የዚምባብዌው ታዋቂ ሙዚቀኛ በ66 ዓመቱ በሞት ተለየ

ኦሊቨር ምቱኩድዚ Image copyright Getty Images

በዚምባብዌ የሙዚቃ ታሪክ እጅግ ተወዳጁና ለ40 ዓመታት ድንቅ ሙዚቃዎችን ሲያቀነቅን የኖረው ኦሊቨር ምቱኩድዚ በ66 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በፈረንጆቹ በ1970 አካባቢ የነጮችን የበለላይነት የሚቃወሙ ሙዚቃዎችን በመጨወት ነበር ኦሊቨር እውቅናን ማትረፍ የጀመረው።

የሙዚቃ ግጥሞቹ ማህበራዊ ለውጥን፣ የፖለቲካ አስተሳሰቦችንና አንዳንዴም ስለ ኤችአይቪ ኤድስ የሚያትቱ ነበር።

የጂግጂጋ ነዋሪ ጥንዶች ስጋት ላይ ነን እያሉ ነው

አዲሱ የካርዲፍ ሲቲ ፈራሚ የገባበት አልታወቀም

በ2001 ዓ.ም. 'ዋሳካራ' የተሰኘው ሙዚቃው እጅግ አነገጋሪና ተወዳጅ ሆኖ ነበር። የሙዚቃው ትርጓሜም በጣም አርጅተዋል እንደማለት ሲሆን ብዙዎች ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ መልእክት ለማስተላለፍ ፈልጎ እንደሆነ ይናገራሉ።

የቀድሞው ፕሬዝዳንትም ሙዚቃው ለአድማጮች ጆሮ እንዳይደርስ ለማገድ ጊዜ አልፈጀባቸውም ነበር።

ኦሊቨር ምቱኩድዚ ሃገርኛ የሙዚቃ ስልቶችን ከዘመናዊው በማቀላቀል የራሱ የሆነ 'አፍሮ ጃዝ' የተሰኘ የሙዚቀቃስልት የፈጠረ ሲሆን አድናቂዎቹ ደግሞ ስራዎቹን 'ቱኩ ሚዩዚክ' በማለት ይጠሯቸው ነበር።

ለአርባ ዓመታት ዚምባብዌያውያንን ሲያስተምርና ሲያዝናና የቆየው ሙዚቀኛ ኦሊቨር ምቱኩድዚ 67 የሙዚቃ አልበሞችን በማሳተም ዓለምን ዞሯል።

በአሜሪካ መቀመጫውን ያደረገው የዚምባብዌው ሙዚቀኛ ቶማስ ማፕፉሞ በዜናው እጅግ ማዘኑን በመግለጽ ኦሊቨር ድንቅ ሙዚቀኛ ብቻ ሳይሆን የነጻነት ታጋይም ነበር ብሏል።

ዋትስአፕ በተደጋጋሚ መልዕክት ማጋራትን አገደ

ባለፈው ጥቅምት ወር የለቀቀው ' ሃንያ ጋ' የተሰኘው የመጨረሻ አልበሙ የሃገሩ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ የሚገልጽ ነበር። የቀድሞው ዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ከ37 ዓመታት በኋላ ስልጣን መልቀቃቸውና አዲሱ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ መተካታቸው ብዙም ያስደሰተው አይመስልም ነበር።