መስታወት መፃዒውን ጊዜ ማየት እንደሚያስችል ያውቁ ኖሯል?

ብዙ መስታወቶች Image copyright AP

መስታወቶች በሚያስገርምና ለመግለጽ በሚከብድ መልኩ አብዛኛዎቻችንን ይስቡናል። መስታወት ተመልክቶ የእራሱን ነጸብራቅ ለማየት የማይጓጓ አለ ብሎ ማሰብ ይከብዳል።

ሌሎች ሰዎች የሚመለከቱትን የእኛን ገጽ የማየት እድል የሚኖረን በመስታወቶች ብቻ መሆኑ ደግሞ ዝም ብለን ማለፍን ከባድ ያደርገዋል።

አብዛኛዎቻችን ጥሩ የሚባል ፈገግታችንን የምንለማመደው፣ ንግግር ለማድረግ የምንዘጋጀው አልያም የለበስነውን ልብስ ማማር የምናየው ከመስታወት ፊት በመቆም ነው።

13 አስደናቂ የፓስፖርት እውነታዎች

ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች

መስታወቶች ከላይ ከጠቀስናቸው ጥቅሞች በተጨማሪ ለብዙ ነገሮች አገልግሎት ላይ ይውሉ እንደነበረ ያውቃሉ?

1. የወደፊቱን ለማየት

Image copyright Empics
አጭር የምስል መግለጫ ምን ይታይዎታል?

በጥንታዊቷ የግሪክ ከተማ ቴሳሊ ይኖሩ የነበሩ የወደፊቱን የሚተነብዩ የሃይማኖት መሪዎች መስታወቶችን በዋነኛነት ይጠቀሟቸው ነበር። የእንስሳትን ደም በመጠቀም መስታወቶቹ ላይ ህጎችን ይጽፉም ነበር።

በጥንታዊ ሮማውያንም መስታወቶች ለተመሳሳይ አገልግሎት ጥቅም ላይ ይውሉ ነበር። የሮም ቄሶች ያለፈውን፣ የአሁኑንና የወደፊቱን ለማየት ይጠቀሙበት እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ።

2. ከሌላ ዓለም ጋር የመገናኛ መንገድ

Image copyright Getty Images

ዘመነኛ መስታወቶች የአልሙኒየም ብናኝ የሚጠቀሙ ሲሆን የጥንት ግብጻውያን ግን የተወለወሉና ከኮፐር የተሰሩ እቃዎችን ይጠቀሙ ነበር።

ኮፐር ደግሞ 'ሃቶር' ከምትባለው የግብጽ መልዐክ ጋር ተያይዞ ይነሳል። በመስታወቱ አማካይነት ከዚህች መልዐክ ጋር መገናኘት እንደሚችሉ ያምኑም ነበር።

የአዝቴክ ሰዎች ደግሞ ከእሳተ-ገሞራ የተገኙ ድንጋዮችን እስኪያብረቀርቁ ድረስ በመወልወል እንደ መስታወት ይጠቀሙ ነበር። 'ቴዝካትሊፖካ' የተባለው አምላካቸው ደግሞ መስታወቶችን እንደ በር በመጠቀም ወደ ምድር ሰዎች ይመጣ እንደነበር ያምናሉ።

'ቴዝካትሊፖካ' የምሽት፣ የሰዓትና የቀድሞ አባቶች ትውስታ አምላክ ነው ተብሎ ይታመን ነበር።

ልባችን ከእድሜያችን ቀድሞ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ?

ልጆችዎ ጤናማ ምግብ እንዲመገቡ ማድረጊያ መላዎች

3. የኃይል ምንጭ

Image copyright Getty Images

ቻይና ውስጥ መስታወቶች ብርሃንን፤ በተለይም የጨረቃን ብርሃን ለመሰብሰብ ግልጋሎት ይሰጡ እንደነበር ይነገራል።

እንደውም ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት የነበረ አንድ የቻይና ንጉስ የጨረቃንና የጸሃይን ሃይል ለመሰብሰቢያነት በተጨማሪ የሰዎችን ትክከለኛ ማንነት ለመለየት ይጠቀምበት ነበር።

ኪን ሺ ሁዋንግ የተባለው ንጉስ ሰዎች ወደ መስታወቱ ሲመለከቱ ትክክለኛ ማንነታቸውን ያሳየኛል በማለት ብዙ ተከታዮችን አፍርቶ ነበር።

4. እውነት መናገር

Image copyright Getty Images

መስታወቶች ቀደም ብለው ያዩትን ነገር አስቀምጠው በሌላ ጊዜ እንደሚያሳዩ በብዙ የዓለማችን ክፍሎች ይታመን ነበር። ጥያቄ በተጠየቁ ጊዜም እውነቱን ይናገራሉ የሚል እምነት አለ።

'ስኖው ዋይት' የተባለው ታዋቂው የሆሊዩድ ፊልምም በዚህ ሃሳብ ላይ የተመሰረተ ነው። ሎህር በተባለ ግዛት፤ በአሁኗ ጀርመን ማለት ነው፤ አንድ ንጉስ አዲስ ላገባት ሚስቱ ትልቅ መስታወት አበርክቶላት ነበር።

መስታወቱ ለተጠየቀው ጥያቄ እውነተኛውን መልስ ይሰጥ ነበር ይባላል። ይህ መስታወት በአሁኑ ወቅት በጀርመን 'ሎህር' ቤተመንግስት ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል።

ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?

ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል የሚረዱ ዘጠኝ ሚስጥሮች

5. ከመስታወት ጋር የተያያዙ እምነቶች

Image copyright Getty Images

መስታወትን ከመስበር ጋር የተገናኙ ብዙ ጥሩና መጥፎ የሚባሉ እምነቶች በመላው ዓለም አሉ።

በጥንት ሮማውያን እምነት አንድ ሰው መስታወት ከሰበረ ለሰባት ዓመታት ጥሩ ያልሆኑ ነገሮች ይገጥሙታል። ሰባት ዓመት የሆነበት ምክንያት ደግሞ የሰው ልጅ ህይወት በየሰባት ዓመቱ እንደሚቀየር ስለሚያምኑ ነው።

ነገር ግን የመስታወቱን ስብርባሪዎች ሰብስቦ መቅበር አልያም ወደ ወንዝ መወርወር ይህንን መጥፎ አጋጣሚ እንደሚሽረውም ያምናሉ።

በፓኪስታን ደግሞ መስታወት መስበር መጥፎ መንፈስን እንደ ማባረር ተደርጎ ይታሰባል። ልክ መስታወት ሲሰብሩ በቤትዎ ውስጥ የነበረ እርኩስ መንፈስ ጥሎት ይጠፋል ማለት ነው።

6. መስታወት መገልበጥ

Image copyright Getty Images

እንግሊዝን ጨምሮ በብዙ የዓለማችን ክፍሎች በስፋት የሚታመን አንድ እምነት አለ። አንድ ሰው ሕይወቱ አልፎ የቀብር ስነ ስርአቱ ሲፈጸም በቤቱ ውስጥ ያሉ መስታወቶች ሁሉ ተገልብጠው እንዲቀመጡ ይደረጋሉ።

ይህ የሚደረገው ደግሞ የሟች ነፍስ መስታወት ውስጥ ተይዛ ትቀራለች ተብሎ ስለሚታመን ነው። ይህ ተግባር በአሜሪካ፣ ቻይና፣ ማዳጋስካርና ሩሲያ አካባቢ ይስተዋል ነበር።

ይህ ተግባር አሁንም ከሚካሄድባቸው መካከል ደግሞ እስራኤል ትጠቀሳለች። ለሳምንት በሚቆየው የሃዘን ሥነ-ሥርዓት በቤቱ ውስጥ ያሉ መስታወቶች በሙሉ ተገልብጠው አልያም ራቅ ብለው እንዲቀመጡ ይደረጋሉ።

8. ትክከለኛ ማንነት

Image copyright Getty Images

በአንዳንድ የጥንት ባህሎች መሰረት ደግሞ መስታወት የአንድን ነው ትክክለኛ ማንነት የማሳየት ሃይል እንዳለው ይታሰባል።

በጥንት እምነቶች መሰረት የሰው ልጅ ደም የሚጠጡ 'ቫምፓየር' በመባል የሚጠሩት ፍጡራን ነብስ ስለሌላቸው መስታወት አጠገብ ቢቆሙ እንኳን ነጸብራቃቸውን በመስታወት መልሰው መመልከት አይችሉም ተብሎ ይታሰባል።

ተያያዥ ርዕሶች