የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሂጃብ ጉዳይ የመጨረሻ ውሳኔ አሳለፈ

ተማሪዎች በትምህርት ቤት Image copyright AFP

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለዓመታት ሲያከራክረው በነበረው የሂጃብ ጉዳይ የመጨረሻ የሚባል ውሳኔ ሰጥቷል። ውሳኔው ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን የአለባበስ መመሪያ ማውጣት እንደሚችሉ አረጋግጧል።

ይህ የፍርድ ውሳኔ የታችኛውን ከፍተኛ ፍርድ ውሳኔ የሚቀለብስ ነው።

ዴንማርክ ሙሉ የፊት ገጽታን የሚሸፍን 'ሂጃብ' አገደች

ሂጃብ ለባሿ የሕግ ብቃት መመዘኛ ፈተና ላይ እንዳትቀመጥ ተከለከለች

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በትምህርት ቤት ሂጃብ የመልበስ መብታቸውን አስከብሮላቸው ነበር። ፍርድ ቤቱ መብቱን አጎናጽፎ የነበረው በ2014 ሦስት ወላጆች በቅዱስ ጳውሎስ ኪዋንጃኒ ትምህርት ቤት ሴት ልጆቻቸውን ሂጃብ እንዳይለብሱ መከልከሉን በመቃወም ክስ በመክፈታቸው ነበር።

የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ከተመለከተ በኋላ ትምህርት ቤቱ ሂጃብ መከልከሉ አግባብ ነበር ሲል ወስኖ የነበረ ቢሆንም በይግባኝ ይህ ዉሳኔ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቀልብሶ ነበር።

በመጨረሻም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዚህ በኋላ ማንኛውም ትምህርት ቤት ትክክል የሚለውን አለባበስ የመወሰን መብትን አጎናጽፏል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ