አሮን ሰናይ: "አክሱምና ላሊበላ ለፈጠራ እና ለዲዛይን ሥራዎቼ የመስፈርቴ ጣሪያ ናቸው"

ኢትዮጵያዊት ሞዴል በአሮን ዲዛይን የተደረገ ልብስ ለብሳ Image copyright Aron Senay

አሮን ሰናይ ሕግንና ኢኮኖሚክስን አጣምሮ አጥንቶ ዲግሪውን ጨብጧል። የተመረቀበት ሙያ ግን አሁን እንጀራ ይሁነኝ ብሎ፣ አልባሳትንና ቦርሳዎችን ዲዛይን እያደረገ ከሚሰራው ሥራ ጋር አይገናኝም። ።

"ዲዛይን ማድረግ በሁሉም ሰው ውስጥ ያለ ሙያ ይመስለኛል" ይላል አሮን። ባለሙያዎቹ ከሌሎቹ የሚለዩት ውስጣቸው ያለውን የሃሳብ ድርና ማግ መልክ አስይዘው፣ ወረቀትና ጨርቅ ላይ ስለሚያሰፍሩት እንደሆነ ይመሰክራል።

"ኮሜዲ፣የጤፍ ዝናብ ነው" ቤቲ ዋኖስ

ቀራፂው ስለ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት ይናገራል

ከፋሽን ጥበብ ጋር ያወዳጀውን ነገር ሲያስታውስ "ቤተሰቦቼ፣ ከአያቴ ከወይዘሮ ንግሥቲ ጀምሮ፣ ወንዱም ሴቱም አለባበስ አዋቂ፣ ሽቅርቅር ነበሩ" ይላል፤ "በተለይ ሴቶቹ ዘናጭ ናቸው" ሲል ያሞካሻቸዋል።

Image copyright Aron Senay

አያቱ ወይዘሮ ንግሥቲ ነርስ ነበሩ፤ ዘመናቸውን ሁሉ የሃገር ባህል ልብስ ነበር የለበሱት። ይኖሩበት በነበረው አዳማ (ናዝሬት) የሚያያቸው ሁሉ የሚያስታውሳቸው እንደ ወተት ነጭ በሆነ ቀሚሳቸውና በሹሩባቸው ነው።

"ዘወትር ይሳለሟት በነበረችው የማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ይቀመጡበት በነበረው ስፍራ ሰው ሁሉ ያውቃቸዋል" የሚለው አሮን ሁሉም ሰው በመልካምነታቸው የሚያውቃቸው አያቱ ወ/ሮ ንግሥቲን አርዓያ በማድረግ እ.ኤ.አ በ2014 በስማቸው የፋሽኑን ሃሳብ እውን አደረገ።

ከወንጀልነት ወደቀዳሚ መዋቢያነት የተሸጋገረው የከንፈር ቀለም

ሁሌም ይህንን የሕይወት ድግግሞሽ ያለማዛነፍ ለዓመታት ኖረውበታል ይላል ስለአያቱ ሲናገር። "ይህንን የእማዬን የአለባበስ ዘዬ ሳስብ ከእራሷ አለመጣላቷ ይታሰበኛል። ሌሎችን ለማስደሰትና ለመመሳሰል ተብሎ የሚቀየር ነገር አልነበራትም። አሁንም እኔ በዲዛይኔ የሌሎችን ዱካ የማይከተል፣ የእራሴን ደማቅ መስመር ለማስመር፣ የእራሴን የፋሽን ዓለም ለመፍጠር እየሠራሁ ነው" ይላል።

ንግሥቲን የሰባት ዓመት ልጅ እያለሁ ነው የጀመርኩት ያለን አሮን "ያኔ ግን ስም አልነበራትም፤ ዝም ብዬ የተለያዩ ነገሮችን እነድፍ ነበር" ይላል።

ከአስተዳደጉ ባሻገር ስምንት ዓመት የኖረባት ፈረንሳይ ስለፋሽን የአቅሟን ማዋጣቷንም ይመሰክራል።

Image copyright Aron Senay

ጅማሮ

እ.አ.አ በ2014 ፈረንሳይ ሃገር የሬስቶራንት ባለቤት የሆነች አንዲት ግለሰብ በየዓመቱ የምታዘጋጀው የፋሽን ትርዒት ላይ ልታካትተው እንደምትፈልግ ነገረችው። ፈቃደኛ ሆነና ከሃገሩ ሲወጣ ቢበርደኝ የምደርበው ብሎ የያዘውን ጋቢ ተጠቅሞ የፋሽን ትርዒቱን ተቀላቀለ። 5 ሴት ጓደኞቹን ጠርቶ በጋቢው የተለየዩ የፈጠራ ሥራዎቹን አሳየ።

"አያቴ ሰነፍ ሆና አታውቅም፤ የምመርጣቸውም ሞዴሎች ሰነፍ አይደሉም፤ እኔም ሰነፍ አይደለሁም። ስለዚህ የምሠራው ሥራ በስንፍና የታጀበ የአረም እርሻ እንዲሆን አልፈልግም። ዘመን የሚሻገር፣ ዘመኑን የሚከተል በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ ነው የምሠራው" ይላል አሮን ስለሥራዎቹ ሲናገር።

በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው?

በመቀጠልም "እኔ የምሠራው ሴቶችን የበለጠ ውብ የሚያደርጉና ደጀን የሚሆኑ ቦርሳዎችን ነው" ይላል።

ወደ ሃገሩ ሲመለስ፣ የዛሬ ዓመት ቮግ ኢታሊያ፣ ጎተ ኢኒስቲትዩትና ኤፍ ኤ ቱ ፋይቭ ፎር፣ የሚባሉ ማህበራት ባዘጋጁት ውድድር ላይ ሰዎች እንዲወዳደር ጋበዙት። ግብዣውን ተቀብሎ ለውድድር ንግሥቲን ይዞ ቀረበ እናም ለፍፃሜ ደረሰ።

Image copyright Aron Senay

ንግቲ የሴቶች ፋሽን አብዮት

ንግሥቲ የምታተኩረው ሴቶች ላይ ነው። የወንድ ፋሽን ያስቸግረኛል ይላል፤ ቲሸርትና ሸሚዝ ብዙም ጥበብ የማይታይባቸው ፈጠራን የሚያመክኑ ነገሮች ይመስሉታል።

"የሴቶች ነገር ለፈጠራ የሚያነሳሳኝ ሲሆን የወንዶች ምርጫ ግን በትንሽ ነገር ስለታጠረ ስሜት አይሰጠኝም።"

አሮን ቀልቡንና ሃሳቡን አዋህዶ የሚጠበብባቸው የፋሽን ሥራዎች ዘመናዊነትን ግለሰባዊ ማንነትን እንዲያሳዩ ይጥራል። የሚሠራቸው ሥራዎች የሴቶች ቦርሳዎች ብቻ አይደሉም፤ አልባሳትም ዲዛይን ያደርጋል።

ኢትዮጵያዊያን ለምን ሥጋ አይመገቡም?

በእራስ መተማመን ያላቸው፣ እራሳቸውን በሃሳብም በቀለምም መግለፅ የሚፈልጉ ሴቶች፤ ችምችም ካለው የሰው ነዶ መካከል ተለይተው መታየት የሚፈልጉ የፋሽን ተከታዮች የእርሱ የገበያ ትኩረት ናቸው።

በንግሥቲ የሚሠሩት ቦርሳዎችን ስም ያወጣላቸዋል። ስሞቹ ለእራስ ቅርብ የማድረግ ኃይል እንዳላቸው ያምናል። ለምሳሌ 'አክሱም' ብሎ የሰየመው ቦርሳ የአክሱም ሐውልትን መነሻ አድርጎ የሠራው ነው።

Image copyright Aron Senay

"ንጉሱ" ብሎ የሰየመው ሥራው በሴቶች መካከል የተገኘ ብቸኛው ወንድ ነበር። ስራውን በዚያ ሰየመው። ኮቼላ የተሰኘው ሥራው ደግሞ በአምስት መልኩ መያዝ ይቻላል። ሲቀመጥ ደግሞ እግር ኖሮት ሸረሪት ይመስላል ይላል።

ኮቼላ በአሜሪካ የሚዘጋጅ ትልቅ የሙዚቃ ድግስ ነው የሚለው አሮን፣ ቦርሳው እንዲህ ዓይነት ድግስ ላይ የሚገኝ ሰው የሚይዘው ነው ይላል።

በከረዩዎችና በኃይለ ሥላሴ መነሻነት የተሠሩ ቦርሳዎችም የእጅ ሥራው ውጤቶች ናቸው። በጥንቸል መነሻነት የተሠራው ሌላው ሥራ 'ምናለበት' የተሰኘው ነው።

Image copyright Aron Senay

ሥራዎቹን ለማስተዋወቅ የሚጠቀመው ኢንስታግራምን ሲሆን ከሄሎ ካሽ ጋር በመሆን የእራሱን ድረ-ገፅ እየሠራ እንደሆነ ይናገራል።

ከድምፃዊ ቤቲ ጂ ጋር የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች በቀጣዮቹ 5 ዓመታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ መገኘት ይፈልጋል። "ከልጅነቴ ጀምሮ የፍሬንች ሃውስን ዲዛይን ባደርግ ደስ ይለኛል እል ነበር" ያለው አሮን ዛሬም ያ የልጅነት ህልሙ ቢሳካ ደስ ይለዋል።

ደንበኞች

"ኢትዮጵያዊያን በሁሉም አቅጣጫ በፋሽን በደንብ አልተገለፁም" ብሎ የሚያምነው አሮን ሽሮሜዳና መርካቶ የሚሸጡ የባህል አልባሳት የፋሽን አስተሳሰባችንን ቀፍድደው ሳይዙት አልቀሩም ይላል፤ "የፋሽኑ ዓለምም በሚፈለገው መጠን ሲበረታታ አይታይም። የሚታዩ የዲዛይነር ሥራዎችም ጥበብን ማዕከል ያላደረጉ ይበዛሉ" ይላል።

በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት

አሮን የቀደምት አባቶችና እናቶቻችን የፈጠራ እና የጥበብ ውጤት የሆኑትን ሥራዎች በመመልከት በእነርሱ ደረጃ የውሃ ልክነት የእራሱን ሥራዎች መሥራት ይፈልጋል።

ላሊበላን በማነፅ ድንቅ የሥነ-ሕንፃ ባለሙያነትን ያስመሰከሩ፣ አክሱምን አልያም ፋሲለደስን በማቆም የፈጠራ ልህቀታቸውን መስመር ያሰመሩ ኢትዮጵያዊያን፤ ለፈጠራ እና ለዲዛይን ሥራዬ የመስፈርቴ ጣሪያ ናቸው ይላል።

አሮን ኢትዮጵያዊያን በፋሽኑ ዓለም ከምዕራባዊያንም ሆነ ከአፍሪካውያን እንደሚለዩ ተረድቷል። ስለዚህ የፋሽን ሥራዎቹ ሴትነትን የበለጠ እንዲያጎሉ፣ በሚደምቁበት አደባባይም የተሰማሩበትን ተግባር እያከናወኑ፣ የሚከተሉት ፋሽን ደጀን እንዲሆናቸው ይፈልጋል። ሥራዎቹንም ኢትዮጵያዊ አሻራን ከዘመናዊነት ጋር ያጣመሩ እንዲሆኑ ይጥራል።

ውክልናን በቪድዮ

ስለ ጠልሰም ወይም በተለምዶ የአስማት ጥበብ ተብሎ ስለሚጠራው ምን ያህል ያውቃሉ?

ጥበብን በወር-አበባና በአጽም

ባህሉን ሳያፈርስ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሳይጥስ ከደንበኞቹ ማንነት፣ ከሴትነታቸው ጋር ፋሽኑን ማጋመድ የእርሱ ሃሳብ ነው።

አሮን፤ ፋሽን የንግድ ሃሳብም መሆኑን አላጣውም። ዘርፉ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ በፈረንሳይ ለ1 ሚሊዮን ሰዎች የሥራ ዕድል በመፈጠር የ150 ቢሊዮን ዩሮ ባለ ካፒታል ባለቤት ነው ይላል።

ንግሥቲ ለደንበኞቿ የምታቀርባቸው ውጤቶች ይህንን ትልቅ ምስል ያየ የሃገር ውስጥና የውጪውን ዓለም የገበያ አድማስ የዳሰሰ እንደሚሆን ይናገራል።

በሃገር ውስጥ በሕይወት መንገድ ላይ ጥቂት ገንዘብ አጠራቅመው መግዛት የቻሉ፣ እንዲሁም ገንዘብ ያላቸው ሁሉ ደንበኞቹ ናቸው።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ