አሜሪካዊው ዶክተር ለአራት አመት ህፃን ዕፀ ፋርስ አዘዘ

ዕፀ ፋርስ

አሜሪካዊው ዶክተር ለአራት አመት ህፃን ልጅ የእፀ ፋርስ ብስኩት ማዘዙን ተከትሎ የሙያ ፍቃዱ እንዳይሰረዝ በመከራከር ላይ ነው።

የተፈጥሯዊ መድኃኒት ባለሙያ የሆነው ዶ/ር ዊልያም ኤይደልማን እንደሚናገረው በጥቂቱ እፀ ፋርስን መውሰድ ህፃኑ ያለበትን ከፍተኛ የሆነ ግልፊተኝነት ቀዝቀዝ እንዲያደርግለት ነው።

የዶክተሩ ምርመራ ልጁ የስሜት መዋዠቅን የሚያስከትለው ባይፖላር ዲስኦርደርና የትኩረት እጥረት ችግሮች እንዳለበት የሚያሳይ ቢሆንም ይህ ግን ስህተት እንደሆነ ተገልፆ ነበር።

ይህንንም ተከትሎ ህክምናን የሚቆጣጠሩ የቦርድ አባላት የስነልቦና ባለሙያዎችን ባለማማከርና በቸልተኝነት ወንጅለውታል።

"ዕፀ ፋርስ በመሸጥ ልጆቼን አሳድጋለሁ" የሌሴቶዋ አምራች

የልጁ አባት የልጁ ባህርይ ነውጠኛ በመሆኑ ከጥቂት አመታት በፊት ዶክተሩን ባማከሯቸው ወቅት ነው ዕፀ ፋርሱን ያዘዘወ።

ዶክተሩም በመጠኑ ዝቅተኛ የሆነ እፀ ፋርስ ያዘዘለት ሲሆን ይህም ይፋ የወጣው የትምህርት ቤቱ ነርስ በምሳ ሰዓት ላይ ከእፀ ፋርስ የተሰራውን ብስኩት እንድትሰጠው በመጠየቋ ነው።

ቦርዱ የዶክተሩ ፍቃድ እንዲሰረዝ የጠየቀው ዕፀ ፋርስን በማዘዙ ሳይሆን የምርመራው ውጤት ቸልተኝነት የተሞላበት በመሆኑ ነው ተብሏል።

ካናዳ ዕፀ ፋርስን ህጋዊ አደረገች

የልጁ አባት በበኩሉ ህፃን እያለ የስሜት መዋዠቅን የሚያስከትለው ባይፖላር ዲስኦርደርና የትኩረት እጥረት ችግሮች አለው በመባሉ ብዙ መድኃኒቶችን ይወስድ እንደነበር ተናግሯል "መሞከሪያ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ብሏል።

በኋላም እፀ ፋርስን መጠቀም የጀመረ ሲሆን መረጋጋትን እንዳመጣለትና፣ ባለቤቱ ላይ ያሳየው የነበረው ግልፍተኝነት ሙሉ በሙሉ እንደተቀየረም ይናገራል።

"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ

ከዚህ ቀደምም የስሜት መዋዠቅን የሚያስከትለው ባይፖላር ዲስኦርደርና የትኩረት እጥረት ችግሮች ላሉበት ለትልቁ ልጁም እፀ ፋርስን እንደሚሰጠው አባትየው አሳውቋል።

አባትየው እንደሚናገረውም ዕፀ ፋርስ በሁለቱም ልጆቹ ላይ በጎ የሆነ አስተዋፅኦ እንዳለው ነው።

ዶ/ር ኤይደልማን ውሳኔውን ተቃውሞ የህክምና ሙያቸውን እንደሚቀጥል ተናግሯል። ጠበቆቹ በበኩላቸው ፍቃዱ እንዳይሰረዝ ማድረግ መቻላቸውንና ጉዳዩም በቀጠሮ እንደተያዘ ገልፀዋል።

ለመድኃኒትነት የሚውለው ዕፀ ፋርስ በካሊፎርኒያ ከአውሮፓውያኑ 1996 ጀምሮ ፍቃድ ያገኘ ሲሆን ዶ/ር ኤይደልማንም በሺዎች ለሚቆጠሩ ህመምተኞችም ዕፀ ፋርስን አዟል።