የቻይና ድርጅቶች ለሴቶች የትዳር አጋር መፈለጊያ እረፍት እየሰጡ ነው

ወጣት ቻይናዊት ሴት ራሷን ስታስውብ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የቻይና መንግስት ሴቶች እንዲያገቡና እንዲወልዱ እያበረታታ ነው።

ቤተሰብ ለመጠየቅ፣ ለመዝናናት፣ ጉዳይ ለማስፈፀም፣ አሊያም ጉብኝት ለማድረግ ከመስሪያ ቤትዎ የሥራ እረፍት ፈቃድ ይጠይቁ ይሆናል። ውሃ አጣጭን ለመፈለግ የሥራ እረፍት ጠይቀው ያውቃሉ? ማን ያውቃል...

ቻይና ቅጥ ያጡ ሰርጎችን ልትቆጣጠር ነው

በቻይና በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በአዲስ ዓመት ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት የሥራ እረፍት ለመውጣት እየተዘጋጁ ነው።

ይሁን እንጂ አንዳንድ እድለኛ ተቀጣሪዎች ደግሞ በ30 ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ያላገቡ ሴቶች ተጨማሪ የ8 ቀን ፈቃድ የማግኘት እድል ቀንቷቸዋል።

ለምን ለእነሱ ብቻ ልትሉ ትችላላችሁ፤ ነገሩ ወዲህ ነው- ፍቅርን እንዲያማትሩ፤ ውሃ አጣጫቸውን እንዲፈልጉ ለማስቻል ታስቦ ነው።

በደቡብ ቻይና የሚገኝ አንድ የዜና ገፅ እንዳስታወቀው በቻይና ሚገኙ ሁለት ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸው ተጓዳኛቸውን መፈለጊያ እረፍት እንዲወስዱ ፈቅደዋል።

ይህንን ተከትሎም በከተማዋ የሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ያላገቡ ሴት መምህራን የህይወት አጋር ለመፈለግ የሚያስችላቸውን 'የፍቅር ፈቃድ' ተጠቃሚ ሆነዋል።

የቻይናውያንን ኑሮ ለማወቅ አምስት ነጥቦች

በቻይና በ20ዎቹ መጨረሻ የሚገኙና ያላገቡ ሴቶች በቻይንኛ 'ሸንግ ኑ' ወይም ቁሞ ቀር ይባላሉ። ቢሆንም ግን ይሄው ልማድም እየተባባሰ መጥቶ አብዛኞቹ ሥራቸው ላይ ማተኮርና ሳያገቡ መቆየትን ይመርጣሉ።

ሴቶች ሳያገቡ የመቆየታቸው ጉዳይ ግን አሳሳቢ እየሆነ ነው፤ የአገሪቱ መንግሥትም እየቀነሰ የመጣው የህዝብ ብዛትና የአምራች ኃይል እጦት እንቅልፍ የነሳው ጉዳይ ሆኗል፤ ሴቶች እንዲያገቡና እንዲወልዱም እየጎተጎተ ይገኛል።

በአንድ ጀንበር ሁለት ሚስት ያገባው ጎረምሳ

'ሌፍት ኦቨር ውማን' እና 'ቤትሬይንግ ቢግ ብራዘር' በተባሉ መፅሐፎቿ የምትታወቀው ሌታ ሆንግ ፊንቸር የተባለችው ቻይናዊ ፀሐፊ በ20ዎቹ መጨረሻ በሚገኙ ያላገቡ ሴቶች ያለው አመለካከት የተዛባ እንደሆነ ትናገራለች።

በተለይ የተማሩ ሴቶች እንዲያገቡና ልጅ እንዲወልዱ የማበረታታቱን ተግባር መንግሥት እየሰራ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልፃለች።

ከአራት ዓመታት በፊት የአንድ ልጅ ፖሊሲ ከተነሳ በኋላ የውልደት መጠን እየቀነሰ መጥቷል፤ የተጋቢዎች ቁጥርም ከስድስት ዓመታት አንስቶ እያሽቆለቆለ ነው።

ባሳለፍነው ዓመት የ15 ሚሊዮን ህፃናት ውልደት የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ2 ሚሊዮን ቀንሷል።

ፀሐፊዋ አገሪቷ ስትከተለው በነበረው የአንድ ልጅ ፖሊሲና ወንዶች እንዲወለዱ የሚያበረታተው ልማድ የፆታ አለመመጣጠን እንዳስከተለ ትናገራለች።

ተጭበርብራ የተሞሸረችው ሴት አፋቱኝ እያለች ነው

"አሁን ላይ በአገሪቱ የሴቶች እጥረት ተከስቷል፤ እንደ መንግሥት ሪፖርት ወንዶች ከሴቶች በ30 ሚሊየን ይበልጣሉ" ትላለች።

በቻይና የሚገኝ የማህበራዊ ሳይንስ አካዳሚ እንዳስታወቀውም የህዝብ ብዛት በሚቀጥሉት 50 ዓመታት ከ1.4 ወደ 1.2 ቢሊየን ሊቀንስ እንደሚችል ጠቁሟል።

ይህ ደግሞ በአገሪቷ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ያስከትላል በሚል ስጋት ጭሯል።

Image copyright Getty Images

ግራ ጎኔ ወዴት አለህ?

ምንም እንኳን ሴቶች የትዳር አጋራቸውን እንዲፈልጉና ራሳቸውን እንዲተኩ የሚያስችል የሥራ ፈቃድ መስጠቱ ችግሩን ምን ያህል ሊለውጠው እንደሚችል ግልፅ ባይሆንም አንድ አንዳንድ የሰው ኃይል አስተዳደሮች ፈቃድ መስጠቱ ጠቀሜታ አለው ይላሉ።

በአንድ ድርጅት ውስጥ የሰው ኃይል አስተዳደር የሆኑት ሁዋንግ ሊ "አንዳንድ ሴቶች ከውጪው ዓለም ጋር ያላቸው ግንኙነት ውስን ነው፤ በመሆኑም ለሴት ሰራተኞች ተጨማሪ ፈቃድ በመስጠት ከተቃራኒ ፆታ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠናክሩ እድል መፍጠር ይቻላል" ሲሉ አስተያታቸውን ሰጥተዋል።

ምንም እንኳን ውጤቱ ያን ያህል አዋጭ ላይሆን ቢችልም ውሃ አጣጭ መፈለጊያ የሥራ ፈቃዱ በሰራተኞች ዘንድ ተቀባይነት እንዳገኘም አክለዋል - ሁዋንግ ሊ።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ