በማሌዥያ ሁለት የዕድሜ ባለፀጎች የነፃ ምግብ እደላ ሲጠብቁ ሕይወታቸው አለፈ

ማሌዥያ ስካይላይን Image copyright Getty Images

በዓላት በመጡ ቁጥር ረዳት የሌላቸውን ሰዎች መጎብኘት፣ ማብላትና ማጠጣት በኢትዮጵያ የተለመደ ነው። ይሁን እንጂ በጎ ተግባሩ በዓላትን ብቻ ጠብቆ መከናወኑ ችግሩን መቅረፍ አልቻለም።

የሞት አፋፍ ላይ ቢሆኑ የመጨረሻ ምግብዎ ምን ይሆናል?

በማሌዥያ በሚቀጥለው ሳምንት የሚከበረውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለአረጋውያን የነፃ ምግብ እደላ ተካሂዶ ነበር። ዜናውን የሰሙ የአካባቢው አረጋውያን ወደ ስፍራው ተመሙ። ቁጥራቸውም ከተጠበቀው በላይ ሆነ።ይህ መሆኑ ባልከፋ- ችግሩ የነፃ ምግብ ስጦታው ለ200 ሰዎች ብቻ የተወሰነ መሆኑ ነበር።

በመዲናዋ ኳላላምፑር ፑዱ ግዛት ለተካሄደው የነፃ ምግብ እደላ ዝግጅትም ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎችም አጋጣሚውን ለመጠቀም ወደ ሥፍራው አቀኑ። 'ኩፖኑንም'( ስጦታውንም) ለማግኘት ባለ በሌለ ኃይላቸው ርስ በርስ መገፋፋት ጀመሩ። ሁለት ሴት የእድሜ ባለፀጎችም ነፃ የምግብ 'ኩፖን' ለማግኘት በተፈጠረ መገፋፋትና መተፋፈግ ሕይወታቸው አለፈ።

አንድ የፀጥታ አስከባሪ ለአገሩ መገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቀው ጩኸት እንደሰማና ሰዎች እርስ በርስ ሲገፋፉ እንዳየ ተናግሯል።

የአገልግል ምግብ አምሮዎታል?

የ78 ዓመቷ ሎው ኦን ናግ እና የ85 ዓመቷ አህ ፖህ ተራቸውን ሲጠባበቁ በነበረበት ወቅት አየር አጥሯቸው ለመተንፈስ ሲቸገሩ ነበር ተብሏል።

ዝግጅቱ የተካሄደበት ፑዱ ኢንቴግሬትድ የንግድ ማዕከል አስተዳዳሪ እንደተናገሩት ፕሮግራሙ በመጭው ሳምንት የሚከበረውን አዲስ ዓመት ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

'ኩፖኑም' የታደለው ለእድሜ ባለፀጎች ብቻ የነበረ ሲሆን በወቅቱ በአጠቃላይ አራት ሰዎች ራሳቸውን ስተው ነበር ሲሉ አክለዋል-ኃላፊዋ።

የአገልግል ምግብ አምሮዎታል?

የ60 ዓመቱ የፀጥታ አስከባሪ በበኩላቸው 'ኩፖኑን' ለመቀበል በአንድ ጊዜ አራት ሰዎች ብቻ መግባት ይፈቀድላቸው እንደነበር አስረድተዋል።

"እንዲሰለፉ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ በመጣስ እርስ በርስ መገፋፋት ጀመሩ" ሲል አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ ፀጥታ አስከባሪም ሁኔታውን ገልፆታል።

ሻሃሩዲን አብዱላህ የተባሉ የፖሊስ ኃላፊ የመተንፈስ ችግር ያጋጠማቸው ሌሎች አዛውንቶች መኖራቸውንም አስታውቀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ