ዮሶ ዶር ለተሰበሰበው ህዝብ የሙዚቃ ስራውን አቅርቧል።

Image copyright AFP

አንድ አሽከርካሪ " ይሄንን መንገድ ላለፉት 15 ዓመታት ተጉዤበታለሁ ፤ እስካሁን የነበረው ድካሜ በዚህ መልኩ ስለተቃለለ ፈጣሪየን አመሰግናለሁ" ሲል የተሰማውን ደስታ ለቢቢሲ ተናግሯል። ድልድዩ የሁለቱን አገራት ግንኙነትም ያጠናክራል ሲል አስተያቱን ሰጥቷል።

የጂግጂጋ ነዋሪ ጥንዶች ስጋት ላይ ነን እያሉ ነው

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የአውሮፓ ጉብኝት

ሌላኛው አሽከርካሪም እንዲሁ "የእቃ መርከቦችን ለመጠቀም ከ 10- 20 ቀን መጠበቅ ግድ ይለኝ ነበር ፤ ይህ ደግሞ አሽከርካሪዎችን ብቻ ሳይሆን ያለውን የንግድ ግንኙነት የሚያዳክም ነበር ።" ሲል ተናግሯል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳል የአፍሪካ ልማት ባንክ ለግንባታው ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ፕሬዚደንት ባሮው በበኩላቸው ድልድዩ ለዘመናት የነበረውን የትራንስፖርት ችግር ያስወገደ ሲሉ ተደምጠዋል።

በአሁኑ ሰዓት ድልድዩን ለመጠቀም ለትንንሽ መኪናዎች 5 የአሜሪካ ዶላር (140 ብር) ይከፍላሉ ፤ ሌሎች ከባድ ተሽከርካሪዎች ግን ከመጭው ሀምሌ ወር ጀምሮ አገልግሎቱን እንደሚያገኙ ተገልጿል።

ተያያዥ ርዕሶች